Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁ | አዲስ ነገር መረጃ

መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም።

በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ "ሸኔ" ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል።

" በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል። አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ።" ብለዋል።

    @Addis_News