Get Mystery Box with random crypto!

የጉለሌ ክፍለከተማ ሲያስገነባቸው የቆዩትን የልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በይፋ አስመረቀ፡፡ በ | Addis Ababa Design And Construction Works Bureau

የጉለሌ ክፍለከተማ ሲያስገነባቸው የቆዩትን የልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በይፋ አስመረቀ፡፡

በክፍለከተማው የተገነቡና ከ171.2 ሚሊዮን ብር በላይ በመንግስት ወጪ የተደረገባቸው 17 የልማት ፕሮጀክቶች እንዲሁም 52 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው 104 ቤት ዕድሳት ስራዎችና 33.7 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የኮብልስቶን፣የፖሊስ ኮሚኒቲ ማዕከል፣የድጋፍ ግንብ የዲች ዝርጋታና የካልቨርት ስራዎችና ሌሎችም የልማት ግንባታዎች በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት በይፋ ተመርቀዋል፡፡

በጉለሌ ክፍለከተማ ከተገነቡ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ያስገነባውና መገኛው በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ የሆነው የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ባለ 5 ወለል ሕንፃ፣የወረዳ 01 አስተዳደር ባለ 3 ወለል ሕንፃ፣የጉቶሜዳ ስፖርት ማዘውተሪያ በዛሬው ዕለት ከተመረቁ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪም በክፍለከተማው የመጀመሪያ የሆነው የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም፣የጉለሌ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነሐሴ 26/2014 ዓ/ም