Get Mystery Box with random crypto!

ማስቲካን ጨምሮ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸዉ ምርቶች ላይ የቀረጥ ማሻሻያ ተደረገ የገቢዎች ሚኒስ | አዲስ ነገር መረጃ

ማስቲካን ጨምሮ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸዉ ምርቶች ላይ የቀረጥ ማሻሻያ ተደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴር ማስቲካን ጨምሮ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸዉ ምርቶች ላይ የቀረጥ ማሻሻያ ማድረጉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባኤው በአዋጁ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ታሳቢ በማድረግ አዋጁ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

የአዋጁ ማሻሻያ ታሰቢ ያደረገው ተደራራቢ የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸው ምርቶች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ፣ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል ለማድረግ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸው የነበሩት አንዳንድ ምርቶች ላይ ታክሱን ለማንሳት፣ እንዲሁም በአስተዳር ምክንያት የተደረጉ ማስተካከያዎችን እና የማሻሻያውን ዋና ዋና ምክንያቶችን ከመረመረ በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1287/2015 እንዲጸድቅ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ማስቲካ ፣ የቸኮሌት ምርቶች ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ባህሪዉ ያልተለወጠ ኢቴል አልኮል፣ ጨዉ ፣ ምንጣፎች እና የእንስሳት ስብና የአትክልት ዘይት የኤክሳይዝ ታክስ ቅነሳ ከተደረገባቸው ምርቶች ዉስጥ ይጠቀሳሉ።

ዳጉ ጆርናል
@Addis_News
@Addis_News