Get Mystery Box with random crypto!

የተፈጥሮ ጋዝ እና የድፍድፍ ነዳጅ ክምችትን መጠን እና አወጣጥ የሚያሳውቅ የመጀመሪያ ጥናታዊ ሰነድ | Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

የተፈጥሮ ጋዝ እና የድፍድፍ ነዳጅ ክምችትን መጠን እና አወጣጥ የሚያሳውቅ የመጀመሪያ ጥናታዊ ሰነድ ይፋ ተደረገ

አርብ ነሐሴ 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ ክምችት መጠንን እና አወጣጥ የሚያሳውቅ የመጀመሪያ ጥናታዊ ሰነድ ይፋ መደረጉን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ "ሰነዱ የተፈጥሮ ጋዝ እና ድፍድፍ ነዳጅ የማልማት አገራዊ እቅዳችንን አንድ እርምጃ ያራመደና በትልቁ የመንግስት ቁርጠኝነት የታየበት ሥራ ነው" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም፤ ሰነዱ ለብዙ ዓመታት ሲጠየቅ የነበረና እስካሁን ያልተመለሱትን፤ ምንና ምን ያህል የሚለውን የመለሰ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሰነድ መሆኑ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

"ይህ ሰነድ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ መጠንና የኢኮኖሚ አዋጭነት የማረጋገጫ ሰርተፊኬት ነው።" ያሉት ኢንጂነር ታከለ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ፣ የፋይናንስ እና በዚህ ኢንቨስትመንት አቅም ያላቸው ኩባንያዎች መጋበዝ የሚያስችልና የመንግስትን የመደራደሪያ አቅም እንደሚያጎለብትም ተናግረዋል፡፡
____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n