Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_tv — አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_tv — አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN
የሰርጥ አድራሻ: @addis_tv
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.17K

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-28 20:56:51
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበት ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ነው።

በአሜሪካ መንግስት መቀመጫ ‘ካፒቶል ሂል’ ፊት ለፊት እየተካሄደ በሚገኘው ሰልፍ ላይ ከአሜሪካ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በተጨማሪ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳትፈዋል።

‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎች የኢትዮጵያን ሕልውና የሚጎዳ እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚያበላሽ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል የሚል መልዕክት በሰልፈኞቹ እየተላለፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡

“ማዕቀብ መጣል ለኢትዮጵያ ጉዳትን እንጂ ምንም ጥቅም አያስገኝም ፤ ጎጂ የሆኑት ረቂቅ ሕጎች ውድቅ መደረግ አለባቸው” የሚሉ መፈክሮችም እየተላለፉ ነው።

በአሜሪካ የኮንግረስ አባል ቶም ማሊኖውስኪ (ኒውጀርሲ) ዋና አርቃቂነት፣ በያንግ ኪም (ካሊፎርኒያ)፣ ግሪጎሪ ሚክስ (ኒው ዮርክ)፣ ዴቪድ ሲሲሊን (ሮድ አይላንድስ)፣ ብራድ ሼርማን(ካሊፎርኒያ) እና ማይክል ማካውል (ቴክሳስ) ደጋፊነት የተዘጋጀው ‘ኢትዮጵያ ስታብላይዜሽን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ አክት’ ወይም ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ በኮንግረሱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ውይይት እንደተደረገበት የሚታወስ ነው።

የ‘ኤችአር 6600’ ተጓዳኝ ወይም አጋዥ (ኮምፓኒየን ቢል) የሆነው የኢትዮጵያ ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2021’ ወይም ‘ኤስ.3199’ በአሜሪካ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርዚ) ዋና አርቃቂነት፣ በሴናተር ጀምስ ሪስች (ኢዳሆ)፣ በሴናተር ክሪስ ኩንስ (ዴልዌር) እና በሴናተር ቶም ቲሊስ (ኖርዝ ካሮላይና) ደጋፊነት የተዘጋጀ ነው።

የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ በ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕግ ላይ ነገ ውይይት እንደሚያደርግ ኢዜአ ዘግቧል።

@Addis_Tv
3.1K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 17:27:31
2.9K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 17:26:24 በአዲስ አበባ የተሰረቁ የተለያዩ ዕቃዎችን እየተቀበሉ በሚሸጡ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በመዲናዋ የተሰረቁ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን በሚቀበሉ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ በመዲናዋ ልደታና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተሰረቁ ዕቃዎችን በመግዛት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ፥ የንብረቶቹ ማከማቻ የነበሩ ሱቆች ላይም እርምጃ ተወስዷል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3፣ ወረዳ 4 እና ወረዳ 7 አካባቢ አንዳንድ ሱቆች በስርቆት የሚመጡ የተለያዩ ዕቃዎችን እንደሚቀበሉ ተደርሶባቸዋል።

በመሆኑም ፖሊስ በክፍለ ከተማው መጋቢት 15 እና 16 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ ሱቆች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ይዟል።

ፖሊስ በልደታ ክፍለ ከተማ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 80 የሞባይል ስልኮች፣ 24 ሲም ካርዶች፣ ሁለት ላፕቶፕ፣ አንድ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እና በርካታ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ተይዘዋል።

ከተያዙት ዕቃዎች ጋር 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽኑ በመግለጫው አመልክቷል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማም መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች በንግድ ሱቆች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 618 የሞባይል ስልኮች፣ አምስት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ 45 ሲም ካርዶች እና ሌሎችም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተይዘዋል።

በተመሳሳይ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የንብረት ዓይነቶች በተለያየ አጋጣሚ የጠፋባቸውና የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ባስመዘገቡት መሰረት እየተመሳከረ በመረጋገጥ ላይ መሆኑ ታውቋል።

በአዲስ አበባ በስፋት እየተስተዋለ የመጣውን ሌብነትና ዘረፋ ለመቆጣጠር በቀጣይም ቁጥጥሩን በማጠናከር እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@Addis_Tv
2.8K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 17:26:16
2.5K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 17:24:15
የብልፅግና ፓርቲ ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የሚመልሱ እቅዶች ተዘጋጅተው እንዲተገበሩ አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው አንደኛ ጉባዔው ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች አስመልክቶ በመላ ሀገሪቱ ከህዝቡ ጋር ሲያደርግ የነበረውን ውይይት አጠናቋል፡፡

የውይይቶቹን መጠናቀቅ ተከትሎም በዛሬው እለት በማእከል ደረጃ የመድረኮቹ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተገኙበትና የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በመሩት የዛሬው መድረክ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደር መድረኮች የተነሱ ዋና ዋና ሃሳቦች ተገምግመዋል፡፡

በህዝቡ የተነሱትን የህዝብ ጥያቄዎች ለመመለስና ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ዝርዝር እቅዶች ተዘጋጅተው እንዲተገበሩ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በመሆኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር እንዲገባ ፓርቲው አቅጣጫ ማስቀመጡን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@Addis_Tv
2.6K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 17:02:18
የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሁለቱ አገራት መሪዎች በሁለትዮሽ አገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና ጂቡቲ ለረጅም ዘመናት የቆየና የጠበቀ ወዳጅነት ያላቸው አገሮች ናቸው።

የሁለቱን አገሮች የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በተለይም በፖለቲካና ኢኮኖሚ መስኮች ይበልጥ ተቀራርበው በመስራት ላይ ይገኛሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያና ጂቡቲ በባቡር፣ በመንገድ፣ በውሃ፣ በቴሌኮም፣ በኤሌክትሪክ ሃይል እና ሌሎችም የልማት መስኮች የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

@Addis_Tv
2.9K viewsedited  14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 17:01:24
አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሜ የጎዳና ሩጫ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ።

አትሌቱ 28:34 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ሪከርድ ጭምር ሰብሮ ውድድሩን ማሸነፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

@Addis_Tv
2.6K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 10:33:16
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 82 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መረቁ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የጤና፣ የትምህርት፣ የስፖርት ማዘውተሪያን ጨምሮ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 82 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መረቁ።

በክፍለ ከተማው የተመረቁት 82 ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ግንባታቸው ተጠናቆ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የተማሪ ምገባ አዳራሾች፣ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ኢዜአ ዘግቧል።

ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ አጠቃላይ 162 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ታውቋል።

በመሆኑም የፕሮጀክቶቹ ምርቃት ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ በተገኙበት ተከናውኗል።

@Addis_Tv
2.8K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 14:11:19 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም ትኩረቱን በመካከለኛና ትላልቅ የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ቴክኖሎጂን መጠቀም፣ መቅዳትና ማላመድን መሠረት ያደረገ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በማውጣት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

በፖሊሲው አፈጻጸም ሂደት የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም መሰረታዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር ስኬታማ እንዳልነበር ከተደረጉ ጥናቶች መረዳት ተችሏል፡፡

በመሆኑም ለአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ልማት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ፤ የኢንተርፕራይዞችን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ ከምርታማነታቸው ጋር ያላቸው ትስስር የሚያጠናክር፤ ለፈጠራ ስራ /Innovation/ ትኩረት የሚሰጥ ፖሊሲ በማስፈለጉ፣ ከግብርና እና ከማኑፋክቸሪንግ በተጨማሪ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ለአገራዊ ብልጽግና መሰረት ተደርገው በመወሰዳቸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲታገዙ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፣ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ለውጦች እና ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት የሚችል እና የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማትን የሚያፋጥን ሁሉአቀፍ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ግብዓቶች በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

2. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው የ11 የአስፈጻሚ ተቋማትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ሲሆን በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት፡-

• የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣

• የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣

• የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣

• የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣

• የኢትዮጵያ ደን ልማትን ሥልጣን፣

• የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣

• የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣

• የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣

• የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣

• የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና

• የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት

አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ያጸደቀ ሲሆን ደንቦቹ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውሉ ምክር ቤቱ ወስኗል

@Addis_Tv
2.7K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 14:11:09
2.3K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ