Get Mystery Box with random crypto!

'ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት እና ውሳኔ አሰጣጥ' (በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ | ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

"ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት እና ውሳኔ አሰጣጥ"

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት እና ውሳኔ አሰጣጥ" በሚል ርእስ በመምህር ታደሰ ወርቁ ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

በመጀመርያ ደረጃ ኦርቶዶክሳዊነት ስንል ምን ማለት እንደሆነ ማስተዋል ተገቢ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ስንል አምስት ነገሮችን የሚገልጥ ነው

1:-መጸሐፋዊነት:-
ሥርዓቷን ትምህርቷ ከመጸሐፍት የመነጨ ነው።

2:-ትውፊታዊነት
ከሌሎች ቤተ እምነቶች የሚለያት ቅብብሎሽ ወይም ትውፊታዊ መንገዶችን የምትቀበል በመሆኗ ነው።

3:-ቀኖናዊነት
መጸሐፍት እና ትውፊቶች መሠረተ እምነትን ጨምሮ ጸንተው የቆሙት በቀኖና ነው።

4:ዶግማዊ
ዶግማ የማይቀየር የማይሻሻል ማለት ነው ኦርቶዶክሳዊነትም ስንል በሰው መሻት የማይቀየር መሠረተ እምነት ያላት ማለት ነው።

5:-መዋቅራዊነት
ከላይ ያሉትን ጨምሮ የሚይዝ ደግሞ መዋቅር ነው። ይህም ከክርስቶስ የጀመረ ሐዋርያት ሐዋሬያነ አበው ሊቃውንት እያለ ከእኛ የደረሰ ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት

ስለ ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት ስንናገር በእነዚህ መአቀፍ ውስጥ መሆን አለበት። ውሳኒያችን መጸሐፋዊ ትውፊታዊ ቀኖናዊ ዶግማዊ መዋቅራዊ የሆነ ወይም ያማከለ መሆን አለበት ማለት ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነት ስንል ምን ማለታችን ነው?

፩:-ጥንተ ተፈጥሮን መጠበቅ:-

የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረ ነው በዚህም ምክንያት የገዢነት ስልጣን ተሰጥቶታል። ከዓራቱ ባሕርያተ ሥጋ እንደመገኘቱ
ዓለመ ሥጋን ገንዘብ አድርጓል ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ እንደመገኘቱ ዓለመ ነፍስን ገንዘብ አድርጓል የሰው ጥንተ ተፈጥሮ ይሄ ነው። አዳም ፍጡር መሆኑ እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑ እንዲታወቅ ዕጸ በለስን አትብላ ተባለ ይህም የፍቅር ህግ ነበር። አዳም ግን የተሰጠውን ሕግ ጣሰ የባሕርይ ጉስቁሉናና የጸጋ መጋፈፍም አገኘውም። ኃላፊነቱን አልተወጣም። ጥንተ ተፈጥሮን መጠበቅ ሰው የመሆን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት መሠረት ነው። አዳምን በኤደን ገነት አኖረው እንዲጠብቃትም አዘዘው። ገነት ያማረች ሳለች ለምን ተንከባከባት አለው? ይሀሰ የሚያሳየን በአንጻረ አዳም ለሰው ልጅ ኃላፊነትን ሲሰጥ
ነው።

፪:- ሌላው ኃላፊነት ማለት የሥላሴ ልጅነትን ጸጋ ማጽናት ነው። በአርባ በሰምንያ የተጠመቀ የሥላሴን ልጅነት ያገኘ ሁሉም ድርሻ አለው ይህንን ጅርሻ መወጣት ነው ኃላፊነት። በሚታይ አገልግልግሎት የማይታይ ጸጋ የሚገኝበት ምሥጢር የሚፈጸምባት ናት።

3 ኃላፊነት ጥሪን ማክበር ነው። የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ደግሞ ጥቂቶች ናቸው እንደተባለው። ይህ ማለት ግን ከብዙዎች መካከል ጥቂቶችን መረጠ ማለት አይደለም። ጥሪውን አድምጠው የመጡትን ሳይሆን ጥሪውን አክብረው የጸኑትን ለመግለጽ ነው። ጥሪው የንሰሐ የአገልግሎት ሊሆን ይችላል ይህንን ጥሪ ማክበር ሲባል ኦርቶዶክሳዊ ኃላፊነትን መውጣት ነው።

ኦርቶዶክሳዊ ውሳኔ አሰጣጥ

የውሳኔ መአከላት ውሳኔ ስንወስን ከሦስቱ ጉዳዮች ውጪ አንሆንም እነሱም:-
1:-ሰው
2:-ሀገረ
3:-ቤተክርስቲያን ናቸው

ከውሰኔ በፊት ሊታሰቡ የሚገቡ ጉዳዮች

1:-ፈቃደ እግዚአብሔርን መጠየቅ
2:-የውሳኒያችን መልካም እድሎችና ስጋቶችን ማየት
3:-አስቀድመን መረጃ መሰብሰብ
4:-ንባቡ እና እውቀቱ ካላቸው ማመካከር
5:-የውሳኔ አማራጮችን ጊዜ ሰጥቶ ማየት
6:-ውሳኔያችንን ከላይ ከጠቀስናቸው ነገሮች አለማፈንገጡን ማረጋገጥ።

ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል ሙሉ ትምህርቱን በባህራን YouTube ላይ ይጠብቁ።

ባሕራን ሚድያ
4/13/2014