Get Mystery Box with random crypto!

'ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል' በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ያገረሸው ግጭት ተባብሶና ሰፍ | አድስ ዜና

"ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል"

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ያገረሸው ግጭት ተባብሶና ሰፍቶ እየቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት መሳሪያ ወርዶ ወደ ንግግር እንዲገባ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ቀጥለዋል።

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ" ጦርነት ቆሞ የሰላም ሂደቱ ይቀጥል" ሲል የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

ጉኤው ምን አለ?

- ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊቆምና የሰላም ሂደቱ ሊቀጥል ይገባል።

- የሰላም ቅድመ ሁኔታው ሰላም ብቻ በመሆኑ ጦርነቱን በማቆም ሰላማዊ ንግግሮች መቀጠል አለባቸው።

- ከዚህ ቀደም የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤አሁንም የሰላም ጥሪ እናቀርባለን።

- የፌደራሉ መንግሥት ለሰላማዊ ንግግሮች ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ እንደገለጸው ሌሎችም ወገኖች ለዚህ ተግባር ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል።

- የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ንጹኃን ዜጎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል።

- ህፃናትን ለወታደራዊ ዘመቻ ማሰለፍ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅና በሁሉም መመዘኛ ተገቢ ባለመሆኑ ሊቆም ይገባል።

-  በወቅታዊ ጉዳይ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

- ትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች መሪዎች የትግራይ ክልል ወደ ሰላማዊ ድርድሩ እንዲመለስ በመምከር አባታዊና መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን።

- የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡና የውጭ ሀገራት መንግሥታት፣አፍሪካ ሕብረት፣ ተመድና ሌሎች አካላት ሁሉ የሰላም ጥረቱ አጋዥ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።

-  የጳጉሜን 5ቱን ቀናት ምእመናን በፆምና ፀሎት እንዲያሳልፉ ጥሪ እናቀርባለን።

(የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ)