Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ በትምህርትቤቶች ላይ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ችግር አሳዝኖኛል | AHADU RADIO FM 94.3

በአዲስ አበባ በትምህርትቤቶች ላይ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ችግር አሳዝኖኛል ሲል ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ ገለጸ፡፡
ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርትቤቶች ላይ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ሀገራዊ የምክክር ኮምሽኑ እንዴት ያይዋል ሲል አሀዱ ጠይቋል
በቀላሉ መጨረስ የሚቻለውን ጉዳይ በዚህ ልክ ችግር እስኪፈጠር ድረስ ተግባራዊ መደረጉ አሳዝኖናል ሲሉ የኮምሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮምሽነር ዶክተር ዬናስ አዳዬ ተናግረዋል፡፡
በንግግር መጨረስ የሚቻለውን ነገር ልዩነትን ወደ የሚፈጥር ፤ወደ ግጭቶች እንዲቀየር እና በህይወት እስኪጠፋ ድረስ መድረግ አልነበረበትም ነው ያሉት፡፡
ብዝሀነት የሚደገፍ ቢሆንም ህዝቡን በሚለያይ መልኩ ሳይሆን ባማከለ መልኩ መደረግ አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ኮምሽኑ ለመስራት ያቀዳቸው ስራዎች እንዳልተሳካ የተናገሩት ኮሚሽነሩ እናዚህ ጉዳይዎች በምክክር እና በውይይት እንደሚፈቱ ኮምሽኑ ያምናል ብለዋል፡፡
ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣት እንደሚያስፍልግል ኮምሽኑ የችግሮች መሰረታዊ ምክንያቶች ምንድናቸው የሚለውን ከህዝቡ የመጡ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚቻልም አንስተዋል፡፡
ከህዝቡ የሚመጡ የመዋቅራዊ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማድረግ መንግስት እንዲህ ማድረግ አለበት በሚልም ምክረ ሃሰቦች እንደሚሰጡ አንስተው፤ እንዲህ አይነት ተግባራት የኮምሽኑን አካሄዶች ሊያደናቅፉ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP