Get Mystery Box with random crypto!

400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር ዋለ መነሻውን ከጅቡቲ | አዲስ ሪፖርተር - NEWS

400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር ዋለ

መነሻውን ከጅቡቲ ወደብ አድርጎ መዳረሻውን ወረታ ከተማ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ፤ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ሕገ ወጥ ድርጊቱ የተፈጸመው በባህርዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ሐምሌ 16/2015 ሲሆን፤ አሽከርካሪው በአሳቻ ሰዓት በመጠበቅ ከሌሊቱ 6:00 ላይ የአፈር ማዳበሪያውን በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ሲያከፋፍል በኅብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የሰባታሚት ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር ኮንስታብል ዮሐንስ ጥላሁን ተናግረዋል።

አብዛኛው ማዳበሪያ ሳይራገፍ ከነተሽከርካሪው ቢያዝም፤ ከ140 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለግለሰቦች በሕገ ወጥ መንገድ መሰራጨቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ፖሊስ ባደረገው ቤተ ለቤት ፍተሻ ከተሽከርካሪው ተራግፎ በግለሰቦች ቤት የተከዘነ በርካታ የአፈር ማዳበሪያ መገኘቱም ተነግሯል፡፡

በዚህም 89 ኩንታል ማዳበሪያ በአንድ ግለሰብ ቤት የተገኘ ሲሆን፤ 24 ኩንታል ማዳበሪያ ደግሞ በአንድ ግለሰብ ቤት በአልጋ ሥር እና በኩሽና ውስጥ መገኘቱ ተገልጿል።

አሽከርካሪው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ኮንስታብል ዮሐንስ ገልጸው፤ ኅብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ተግባርን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

አማራ ለሆኑ ብቻ

https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0
https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0