Get Mystery Box with random crypto!

የዐዋቂ ምክር ለባለትዳር ጥንዶች… بسم الله الرحمن الرحيم እጅግ በጣም አዛኝና | የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች

የዐዋቂ ምክር ለባለትዳር ጥንዶች…

بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ።

نصيحة عالم للزوجين

قال الإمام العلامة ابن باز رحمه الله تعالى :

الواجب على الرجل أن #لايستعجل في #الطلاق ؛ وأن #يعاشر_بالمعروف وأن يحذر ظلم المرأة وبخسها حقوقها ..

ታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ (ከፍ ያለው አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ አሉ ፦

በአንድ ወንድ ላይ ግዴታ የሚሆነው
ባለቤቱን በመፍታት ላይ አለመቾከሉ ነው።

እንዲሁም በመልካም ሁኔታ ሊኗኗራት
ነው።

ሴቲቱንም ከመደል ሊጠነቀቅ ነው።

(ያላትን) ሐቅም ላያሳንስባት ነው !

والواجب على #الزوجة_التواضع وعدم إغضاب الزوج وعدم إيذائه، وعليها أن تتواضع وأن تستعمل اللطف والرفق والكلام الطيب مع الزوج حتى لا تثير حفيظته فيطلق .

በርሷም (በባለቤቱ) ላይ ግዴታ የሚሆንባት ለባለቤቷ መተናነስ ነው ።

እንዲሁም ባለቤቷን አለማስቆጣትና
አለማስቸገርም ነው።

በርሷ ላይ ያለባት ለሱ መተናነስ ስትኗኗረው በእዝነትና ለስለስ ባለ ሁኔታ ላይ መሆን ነው።

እንዲፈታት በመጠባበቅ ላይ እስከ
ማትመርጥ ድረስ ከባለቤቷ ጋር መልካም
ንግግርን መነጋገር ነው ያለባት !

وعلى الجميع الصبر والاحتساب في جميع الأحوال ..

كما قال سبحانه وتعالى :

« إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ » ( الزمر : ١٠)

فلا بد من الصبر على بعض العوج .. ولا بد للمرأة أن تصبر أيضاً على ما قد يقع من الزوج من بعض الخلل أو بعض التقصير وما أشبه ذلك .

مجموع الفتاوى/٤٧١٣ .

ባጠቃላይ ሁላቸውም ላይ ያለባቸው በሁሉም ሁኔታቸው ላይ ታጋሽ መሆንና
(ከአላህ) ጋር ሒሳባቸውን መተሳሰብ
ነው።

ልክ አላህ እንዳለው ፦

(( " (እነዚያ) ታጋሾች (አላህ ዘንድ)
ያላቸው ምንዳ ከትስስብ ውጪ
ነው። " ))
【አል–ዙመር (10)】

(ለወንድ ልጅ) ከፊሉ ጥመት አለው በተባለው (የሴት ልጅ አፈጣጠር ላይ …) ትዕግስት ማድረጉ ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው !!!

እንዲሁም በሴቲቱ ላይም በድጋሚ ከባለቤቷ በሚገጥማት አንዳንድ ክፍተቶች ፥ ጉድለቶችና የመሳሰሉ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ታጋሽ መሆኗ ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው !!!

(አል–ፈታዋ / 4713)

[ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ
ቢን ባዝ]
https://t.me/Adnan567mh