Get Mystery Box with random crypto!

አጫጭር መረጃዎች በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል ባገረሸው አዲስ ውጊያ ከአማራ ክልል ሰሜን ወ | አድስ ዜና

አጫጭር መረጃዎች

በመንግሥት እና በሕወሃት መካከል ባገረሸው አዲስ ውጊያ ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከ30 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የተመድ ዋና ጸሃፊ ቃል አቀባይ ስቲፈን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በአፋር ክልል እና ትግራይ ክልል አዋሳኞች አካባቢዎች በያሎ እና ገሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ስለመፈናቀላቸው ተመድ ሪፖርት እንደደረሰው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። በአፋር እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ጭፍራ ወረዳ ጭምር ነዋሪዎች ስለመፈናቀላቸው ሪፖርት ደርሶኛል ብሏል።

3፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በካርቱም የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮን ጠርቶ ማነጋገሩን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የሱዳን መንግሥት አምባሳደር ይበልጣልን ጠርቶ ያነጋገረው፣ አምባሳደሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሱዳን በኩል ጦር መሳሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ የገባ አንድ አውሮፕላን መትቶ ጥሏል በማለት ሰኞ'ለት በካርቱም ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጋር በተያያዘ  ነው። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ የአምባሳደሩ መግለጫ ከአስተናጋጇ አገር ጋር ቀድሞ በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር የሚጠይቀውን የዲፕሎማቲክ ደንብ የጣሰ ነው ብሏል።

4፤ ትናንት እኩለ ሌሊት በመቀሌ ተፈጸመ የተባለው የአየር ድብደባ የተፈጸመው በአይደር ሆስፒታል አካባቢ ነው ሲል ሮይተርስ የሆስፒታሉን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል። ትናንት ተፈጸመ በተባለው የአየር ድብደባ ምን ጉዳት እንደደረሰ ግን የሮይተርስ ዘገባም ሆነ ሕወሃት አልጠቀሱም። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሕወሃት ውንጀላ ላይ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም። የአየር ድብደባ ተፈጽሟል ሲሉ ሌሊት ላይ በትዊተር ገጻቸው የገለጡት የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ነበሩ።

5፤ ኦፌኮ በሰሜን ኢትዮጵያና ኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሱት ግጭቶች ሊፈቱ የሚችሉት ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጣ እውነተኛና ሁሉን ዓቀፍ ድርድር ብቻ ነው ብሎ እንደሚያምን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በመንግሥት እና ሕወሃት መካከል ጦርነቱ በድጋሚ ማገርሸቱ በጦርነቱ አካባቢ ያሉ ሕዝቦችን ለዳግም ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ እንደሆነ ኦፌኮ ገልጧል። ኦፌኮ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ግጭቱን አብርደው ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ አድርጓል። ኦፌኮ በኦሮሚያ ክልል በግጭትና ድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የሰብዓዊ ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑንም ጠቅሷል።

6፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ4617 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ5109 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 58 ብር ከ7334 ሳንቲም፣ መሸጫው 59 ብር ከ9081 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ52 ብር ከ6401 ሳንቲም ሲገዛ እና በ53 ብር ከ6929 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል።