Get Mystery Box with random crypto!

12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በዛሬው እለት ተ | አዲስ ነገር መረጃ

12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በዛሬው እለት ተጀመረ

መንግስት ለዜጎች ትኩረት በሰጠበት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እስካሁን በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቄ አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ከሳውዲ አረቢያ ውጭ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሳራቅ ሀጋራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ራሱን የቻለ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲንቀሳቅስ መቆየቱን ገልፀዋል።

በዚህም በዛሬው እለት 12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

ከታንዛኒያ፣ከማላዊ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ ፣ ጁቡቲ ሱዳን፣ የመን እና ኦማን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚመለሱት ከአለም የፍልሰት ድርጅት አይ ኦ ኤም  ጋር በተደርገ የጋራ ስራ እንደሆነም አምባሳደር መለሰ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

መንግስት ከሳውዲ አረቢያ ከመጋቢት 21 ጀምሮ በተደረጉ 126 በረራዎች 102 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችንም መመለሱንም አንስተዋል ። እነዚህ ዜጎች በሶስት ወራት ውስጥ ከሪያድ እና ከጅዳ የተመለሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

@Addis_News
@Addis_News