Get Mystery Box with random crypto!

በኮንሶ ዞን አንድ አይን ብቻ ያላት የበግ ግልገል ተወለደች አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲ | Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

በኮንሶ ዞን አንድ አይን ብቻ ያላት የበግ ግልገል ተወለደች

አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኮንሶ ዞን፤ ካራት ዙሪያ ወረዳ ታችኛው ሶሮቦ ቀበሌ አንድ አይን ብቻ ያላት የበግ ግልገል መወለዷ ተገልጿል።

የካራት ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ኢሳያስ እስጥፋኖስ፤ በኮንሶ ዞን አከባቢ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት መሆኑን በመግለጽ፤ ክስተቱ ከብዙ ሺሕ ውልደቶች መካከል ሊከሰት የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል።

ዶክተር ኢሳያስ እንደዚህ አይነት ክስተቶች ያልተለመዱ መሆኑና "ኮንጄንታል ማልፎርመሽን" የሚባል ተፈጥሯዊ ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።

በአንድ አይን የተወለደችው የበግ ግልገሏ የላኛው መንጋጋ እና አፍንጫ እንደሌላት በዚህም በአፏ እንደምትተነፍስ የእንስሳት ሃኪሙ አስረድተዋል።

ነሐሴ 20 ቀን 2014 ማታ የተወለደችው ግልገሏ፤ እስካሁን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ መገለጹን የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n