Get Mystery Box with random crypto!

ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ africauniondebremihret — ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ africauniondebremihret — ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @africauniondebremihret
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

ባህራን ሚዲያ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የአገልግሎት እንቅስቃሴ፣ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እንዲሁም ማስታወቂያዎችን የምንለቅበት ይፋዊ የቴሌግራም ገጻችን ነው።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 20:58:20
187 viewsMoges abreham, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:15:05
ለኦርቶዶክሳውያን የተዘጋጀው ልዩ የክረምት ትምህርታዊ ስልጠና እነሆ ዘጠነኛ ክፍል ደርሷል ማክሰኞ ነሐሴ 17 በመምህር ሄኖክ ኃይሌ ቤተክርስቲያን ነገ በሚል ርእስ ትምህርቱ ይቀጥላል። መማር ይቅደም።

ያለፉትን ሥልጠናዎች ለማግኘት በባሕራን ሚዲያ የዩቱዩብ ገጽ subscribe በማድረግ ይከታተሉ የምንለቃቸው ትምሕርቶች እንዲደርሶ የደወል ምልክቱን ይጯኑ ለሌሎችም ያጋሩ ።
https://youtube.com/channel/UCfs9sQ51kB6zs4hgWZueEFQ
539 viewsMoges abreham, edited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:41:25

572 viewsbereket, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 16:22:21 ደብረ ታቦር በደብረ ምሕረት 2014

539 viewsbereket, 13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:05:54
ነገ እሁድ በ15 ለኦርቶዶክሳውያን የተዘጋጀው ልዩ የክረምት ትምህርታዊ ስልጠና እነሆ ስምንተኛ ክፍል ደርሷል የፊታችን እሁድ በመምህር ቢትወደድ ወርቁ ኦርቶዶክሳዊ ግጭት አፈታት በሚል ርእስ ትምህርቱ ይቀጥላል። መማር ይቅደም።
ያለፉትን ሥልጠናዎች ለማግኘት በባሕራን ሚዲያ የዩቱዩብ ገጽ subscribe በማድረግ ይከታተሉ የምንለቃቸው ትምሕርቶች እንዲደርሶ የደወል ምልክቱን ይጯኑ ለሌሎችም ያጋሩ ።
https://youtube.com/channel/UCfs9sQ51kB6zs4hgWZueEFQ
576 viewsbereket, edited  08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 11:26:22 ++ኦርቶዶክሳዊ የጊዜ አጠቃቀም++

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ የጊዜ አጠቃቀም" በሚል ርእስ በዲያቆን ዘላለም ታዬ ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” ዘፍጥረት 1፥1

ዓለም ራሱ ስልጡን የምትላቸው ጊዝያቸውን በአግባቡ የተጠቀሙትን ነው።ለሰው ልጅ የተሰጠው ትልቁ ሀብት ጊዜ ነው።

ጊዜ ሁለት አይነት ሲሆን አንደኛው የሚያልፍ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣቸው ቀመር መለኪያ ፍጡራን የሆኖ የሚመሩበት ቋሚ ያልሆን አላፊ የሆነ ማለት ነው። ሁለተኛው የማያልፍ የምንለው ነው ይህም ዘላለማዊ የሚለው ይገልጸዋል ይህ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚሰራ ነው።

እግዚአብሔር ከሁሉ አስቀድሞ የፈጠረው ጊዜን ነው። በኦሪት ዘፍጥረት መጀመርያ የሚለው ጊዜን የሚወክል ነው። ጊዜን በአግባቡ ያልተረዳ ሰው ደካማ መላምት ውስጥ ይገባል። የጊዜ አጠቃቀም ያስተማረነ እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ልብ በሉ። አላፊ ጊዝያችሁን ለዘላለማዊነት ለውጡት በማለት እመቤታችን ተናግራለች። ስለዚህ ጊዜ አላፊ መሆኑን የተፈጠረ መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል። በሚያልፈው ጊዜ የማያልፈውን ዘላለማዊነትን መያዝ ያስፈልጋል

ጊዜ ለእኛ ስጦታ ነው ጌታችን ዳግም ስለመምጣቱ ያስተማራቸው ሦስት ምሳሌዎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዱም ለባርያዎቹ መክሊት ስለሰጣቸው ሰዎች ያወራል። ይህንን ትምህርት ክርስቶስ ስለ ጊዜ አስተምሮበታል። 5 መክሊት ረጅም ዓመት ያለው ሰው ሁለት የተባለው መአከላዊ አንድ የተሰጠው አነስተኛ እድሜ ያለው ነው። መክሊት ስጦታ ማለት ነው። በዚህ ስጦታ ዘላለማዊነትን መያዝ ነው። ማቴ 25:15

ጊዜን መጠቀም እና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ማለት ይለያያል። ጊዜን መጠቀም የሚለው በ24 ሰዓት ውስጥ ሁሉን መሥራት የሚል ሲሆን ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ማለት ደግሞ የምንቀንሳቸው ሥራዎች አሉ ለማለት ነው ማለት ትኩረት የሚደረግባቸው ላይ ብቻ መሥራት። ሐዋርያው ጳውሎስ ቀን ቀን ያስተምራል ለሊቱን ደግሞ ድንኳን ይሰፋ ነበር። ይህ ለወንጌልም ለሥጋም ለሚሠጥ ጊዜ ምሳሌ ነው።

እቃዳችን ማይሳኩት ለምንድን ነው?

1:-ላቀደው እቅድ ትኩረት መስጠት አለመቻል።
2:-የሰማነው ነገር ሁሉ ይሆናል ብሎ ማመን።

እቅዳችን በጊዜ መሠረት እንዲሳካ ምን እናድርግ

1:-አምላክ ለእኛ ካለው እቅድ ጋር ዓላማን መንደፍ።“ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤”— 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥26። ጊዜ እንደ ነፋስ ነው። የትኛውም እቅዳችን ከአምላክ እቅድ ጋር መነጻጸር አለበት። የኛ ምድራዊ እቅድ የሚከተለው ከእግዚአብሔር እቅድ በኋላ ነው።

2:-እቅድና ቅድመ ተከተል ይኑርህ። ማቀድ ብቻ ሳይሆን ጥቅሙ የጊዜን ቅድመ ተከተል ማዘጋጀት ነው። በቋሚነት በግዴት ልንፈጽማቸው የሚገቡ ዕቅዶች አሉ።እነዚህን በቀድመ ተከተል መደልደል ያስፈልጋል።

3:-እቅዶችህን ከታቀደልህ ጋር ማስማማት። እቅዳችንን ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር ማስማማት ያስፈልጋል። መዝ 33:11። የእግዚአብሔር ሀሳብ እና ምክር የእኛን ሀሳብ ያቀናልናል።

ጊዜ እንድንሰጣቸው የምንገደድባቸው 5 ነገሮች

1:-ለቤተሰብ ጊዜ መስጠት
2:-ለቤተክርስቲያን ጊዜ መስጠት
3:-ለሥራ ጊዜ መስጠት
4:-ለአካባቢው ሮሜ 14:7
5:-ለራሳቸው ሉቃ 2:25

ባሕራን ሚድያ
636 viewsMoges abreham, edited  08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:08:31
ሰባተኛው ዙር ትምህርታዊ ስልጠና ነገ ማክሰኞ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ እንዴት እንፍጠር በሚል ርእስ በመምህር ፍሬሰንበት የሚሰጥ ይሆናል። ማስታወቅያው ለሁሉም እንዲዳረስ ያጋሩት።
572 viewsMoges abreham, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 18:15:11 የነገው ትምህርታዊ ስልጠና የተጠበቀ ነው። በጊዜው በመገኘት የበኩላችንን እንወጣ በተጨማሪ እስከ አሁን አራት ትምህርቶች በባህራን you tube የተለቀቀ ሲሆን share like subscribe በማድረግ የበኩሎቱን እንዲወጡ እንጠይቃለን።
647 viewsMoges abreham, edited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 13:42:08 ኦርቶዶክሳዊ የወጣቶች ስልጠና ፫ በመመምሕር ታደሰ ወርቁ ሊንኩን በመጠቀም በዩቱዩብ ይማሩ ለሌሎችም ያጋሩ።



686 viewsbereket, edited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 22:24:44
ለኦርቶዶክሳውያን የተዘጋጀው ልዩ የክረምት ትምህርታዊ ስልጠና እነሆ ስድስተኛ ክፍል ደርሷል የፊታችን እሁድ በዲያቆን ዘላለም ታዬ ኦርቶዶክሳዊ የጊዜ አጠቃቀም በሚል ርእስ ትምህርቱ ይቀጥላል። መማር ይቅደም።
755 viewsMoges abreham, edited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ