Get Mystery Box with random crypto!

አገልግሎት አሰጣጡን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ዓቅም የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በጉለሌ ክፍ | Addis Ababa Design And Construction Works Bureau

አገልግሎት አሰጣጡን ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ዓቅም የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በጉለሌ ክፍለከተማ በይፋ ተመርቀዋል፡፡

በክፍለከተማው ከተመረቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ የሚጠቀሰው ባለ 3 ወለሉ የወረዳ 01 አስተዳደር ህንፃ አንዱ ሲሆን በክፍለከተማው ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ባለቤትነት እንዲሁም በታቡ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ ተቋራጭነት ግንባታው ተከናውኖ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርጓል፡፡

በ230 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ለወረዳው የተለያዩ ፅ/ቤቶች የቢሮ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ግንባታው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይና ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዲሁም የጉለሌ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡

ይህ ሕንፃ የወረዳውን አስተዳደር የቦታ ጥበት በመቅረፍ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ምቹ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ዓቅም ከመፍጠርም ባለፈ ለሰራተኛውም ምቹ ከባቢን በመፍጠርና የስራ ተነሳሽነቱን ወደላቀ ደረጃ ከፍ በማድረግ ምርታማነቱን የማሳደግ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በመንግስት ወጪ የተገነቡ 17 ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 104 የቤት ዕድሳት ስራዎችና ሌሎች ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነሐሴ 26/2014 ዓ/ም