2023-04-27 11:40:23
ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁላቹህ ።
#ስንቶቻችን ነን እናቶቻችን እና አባቶቻችን ቀለልባለ መንገድ የተለያዩ እፅዋቶችን ተጠቅመው የተለያዩ የጤናችግሮችን ማከምና ችግሮችን ማስወገድ እንደሚችሉ ምናውቀው ??????
(የቤት ለቤት ሕክምና)
#ከሚጠቀሙባቸው
ባህላዊ መድኃኒቶች በጥቂቱ ፦
#ፌጦ፦ ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል።
#የነጭ_ባህርዛፍ_ቅጠሉ፦ ቅጠሉን በውሃ ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነትን ያለ ኪኒን በሁለት ቀን ውስጥ ፈውስ ያስገኛል።
#ነጭ ሽንኩርት፦ ለደም ዝውውር ፣ ለጨጓራ ፣ ለውስጥ ካንሰር፣ ለመተንፈሻ አካል፣ ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ ይናገራሉ።
#ጤና አዳም፦ ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ ህመም ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ሕመሞች መድኃኒትነቱ ፍቱን ነው ። 40 ገቢር አለው በቅርቡ እለቀዋለሁ ።
#እንስላል፦ በውሃ ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል። ከፍተኛ የኩላሊት ጠጠር ያጠፋል፣ ኩላሊት ያጥባል። የሽንት ስራተኡደትን ያስተካክላል ።
#ሽፈራው: - የዚህ ዛፍ ቅጠል የማያድነው በሽታ የለም ይባላል የስኳር መጠንን ይቀንሳል ፣ የደም ግፊትን ይቀንሳል ፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል ቅጠሉን.... እንደ ሻይ ተፈልቶ ፣ ዱቄቱ ተወቅጦ በውሃ መጠጣትም ይቻላል ፤ እንዲሁም እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላትም ይቻላል።
#ዳማከሴ፦ ለጉንፋን ፣ ለከባድ ራስ ምታት (ማይግሬን) በአፍንጫ ስቦ መውሰድ ፣ ለመተንፈሻ አካል ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድኃኒት ነው።
እንደሁም ስሩን ለ40 ደቂቃ አኝኮ ፆታዊ ግንኝነት ቢፈፅሙ የዘር ፍጥነትን (ቶሎመጨረስን ያስተካክላል ነገር ግን ጊዜአዊነው በየቀኑ መጠቀምን ይጠይቃል ።
#ሬት ልጣጩ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ ፈሳሽ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው ፣ ለፎረፎር ቢቀቡት፣ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደ ሻይ አፍልተው ቢጠጡት ጥቅሙን ያገኙታል።
ስሩ ተከትፎ ደርቆ ተፈጭቶ ቢቀቡት ፈንገስን ያጠፋል።
#አርማ ጉሳ፦ አረንጓዴውን ቅጠል በማድረቅ ወቅጠው እንደ ሻይ ለረጅም ጊዜ በመጠጣት የስኳር ህመምተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ፈጥኖ የማውረድና የመቀነስ አቅም አለው። ቅጠሉን ደግሞ በአረንጓዴነቱ ወቅጠው ጨምቀው ቢጠጡት ከቁርጥማት የመፈወስ ኃይልና የምግብ ፍላጎት የመክፈት ኃይል አለው። እንዲሁ ለክፉ ሱስና ለደም ግፊትም ፈዋሽ መድኃኒት ነው።
#የእንጆሪ ቅጠል፡- በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል። ስሩ ለስንፈተወሲብ ፈዋሽነው ።
#ጣዝማ ማር፦ ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የማር ዓይነት ሲሆን ከነጭ አዝሙድና ኮረሪማ ጋር በመቀላቀል ጠዋት ጠዋት ሁለት ማንኪያ በመውሰድ ከሳል ፣ ከአስም ፣ ከቁርጥማት ወዘተ ህመም ማገገም ይቻላል። ይህንን መድኃኒት የወሰደ አንድ ሰው መድኃኒቱ እንዲሠራ ቢያነስ ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ተኩል ጊዜ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይጠጣ ይመክራል።
#ሎሚ፡- ለብዙ ዘመናት ከምግብ መመረዝና ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የሆድ በሽታ ለመፈወስ ሲጠቀሙት የቆየ ባህላዊ መድኃኒት ነው።
የሎሚ ውሀ ከነጭሽንኩርት ጋር አቀላቅሎ ውሀውን ቢቀቡት ብግር ማድያት ያድናል።እንዲሁም ለቆዳ አላርጅክ ቢቀቡት ያድናል።
#እንቆቆና መስመስ፦ ለሆድ ትላትልና መሰል በሽታዎች ተፈጭቶና ተበጥብጦ ከኮሶ ጋር በመደባለቅና በመጠጣት ለኮሶ ትልና መሰል የሆድ ህመም መድኃኒት ነው።
#የእንሰት ስር(አምቾ)፡- ከውስጥ አካሉ የሚገኘው ውሃ እና አሚቾው ተቀቅሎ ደጋግሞ መብላት እንዲመግል የተፈለገ የተጎዳ የሰውነት አካልም ሆነ በሰውነት የወጣ ማንኛውም እባጭ መግል ሆኖ እንዲፈነዳ/እንዲወጣ ያግዛል ፣ የተሰበረ አጥንት በወጌሻ ማጀል ሲያስፈልግ የተሰበረው ቦታ ለማለዘብ (ለማለስለስ) አምቾውን በእርጎ እያማጉ ደጋግሞ መብላት ነው ፣ በጠቦት ሾርባ ደጋግሞ መብላት በመኪናም ሆነ በጦር ሜዳ ስጋው የተቦጨቀ ወይም አጥንቱ ላይ አደገኛ ስብራት ያጋጠመው ቁስሉ እንዲሽር(እንዲጠገን) ያደርጋል።
#ኮሶ፡- የደረቀ የኮሶ ዛፍ አበባ ከእንቆቆና መስምስ ወቅጦ በብርጭቆ በመጠጣት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትልን ጠራርጎ ማስወጣት ይቻላል።
#እነዚህ እፅዋቶች እንደየ አከባቢው አጠራር ስማቸው ሊለያይ እንደሚችል ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል።
በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ #ሸር ማድረግዎን እንዳይረሱ
የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይቀርባል ይብራራል
# 09 12 99 97 05 በስራ ሰዓት ይደውሉ
#እናመሰግናለን
62 views08:40