Get Mystery Box with random crypto!

ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች ሶስት የቡርጂ አርሶአደሮች መገደላቸዉ ተነገረ። በደቡብ ክልል በ | አዲስ ነገር መረጃ

ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች ሶስት የቡርጂ አርሶአደሮች መገደላቸዉ ተነገረ።

በደቡብ ክልል በቡርጂ ልዩ ወረዳ በትላንትናው ዕለት ከምዕራብ ጉጂ የመጡ ናቸዉ በተባሉ የታጠቁ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሶስት አርሶ አደሮች መገደላቸዉን እና በርካታ ከብቶች መዘረፋቸዉን ምንጮች ተናግረዋል።

ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ገደማ በዋሌያ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ የእርሻ ስራ እና ጤፍ በማጨድ ላይ የነበሩ ሶስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ከ50 በላይ ከብቶች መዘረፋቸዉን የቡርጂ ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረወልድ ሂዶ ተናግረዋል። ለጥቃቱ ተጠያቂ የሚሆነዉ መንግስት "ኦነግ ሸኔ" በማለት የሚጠራቸዉ ቡድኖች ናቸዉ የሚሉት ኃላፊዉ የጉጂ ማህበረሰብ ግን በዚህ ዉስጥ አይካተትም ሲሉ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

በቡርጂ ልዩ ወረዳ በተደጋጋሚ ከምዕራብ ጉጂ በሚነሱ ታጣቂዎች ግጭት እንደሚነሳ የሚያስታውሱት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊው አቶ ገብረወልድ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ብቻ አምስት አርሶአደሮች ሲገደሉ ከ 60 በላይ ከብቶች ተዘርፈዋል ብለዋል።

ለግጭቱ መነሻ ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ "የድንበር ይገባኛል" የሚል ሳይሆን ሌላ አላማ ያለው ነው የሚሉት የልዩ ወረዳዉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረወልድ ሂዶ መንግስት በሌሎች አከባቢዎች እያደረገ የሚገኘዉን የህግ ማስከበር ዘመቻ በቡርጂ እና በጉጂ ኦሮሚያ አከባቢዎች ላይም መዉሰድ እንደሚገባዉ ተናግረዋል።
Via AddisZeybe

@Addis_News
@Addis_News