Get Mystery Box with random crypto!

'ብሄር' እና 'ብሄረሰብ' እና ፖለቲካችን --- አፈንዲ ሙተቂ --- ብሄር ( Nation) ብሄ | AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴

"ብሄር" እና "ብሄረሰብ" እና ፖለቲካችን
---
አፈንዲ ሙተቂ
---
ብሄር ( Nation)

ብሄር ማለት ተለይቶ በሚታወቅ የጂኦግራፊ ክልል የሚኖር፣ የራሱ ቋንቋ ያለው፣ ተወላጆቹ በዘር ሀረግ (geneology) የሚገናኙ፣ የተለየ ባህልና ማህበራዊ አወቃቀር ያለው፣ ተወላጆቹ በኢኮኖሚ ስምሪታቸው የሚመሳሰሉ፣ የተወላጆቹ ስነ ልቦናዊ ባህሪ የሚመሳሰል፣ የራሱ መነሻው እና ታሪካዊ ጉዞ ያለው የሰዎች ስብስብ ማለት ነው። አንድ ብሄር በተለያየ ነገድና ጎሳ ሊከፋፈል ይችላል (ኦሮሞ፣ ሶማሊ፣ ዙሉ፣ ሃውሳ ወዘተ)። የጎሳና የነገድ ክፍፍል የሌለውም ሊሆን ይችላል (አማራ፣ ትግራይ፣ ፋርሲ፣ ካታላን)።
--
ብሄረሰብ (Nationality)

ብሄረሰብ በብዛቱ ከብሄር የሚያንስ እና በተለያዩ ክልሎች በሚኖሩት ቡድኖቹ መካከል በቋንቋ እና በባህል ብዙ የመለያየት ባህሪ የማይታይበት የሰዎች ስብስብ ማለት ነው (ለምሳሌ የአንድ ብሄር አባላት ቋንቋቸውን በተለያየ dialect ሊናገሩት ይችላሉ። የሀረር ኦሮምኛ ዘይቤ፣ የወለጋ ኦሮምኛ ዘይቤ፣ የሸዋ ኦሮምኛ ዘይቤ ወዘተ። የአንድ ብሄረሰብ አባላት ግን ቋንቋቸውን በተመሳሳይ dialect ነው የሚናገሩት። ለምሳሌ ሀረሪ፣ ሀላባ፣ ስልጢ)

ሁለቱ የእንግሊዝኛ ቃላትን በትክክለኛ መልኩ የሚገልፁ የአማርኛ ቃላት የሉም። "ብሄር" እና "ብሄረሰብ" በ1966 በፈነዳው አብዮት ማግስት ነው የተፈጠሩት (ልክ እንደ አብዮት፣ ህረተሰብአዊነት፣ ተራማጅ፣ አድሃሪ፣ ወዘተ ማለት ነው)። ሌሎች ቋንቋዎች ግን እነርሱን የሚተኩ ቃላት አሏቸው (ኦሮምኛ፣ አረብኛ፣ ሀረሪ፣ ሶማሊ ወዘተ)።
-----
ይህንን ፍቺ ያገኘሁት ከAmerican Heritage Dictionary ነው።
----
ጎሳ በእንግሊዝኛ Clan ነው የሚባለው። ነገድ ደግሞ tribe ነው የሚባለው።

ደግሞ "ዘውግ" እና "ዘውገኝነት" የሚሉ አባባሎች በቅርቡ ተፈጥረዋል። ይህንን አጠራር ያመጣው አንዳርጋቸው ጽጌ ነው (በ1997 ባሳተመው "ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጪ" በተሰኘ መጽሐፉ)። ይህም የብሄር ፖለቲካን እያጥላላ የአሃዳዊነትን ቅቡልነት ለማስረፅ የዘየደበት መላ ነው።
----
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብሄርና የብሄረሰብ ፖለቲካ ነው እንጂ የጎሳ ፖለቲካ አይደለም። ፖለቲካው በዚህ መንፈስ የተቃኘው በኢትዮጵያ ከባድ የሆነ የብሄር ጭቆና ይካሄድ ስለነበረ ነው። አሁን ያለው ፌዴራሊዝምም የብሄርና ብሄረሰብ ፌዴራሊዝም ነው።

"የብሄር ፖለቲካ እና የብሄር ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ወይስ አያስፈልግም?" ብሎ መከራከር አንድ ነገር ነው። በኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦችን ህልውና እየካደ ወደ ጎሳ ደረጃ ዝቅ ከሚያደርግና "የጎሳ ፖለቲካ ይቁም" ከሚል ሰው ጋር ግን የሚካሄድ ክርክር የለም።