Get Mystery Box with random crypto!

++ኦርቶዶክሳዊ የጊዜ አጠቃቀም++ (በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ 'ኦርቶ | ባሕራን ሚዲያ አ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ቤት

++ኦርቶዶክሳዊ የጊዜ አጠቃቀም++

(በሰንበት ትምህርት ቤታችን በተዘጋጀው ስልጠና ላይ "ኦርቶዶክሳዊ የጊዜ አጠቃቀም" በሚል ርእስ በዲያቆን ዘላለም ታዬ ከተሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰዱ አስተማሪ ነጥቦች)

“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” ዘፍጥረት 1፥1

ዓለም ራሱ ስልጡን የምትላቸው ጊዝያቸውን በአግባቡ የተጠቀሙትን ነው።ለሰው ልጅ የተሰጠው ትልቁ ሀብት ጊዜ ነው።

ጊዜ ሁለት አይነት ሲሆን አንደኛው የሚያልፍ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣቸው ቀመር መለኪያ ፍጡራን የሆኖ የሚመሩበት ቋሚ ያልሆን አላፊ የሆነ ማለት ነው። ሁለተኛው የማያልፍ የምንለው ነው ይህም ዘላለማዊ የሚለው ይገልጸዋል ይህ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚሰራ ነው።

እግዚአብሔር ከሁሉ አስቀድሞ የፈጠረው ጊዜን ነው። በኦሪት ዘፍጥረት መጀመርያ የሚለው ጊዜን የሚወክል ነው። ጊዜን በአግባቡ ያልተረዳ ሰው ደካማ መላምት ውስጥ ይገባል። የጊዜ አጠቃቀም ያስተማረነ እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ልብ በሉ። አላፊ ጊዝያችሁን ለዘላለማዊነት ለውጡት በማለት እመቤታችን ተናግራለች። ስለዚህ ጊዜ አላፊ መሆኑን የተፈጠረ መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል። በሚያልፈው ጊዜ የማያልፈውን ዘላለማዊነትን መያዝ ያስፈልጋል

ጊዜ ለእኛ ስጦታ ነው ጌታችን ዳግም ስለመምጣቱ ያስተማራቸው ሦስት ምሳሌዎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንዱም ለባርያዎቹ መክሊት ስለሰጣቸው ሰዎች ያወራል። ይህንን ትምህርት ክርስቶስ ስለ ጊዜ አስተምሮበታል። 5 መክሊት ረጅም ዓመት ያለው ሰው ሁለት የተባለው መአከላዊ አንድ የተሰጠው አነስተኛ እድሜ ያለው ነው። መክሊት ስጦታ ማለት ነው። በዚህ ስጦታ ዘላለማዊነትን መያዝ ነው። ማቴ 25:15

ጊዜን መጠቀም እና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ማለት ይለያያል። ጊዜን መጠቀም የሚለው በ24 ሰዓት ውስጥ ሁሉን መሥራት የሚል ሲሆን ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ማለት ደግሞ የምንቀንሳቸው ሥራዎች አሉ ለማለት ነው ማለት ትኩረት የሚደረግባቸው ላይ ብቻ መሥራት። ሐዋርያው ጳውሎስ ቀን ቀን ያስተምራል ለሊቱን ደግሞ ድንኳን ይሰፋ ነበር። ይህ ለወንጌልም ለሥጋም ለሚሠጥ ጊዜ ምሳሌ ነው።

እቃዳችን ማይሳኩት ለምንድን ነው?

1:-ላቀደው እቅድ ትኩረት መስጠት አለመቻል።
2:-የሰማነው ነገር ሁሉ ይሆናል ብሎ ማመን።

እቅዳችን በጊዜ መሠረት እንዲሳካ ምን እናድርግ

1:-አምላክ ለእኛ ካለው እቅድ ጋር ዓላማን መንደፍ።“ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤”— 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥26። ጊዜ እንደ ነፋስ ነው። የትኛውም እቅዳችን ከአምላክ እቅድ ጋር መነጻጸር አለበት። የኛ ምድራዊ እቅድ የሚከተለው ከእግዚአብሔር እቅድ በኋላ ነው።

2:-እቅድና ቅድመ ተከተል ይኑርህ። ማቀድ ብቻ ሳይሆን ጥቅሙ የጊዜን ቅድመ ተከተል ማዘጋጀት ነው። በቋሚነት በግዴት ልንፈጽማቸው የሚገቡ ዕቅዶች አሉ።እነዚህን በቀድመ ተከተል መደልደል ያስፈልጋል።

3:-እቅዶችህን ከታቀደልህ ጋር ማስማማት። እቅዳችንን ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር ማስማማት ያስፈልጋል። መዝ 33:11። የእግዚአብሔር ሀሳብ እና ምክር የእኛን ሀሳብ ያቀናልናል።

ጊዜ እንድንሰጣቸው የምንገደድባቸው 5 ነገሮች

1:-ለቤተሰብ ጊዜ መስጠት
2:-ለቤተክርስቲያን ጊዜ መስጠት
3:-ለሥራ ጊዜ መስጠት
4:-ለአካባቢው ሮሜ 14:7
5:-ለራሳቸው ሉቃ 2:25

ባሕራን ሚድያ