Get Mystery Box with random crypto!

የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነ | አድስ ዜና

የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አንስተው ነበር።

ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ?

- በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ግጭት መቀጠሉን እና አሁን ላይ ያለድ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ገልፀዋል።

- የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች ማለትም በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለ ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

- በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ ጭፈራ ወረዳ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚገልፅ ሪፖርት መኖሩን አመልክተዋል።

- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከሚገኘው የጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎችም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈናቅለዋል።  

- ዳግም ባገረሸው ግጭት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን ይጨምራል ብለዋል።