Get Mystery Box with random crypto!

ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ africauniondebremihret — ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ africauniondebremihret — ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @africauniondebremihret
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

ባህራን ሚዲያ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የአገልግሎት እንቅስቃሴ፣ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን የምንለቅበት ይፋዊ የቴሌግራም ገጻችን ነው።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-10 15:17:22 "ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት እና ውሳኔ አሰጣጥ"

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት እና ውሳኔ አሰጣጥ" በሚል ርእስ በመምህር ታደሰ ወርቁ ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

በመጀመርያ ደረጃ ኦርቶዶክሳዊነት ስንል ምን ማለት እንደሆነ ማስተዋል ተገቢ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ስንል አምስት ነገሮችን የሚገልጥ ነው

1:-መጸሐፋዊነት:-
ሥርዓቷን ትምህርቷ ከመጸሐፍት የመነጨ ነው።

2:-ትውፊታዊነት
ከሌሎች ቤተ እምነቶች የሚለያት ቅብብሎሽ ወይም ትውፊታዊ መንገዶችን የምትቀበል በመሆኗ ነው።

3:-ቀኖናዊነት
መጸሐፍት እና ትውፊቶች መሠረተ እምነትን ጨምሮ ጸንተው የቆሙት በቀኖና ነው።

4:ዶግማዊ
ዶግማ የማይቀየር የማይሻሻል ማለት ነው ኦርቶዶክሳዊነትም ስንል በሰው መሻት የማይቀየር መሠረተ እምነት ያላት ማለት ነው።

5:-መዋቅራዊነት
ከላይ ያሉትን ጨምሮ የሚይዝ ደግሞ መዋቅር ነው። ይህም ከክርስቶስ የጀመረ ሐዋርያት ሐዋሬያነ አበው ሊቃውንት እያለ ከእኛ የደረሰ ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት

ስለ ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት ስንናገር በእነዚህ መአቀፍ ውስጥ መሆን አለበት። ውሳኒያችን መጸሐፋዊ ትውፊታዊ ቀኖናዊ ዶግማዊ መዋቅራዊ የሆነ ወይም ያማከለ መሆን አለበት ማለት ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት ስንል ምን ማለታችን ነው?

፩:-ጥንተ ተፈጥሮን መጠበቅ:-

የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረ ነው በዚህም ምክንያት የገዢነት ስልጣን ተሰጥቶታል። ከዓራቱ ባሕርያተ ሥጋ እንደመገኘቱ
ዓለመ ሥጋን ገንዘብ አድርጓል ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ እንደመገኘቱ ዓለመ ነፍስን ገንዘብ አድርጓል የሰው ጥንተ ተፈጥሮ ይሄ ነው። አዳም ፍጡር መሆኑ እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑ እንዲታወቅ ዕጸ በለስን አትብላ ተባለ ይህም የፍቅር ህግ ነበር። አዳም ግን የተሰጠውን ሕግ ጣሰ የባሕርይ ጉስቁሉናና የጸጋ መጋፈፍም አገኘውም። ኃላፊነቱን አልተወጣም። ጥንተ ተፈጥሮን መጠበቅ ሰው የመሆን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት መሠረት ነው። አዳምን በኤደን ገነት አኖረው እንዲጠብቃትም አዘዘው። ገነት ያማረች ሳለች ለምን ተንከባከባት አለው? ይሀሰ የሚያሳየን በአንጻረ አዳም ለሰው ልጅ ኃላፊነትን ሲሰጥ
ነው።

፪:- ሌላው ኃላፊነት ማለት የሥላሴ ልጅነትን ጸጋ ማጽናት ነው። በአርባ በሰምንያ የተጠመቀ የሥላሴን ልጅነት ያገኘ ሁሉም ድርሻ አለው ይህንን ጅርሻ መወጣት ነው ኃላፊነት። በሚታይ አገልግልግሎት የማይታይ ጸጋ የሚገኝበት ምሥጢር የሚፈጸምባት ናት።

3 ኃላፊነት ጥሪን ማክበር ነው። የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ደግሞ ጥቂቶች ናቸው እንደተባለው። ይህ ማለት ግን ከብዙዎች መካከል ጥቂቶችን መረጠ ማለት አይደለም። ጥሪውን አድምጠው የመጡትን ሳይሆን ጥሪውን አክብረው የጸኑትን ለመግለጽ ነው። ጥሪው የንሰሐ የአገልግሎት ሊሆን ይችላል ይህንን ጥሪ ማክበር ሲባል ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነትን መውጣት ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ውሳኔ አሰጣጥ

የውሳኔ መአከላት ውሳኔ ስንወስን ከሦስቱ ጉዳዮች ውጪ አንሆንም እነሱም:-
1:-ሰው
2:-ሀገረ
3:-ቤተክርስቲያን ናቸው

ከውሰኔ በፊት ሊታሰቡ የሚገቡ ጉዳዮች

1:-ፈቃደ እግዚአብሔርን መጠየቅ
2:-የውሳኒያችን መልካም እድሎችና ስጋቶችን ማየት
3:-አስቀድመን መረጃ መሰብሰብ
4:-ንባቡ እና እውቀቱ ካላቸው ማመካከር
5:-የውሳኔ አማራጮችን ጊዜ ሰጥቶ ማየት
6:-ውሳኔያችንን ከላይ ከጠቀስናቸው ነገሮች አለማፈንገጡን ማረጋገጥ።

ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል ሙሉ ትምህርቱን በባህራን YouTube ላይ ይጠብቁ።

ባሕራን ሚድያ
4/13/2014
640 viewsMoges abreham, edited  12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 14:03:34 ስልጠና 2 በባሕራን ቲዩብ ሊንኩን በመክፈት ይከታተሉ ለሌሎችም ያጋሩ

የወጣቶች የክረምት ስልጠና ኦርቶዶክሳዊ ግብረ ገብነት 2014 ባሕራን ሚዲያ BAHRAN MEDIA
517 viewsbereket, edited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 15:16:26
የጸሎት መርሃ ግብር ጥሪ ከነሃሴ 1 እስከ ነሃሴ 16 የሚቆይ የጸሎት መርሃ ግብር ስለሚኖር የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና የአጥቢያው ወጣቶች ምሽት የሰርክ ጉባኤ እንዳለቀ በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ በመገኘት እንድትሳተፉ እንጠይቃለን
750 viewsbereket, 12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 10:07:16
አምስተኛው ዙር ስልጠና ነገ ማክሰኞ ከ12:00 ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ የውሳኔ አሰጣጥ በሚል ርዕስ በመምህር ታደሰ ወርቁ ይሰጣል።
658 viewsMoges abreham, edited  07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 23:31:18 ኦርቶዶክሳዊ ንግግር ክህሎት

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ የንግግር ክህሎት" በሚል ርእስ በዲያቆን አቤል ካሳሁን ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውው ትልቅ ስጦታ መናገርን ነው። እግዚአብሔርን ከምንመስልበት መንገድ አንዱ በነባቢነት ነው። ይህም እንዲታወቅ እግዚአብሔር እራሱ እንደሚናገር መጸሐፍ ይነግረናል።ቅዱ እግዚአብሔር አብዛኛውን ፍጥረት ሲፈጥር በመናገር ጨምር ነው። ተናግሮ ፈጥሯል እንዲሁም ተናግሮ ስም ሰጥቷል። አዳም በእግዚአብሔር መልክ ስለተፈጠረ እግዚአብሔር ስም እንዳወጣ አዳምም ለእንስሳት ስም አውጥቷል ይህ ቀላል ንግግር የተደረገበት አይደለም ለሁሉም እንስሳት ስም ሲያወጣ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። አዳም የመጀመርያ ሥራውም መናገር ነበር። የሰው ልጅ የማሰብ አድማሱ የሚታወቀው በሚጠቀምበት የቃል አንጻር ነው። የሰውን ልጅ መጀመርያ የምናቀው በመናገር ነው።

የንግግር ክህሎት ማለት ግልጽ በሆነ መንገድ ሀሳብን ማስተላለፍ ነው። ይህን ያሰተማረንም እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር በራሱ መለኮታዊ ቃል አልተነገረም ሰዎች በሚገባቸው መልኩ ነውእንጂ። ስለዚህ ቃልን ማወሳሰብ በራሱ የንግግር ክህሎትን ያዳክማል። እግዚአብሔር የኛን ድካም ጎን ተመልክቶ በኛ የቃል ልክ ነው የተገለጠው።

ንግግር በጣም ኃይል አለው። በምድር ላይ ኃይል ያለው ድምጽ የሰው ነው። ሰው በንግግሩ ሊገድል ይችላል። ሰው በሹክሹክታ በሚያወጣው ቃል ሰውን ይጎዳል።ብዙ ጊዜ ሀሳብ ላይ እንጂ የንግግር ሂደታችን ላይ ትኩረት አናደርግም። ለስላሳ የሆኑ ሀሳቦች ሆነው ነገር ግን ጠንከር ባሉ ቃላቶች ሲገለጽ ፍጻሜው የከፋ ነው።

ይህ የንግግር ክህሎት በቀድሞው ዘመን የሳይንስ ቁንጮ ነበር። በግሪኩ ሪቶሪክ ይባላል አርትኦት ልሳን በማለት የሚፈቱት አሉ። ሪቶሪክ የሚለውን ቃል በኛ ቋንቋ ስንተረጉመው ጥራትን እና ውጤታማነትን የተከተለ ንግግር ማለት ነው። ሪቶሪክ ንግግርን ብቻ ሳይሆን ጽሑፍንም ያካትታል ዮሐንስ ጠምቆ ዮሐንስ ጠጣው ይባላል ይሄ ማለት ይሄ ራሳችን ተናግረን ራሳችን ብቻ የሚገባን አድማጩን ያልተከተለ ንግግር ማለት ነው። የንግግር ክህሎት የምንለው ግን ቀጥተኛና በማያሻሙ ቃላቶች የታሸ ንግግር ማለት ነው።

ይህ የንግግር ክህሎት ቅድመ ልደት ክርስቶስ ከአምስተኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ሲሰጥ የነበረ ሲሆን የጀመሩትም የሱፊዝምን ፍልስፍና የሚከተሉ ሰዎች ነበር። ዓላማውም ሕዝብ ላይ ተጽእኖ ማሳደር እና ፍልስፍናቸውን ተደራሽ ለማድረግ ነው። እውነት ግላዊ ነው ኅብረታዊ ነው? መልሱ የግል እውነት የሚባል የለም ነገር ግን በዘመኑ ግለሰባዊ እውነታዎችን የሚያስፋፉበት መንገድ አንዱ የንግግር ክህሎትን በማሰልጠን ነበር። በዛንጊዜ ብዙሀን የተሰማሙበትን ነገር እንደትክክል አድርጎ መቀበል ስለሚታስብ በእጅጉ ተጠቅመውበታል።

የሶፊዝም ፍልስፍና ሲያስተምር የነበረው የንግግር ክህሎት ችግር እየፈጠረ መጣ። ይህም ወጣቶች ከሕግ እንዲወጡ እና እኩይ ምግባሮችን ጭምር የህይወት ዘዴ አድርገው በተማሩት ንግግር ክህሎት መከራከር ጀመሩ። ፕሎቶም ይሄን በመቃወም የመጀመርያው ሰው ነበር። ይህ ሰው የንግግር ክህሎት አንድን ሰው ጠቢብ ያስመስለዋል ነገር ግን ጥሩና ጥበበኛ ግን አያደርግውም። ይላል። በተጨማሪም ሰው መከተል ያለበት ሪቶሪክን ሳይሆን ፍልስፍናን ነው መማር ያለብት። ንግግር ክህሎት ብቻውን ስኳር ነው ስኳር ሲበላ ይጣፍጣል ከዛን ግን ጥቅም የለውም። እንደዚህ ሁሉ የንግግር ክህሎት እውቀት ከሌለው ሲገባ ቢጣፍጥም ጥቅም ግን የለውም።

ሲሴሮ እንዳለው የንግግር ክህሎት ጥቅሙ መሆን ያለበት ለትምህርት እና የስነ ምግባር ትምህርቶችን ማስተላለፍያ ነው።

ክርስትና ለጋ በነበረበት ጊዜ ትልልቅ የቤተክርስቲያን አባቶች የንግግር ክህሎትን ተምረዋል። የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ተምረዋል ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ አንዱ ነው። በተጨማሪም ቅዱስ አርሳንዮስ በዝምታ የሚታወቅ አባት ነው ነገር ግን የንግግር ክህሎት ሊቅ እንደነበር ታሪኩ ይነግረናል። ይህ ጥበብ ከአህዛብ የመጣ በመሆኑ በቤተክርስቲያን መአቀብ ተጥሎት ነበር። በኋላ ግን አስፈላጊ በመሆኑ ሆሚሊቲክሰ በሚል ቀይረውት አንዱ የንግግር ክህሎት እንዲሰጥ ሆነ። ሆሚሌቲክስ ማለት ስብከትን የሚወክል ነው።ወጥቶ ከመስበኩ በፊት ይህን ኮርስ መውሰድ ይጠበቅበት ነበር። ምእመናን የሚይዝ መልካም እና ያማረ ስብከት በዘመኑ በብዙ ተሰጥቷል። የዚህም ምንጭ የንግግር ክህሎት አስተዋጽኦ አንዱ ነው።

የድሩ ሊቃውንት ይህን ትምህርት ስላወቁ ጽሑፉቸውም ትምህርታቸውም የታወቀ ና የተወደደ ነው።

ንግግራችን ተደማጭ እንዳይሆን ከሚያደርጉ ነገሮች

1:-ሐሜትን መደጋገም
2:-ፈራጅ ብቻ መሆን
3:-አማራሪ መሆን ነው
4:-ሁሌ አጥፊ ሁሌ ይቅርታ ጠያቄ መሆን።
5:-ውሸት
6:-የግል አስተያየትና እውነታን መቀላለቀል

ንግግራችን ገልበት እንዲኖረው የሚያደርጉ ነገሮች

1:-ታምኝነት
2:-አለማወሳሰብ
3:-ራስን መሆን
4:-ከቅንነት እና ከፍቅር መነሳት

አርትኦተ ልሳን አምስት ክፍሎች አሉት
(ሦስቱን እንመልከት)

1:-የዝግጅት ክፍል ነው:-ይህም 3 ክፍል አለው

1.1 ኢቶስ የግሪክ ቃል ነው ሀሳቡ የሚሰማህን ሰው እምነቱን መጣል አለበት ምክንያት ማቅረብ አለበት ለምን እንደሚሰሙህ አስቀድመህ ማሰብ።
1.2 ሎጎስ:-ከሎጂክ ጋር የሚገናኝ ነው በአመክንዮ የመሞገት ጉዳይ።
1.3 ፓቶስ የሚሰሙህ ሰዎች ምን አይነት ስሜት እንደዲሰማቸው ነው ምትፈልገው። ውጤት ላይ ማተኮር

2:-መሰደር አሬንጅምነት:-ርእሰ ጉዳይን ማስተዋወቅ፤የሀሳቡን ጭብጥ ማስረዳት፤ለተቃርኖ የሚሆን መልስ መዘጋጀት እንዲሁም ማጠቅለያ መስጠት።

3:-ማስታወስ ማቅረብ የመጨረሻው ደረጃ ነው።

ባሕራን ሚድያ
650 viewsMoges abreham, edited  20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:06:32
777 viewsbereket, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 21:51:37
አራተኛው የሥልጠና መርኃግብር የፊታችን እሁድ ከረፋዱ 4:30 ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ የንግግር ክህሎት በሚል ርእስ በዲያቆን አቤል ካሳሁን ይሰጣል።
836 viewsMoges abreham, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 22:33:16 እንጄ ተቀምጠውባታል አለ፡፡ ውጪ አላት ሴቲቷንም ስለምን እንዲህ አደረግሽ አላት እሳቸው ቢያመጡኝ ነው እኔ ምን ላድርግ አለች በኋላም ታላቁ አባት አባ መቃርስ መነኩሴውን መክረው ገስጸው ወደ በዓታቸው ሲሔዱ ዕጽዋት ድንጋዩ ‹‹መቃርዮስ ስነ አምላክ በዲበ ምድር›› እያሉ መስክረውለታል፡፡ አባቶች የበደለን እንኳን አይፈርዱበትም መክረው ይመለሱታል እንጂ።

አባቶች ሦስት ነገር ይደንቃቸዋል። 1:-የበቁትን በገነት አለማግኘት።2:-ኃጢአተኞችን በገነት መገኘታቸው።3:-ራሳቸውን ገነት ማግኘታቸው። አንድ አንድ ጊዜ የፈረድንባቸው ነገር ግን ጽድቃቸውን ያላውቅናለቸው ሰዎች አሉ።

፭:-አለመግባባትን እንዴት እንፈታለን

በሐዋርያትም ጭምር አለመግባባት እንደነበር መጸሐፍ ይነግረናል “ደግሞም ማናቸውም ታላቅ ሆኖ እንዲቈጠር በመካከላቸው ክርክር ሆነ።”— ሉቃስ 22፥24

አለመግባባትን ለመፍታት የሚረዳ አንድ የመጸሐፍ ቅዱስ ክፍል አለ ይህም ከአህዛብና ከአይሁድ በመጡ ክርስቲያኖች በተፈጠረው አለመግባባት ሐዋርያት የሄዱበትን ሂደት የሚያሳይ ነው።

" አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ። ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፥ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት ሽማግሌዎችም ተቀበሉአቸው፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ አወሩ።ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው፦ ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል አሉ።ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ። ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ።ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ? ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን። ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፥ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር።እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ። እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል። ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ። ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው። ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት። ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።"

በዚህ ዘለግ ያለ ታሪክ ውስጥ ደቀመዛሙርቱ አለመግባባትን የፈቱበት መንገድ ለሁሉም ሰው ታላቅ ትምህርት ነው። ከዚህ ታሪክ ውስጥም አራት ነገር ማይት እንችላለን።

1:-እራስን ለውይይት ማዘጋጀት ሐዋርያት የተፈጠረውን አለመግባባት በመሰሙ ጊዜ ችላ ብለው አላለፉትም ለውይይት ቀን ቆጠሩ። ይህ አለመግባባትን መፍታት የሚቻለው በመምከርና በመወያየት መሆኑን ያስተምራል።

2:-ቃለ እግዚአብሔርን በመናገር መጀመር በዚህ በሐዋርያት ጉባኤ ሊይ ቀጥታ ሬእሰ ጉዳዩ አልተነሳም ቅዱስ ጴጥሮስ የሚያጽናኑ መልካም ትምህርትን አስተማር። ጴጥሮስ መናገር ከጀመረና ከተናገረ በኋላ በጉባኤው ጸጥታ ሰፍኖ ነበር ሁሉም ወደ ሰከነ ማንነት ተመልሰዋል ከዛን ቀጥሎ ጳውሎስና በርናባስም ያለዌን ነገር ሁሉ ለጉባኤው አስረዱ። አለመግባባት መካከል ላይ ቃለ እግዚአብሔርርን መስማት ብዙ ነገርን ያቀላል።

3:-ለሀሳቦች እድል መስጠት ደቀ መዛሙርቱ የኛ ውሳኔ ይህ ነው ብለው ከማሳወቃቸው በፊት ከሁሉም አቅጣጫ የመጣውን ሐሳብ አሴተናግደዋል። ይህም አለመግባባትን ለመቅረፍ ሀሳቦችን መስተናገደን እንደሚገባ ያሳየናል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ባሕራን ሚድያ
974 viewsMoges abreham, 19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 22:33:14 ++ኦርቶዶክሳዊ ስነ ተግባቦት++

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ ሥነ ተግባቦት" በሚል ርእስ በዶክተር ዲያቆን ዳዊት ከበደ ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

፩:-የስልጠናው አስፈላጊነት

1.1 በሰንበት ተምህርት ቤት አገልግሎት ትልቁ ችግር የተግባቦት ክህሎት አናሰ መሆን ነው። ተግባቦት ክህሎት ከቤተክርስቱያን ውጪ በቤተሰብ በሥራ በትዳር ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነው። ወደ ቤተክርስቲያን ስንመለስ ደግሞ የዳበረ የተግባቦት ክህሎት ወሳኝ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።

1.2 ለመዳንም አስፈላጊ ነው ክርስትና በቃልም በህይወትም ይሰበካል። ስለዚህ ሌሎችንም ለማዳን የሚያስብ ሰው ጥሩ የሆነ የስነ ተግባቦት ክህሎት ሊኖረው ይገባል። "ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ሰው ድኗል ብዬ አላምንም" እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።

1.3 ስብከተ ወንጌልን ለማስፉፉት እና ቃለ እግዚአብሔር ተደራሽለማድረግም ያስፈልጋል። በህይወታችን ውጤታማ ደስተኛ ለመሆን እጅግ አስፈላጊው ነገር መልካም ተግባቦት ነው። በእኛ መጥፎ ንግግር ብዙዎች የጠፉ ያዘኑ አሉ።።

፪:-ትርጉም

2.1 ተግባቦት መልካም ግንኙነት የመግባባት ክህሎት የንግግር ክህሎት በማለት ይፈታል። ሰው በአካላዊ እንቅስቃሴ በሶሻል ሚድያ እና በመሰል ጉዳዮች ተግባቦት ይፈጥራል።ከእነዚህ ውስጥም አንዱ የንግግር ክህሎት ነው። ለተግባቦት መሠረታዊ ነገርም የንግግር ክህሎት ነው። የቀደሙ አባቶችም ለዚህ ነገር ትኩረት ሰጥተው ሰርተዋል። በተለይ በዘመነ ሊቃውነት አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነው።

2.2 እግዚአብሔር ንግግር ላይ ጥሩ የሆኑትን ለስራው ይጠቀምባቸዋል ለዚህም በሙሴ ታሪክ የተገለጸው አሮን ምሳሊያችን ነው።
"ሙሴም እግዚአብሔርን፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ አፌ ኰልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም። እግዚአብሔርም፦ የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?"......“የእግዚአብሔርም ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ደህና እንዲናገር አውቃለሁ፤ እነሆም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ባየህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለዋል።”ዘጸ 4:10

ይህ የሚያሳየን ለሰው ልጆች ለመዳን የሚናገር ሰው እንደሚያስፈልግ ስለተረዳ አሮንን መድቦላቸዋል ስለዚህ የተግባቦት አንዱ ክህሎት ንግግር ነው። ክርስቶስመ በቃሉ በንግግሩ ብዙዎችን አስተምሮ መልሷል።

፫:-የውጤታማ መግባባት ክህሎት

3.1 ማዳመጥ:-

ቦዙዎቻችን ለመናገር እናጂ ሰዎችን ለመረዳት ለማዳመጥ የተዘጋጀን አይደለንም። ተፈጥሮ እንኳን ብዙ እንደንሰማ ነው ሚያስገድደን። አለመስማት አይቻለም አመናገር ግን ይቻላል። “ሳሙኤልም፦ በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።" — 1ኛ ሳሙኤል 15፥22

3.2 አለማቋረጥ

ሰውን በትክክል እስኪጨርስ ድረስ አለመጠበቅ መልስ ለመስጠት አለመቸኮል አንዱ የተግባቦት ክህሎት አለ። "ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለው በመናገሬም አዝናለው በዝምታዬ ግን የዘንኩበት ጊዜ የለም።" አባ አርሳንዮስ

3.3 ጤናማና የማይነቀፍ ንግግሮች መናገር

“የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ።”— ቲቶ 2፥7-8

" በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤"1ጴጥ3:5

“ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል።”— ምሳሌ 15፥4

"ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው። እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።"ያዕ3:1-6

፬:-የመግባባት ክፍተቶች

4.1 ቁጣ

ቁጣ ከዝሙት ጋር ይነጻጸራል። ቁጡ ሰው የዝሙት ጾር ቢነሳበት መመከት አይቻለውም ይባላል።እኔ እናገራለው እንጂ ውስጤ ባዶ ነው የሚል አለ የሰው ልብ ካሳዘንን ከበደልን በኋል ይህን ማለት የሚረባ አይደለም።አንድ አባት እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኋሉ ንጹህ ነው። በማለት ተናግረዋል።

“መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።”
— ኤፌሶን 4፥31

ባስልዮስ ስለ ሰው ልጆ ባሕርይ በጻፈበት ድርሰቱ ላይ እንዲህ ይላል ሰው የእግዚአብሔርን መልክ እንዴት ይመስላል.......የሰውም ልጅ የሰማይ አእዋፍትን ይግዛ ይላል መመስሎ በገዢነት ነው። የሰው ልጅ አራዊትን እንዴት ነው ሚገዛው የሰው ልጅ በምክንያታዊና በብልሀትነቱ ይገዛል። አራዊቶችን ስላልገዛ አይጠየቅም ነበውስጡ ያሉን ክፉ አውሬዎችን ቁጣንና ንዴትን መግዛት አለበት።"

አንድ የራሽያ አባት ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ስንናደድ ለምን እንጮሀለን ብለው ጠየቋቸው። ራሳችችንን መቆጣጠር ስለማንችል አሏቸው። እሳቸው ግን በተቃራኒው ስንናደድ የምንጮህው በልባችን መካከል ያለው ርቅት ስለሚጨምር ነው። ሰዎች ሲዋደዱ ደግሞ ዝቅ ብለው በሹክሹክታ ያወራሉ በጣም ሲግባቡ ደግም በዓይን ይግባባሉ። ብለዋቸዋል

4.2 ወቀሳ እና መፍረድ

“ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።”— 1ኛ ቆሮንቶስ 4፥5

“አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም፤ አትኰንኑ አትኰነኑምም። ይቅር በሉ ይቅርም ትባላላችሁ።” — ሉቃስ 6፥37 ሰውን ለመውቀስ ማስተማር ይቀድማል።

አባ መቃርስ በአበ ምኔትነት በሚያገለግልበት ገዳም አንድ ታውሚጦስ የሚባል መነኮሴ ይኖር ነበር፡፡ በገዳሙ የነበሩት መነኮሳትም አባ ታውሚጦስን ለመክሰስ አባ መቃርስ ፊት በመቆም ይህ ታውሚጦስ የተባለ ሰው እየወጣ ይውላል ከሴት ይገናኛል አሉት፡፡ አባ መቃርስም ልጄ ንጹህ ነው ያለበደሉ አትውቀሱት ብሎ መለሰላቸው፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ታውሚጦስ በድብቅ ሴት ይዞ ሲገባ የተመለከቱ መነኮሳት ወደ አባ መቃርስ በመሔድ ይህው እንዳልነው እንደቀድሞ ግብሩ ሴት ይዞ ገባ በማለት አባ መቃርስን አስከትለው ወደ አባ ታውሚጦስ በዓት ሔዱ፡፡ አባ ታውሚጦስም እንደመጡ ባወቀ ጊዜ ሴቲቷን ከቅርጫ ስር ደበቃት በዓቱንም ከፍቶ መነኩሳትንም ሁሉ ወደ በዓቱ አስገባቸው፡፡ የአባ ታውሚጦስን ስህተት የተረዱት አባ መቃርስም ሴቲቷ የተደበቀችበት ቅርጫት ላይ ከተቀመጥ በኋላ በሉ እንግዲ ያላቹት ሁሉ ውሸት ነው ያልተገባ ፍርድ ነው የፈረዳችሁት ብሎ መነኩሳቱን አሰናበታቸው፡፡መነኮሳቱም ከወጡ በኋላ አባ መቃርስ ከአባ ታውሚጦስ ጋር ጨዋታ ይጀምራል ሰላምታ ከተለዋወጡና ጥቂት ከተነጋገሩ በኋላ የገዳሙ አበ ምኔት አባ መቃርስ እግዚአሔር ሳይፈርድብህ እራስሀ ላይ ፍረድ ብለው ቢነግሩት እኔስ ፈርቼ ነው
662 viewsMoges abreham, edited  19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 11:32:54
ሦስተኛ ዙር ስልጠና ማክሰኞ ሐምሌ 26 ከ12:00 ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ አስተዳደር በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ይሰጣል።
622 viewsMoges abreham, edited  08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ