Get Mystery Box with random crypto!

የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል G+4 ሕንፃ በይፋ ተመረቀ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ዲ | Addis Ababa Design And Construction Works Bureau

የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል G+4 ሕንፃ በይፋ ተመረቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እና በመላኩ ግርማ ሕንፃ ስራ ተቋራጭ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል G+4 ሕንፃ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም፣የጉለሌ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በተለያዩ ምክንያቶች ሲጓተት ቆይቶ የነበረ ሲሆን የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ባሳለፈው ውሳኔ እና ባደረገው ልዩ ክትትል ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርጓል፡፡

ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ማዕከሉ በ950 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ሰልጣኞች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና የሚወስዱባቸው የመማሪያ ክፍሎችና ቢሮዎች፣ባርና ሬስቶራንት፣የሴቶችና የወንዶች የውበት ሳሎን የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ-ልማቶች ተሟልተውለታል፡፡.........