Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የ55 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች ሐምሌ 12፣ 2014 (አዲስ ዘይ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የ55 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ሐምሌ 12፣ 2014

(አዲስ ዘይቤ፡ አዲስ አበባ) አሜሪካ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ55 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች።

ድጋፉ በዓለም አቀፉ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት በኩል መደረጉም ተገልጿል። የአሜሪካው ዓለምአቀፍ ተራድዖ ድርጅት USAID ተጨማሪው የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያ ወቅታዊውን የምግብ አቅርቦት ችግር ለመቋቋም እና ወደፊት ከምግብ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ አቅም እንደሚገነባላት አስታውቋል።

የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት የገንዘብ ድጋፉን ከሁለት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለምግብ እና ውሃ አቅርቦት ችግር ለተጋለጡ አርሶ እና አርብቶ አደሮችን እንዲሁም ቀሪ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመደገፍ እንደሚያውለው አስታውቋል።

ፈንዱ የተገኘው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በጀርመን በቡድን 7 የመሪዎች ጉባዔ ላይ ቃል በገቡት መሠረት ነው።

ፕሬዚዳንቱ በጉባዔው አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለምግብ ዕጥረት ቀውስ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች 2 ነጥብ 76 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቀው ነበር።
_______
ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የአዲስ ዘይቤ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።
Twitter : https://bit.ly/3uQBnvj
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Telegram : https://bit.ly/3JX93LY
Website : https://bit.ly/3JOUavm
YouTube : https://bit.ly/37rIyBa