Get Mystery Box with random crypto!

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የመጠለያ ጣቢያ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ በዋግ ኽ | አዲስ ነገር መረጃ

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የመጠለያ ጣቢያ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከአበርገሌ፣ ከዝቋላ፣ ከባዱቢ ፣ከዛታ፣ ከወፍላ እና ኮረም አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች በበጎ ፍቃደኞች የሚሰጠው ድጋፍ ከተደረገ አንድ ወራት ማስቆጠሩን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዝናሽ ወርቁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረው መደበኛ ድጋፍ ያልተቋረጠ ቢሆንም በበጎ ፍቃደኞች ይሰጥ የነበረው ድጋፍ መቅረቱ ከተፈናቀዮች አንፃር ክፍተት መፍጠሩ ተገልፆል፡፡በተለይም ለአጥቢ እና ለነብሰ ጡር እናቶች ተጨማሪ ድጋፍ እንደሌላቸው እና ከክረምቱ ጋር ተያይዞ ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም ማይ ጉሊት በተባው ስፍራ ያሉት ተፈናቃዮች ያሉበት መጠለያ ከፍተኛ ክፍተት ያለበት ዝናብ የሚስገባ ከመሆኑ አንፃር የመጠለያ ጣቢያ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆኑ ለተከታታይ ቀናት የሚዘንብ ከሆነ የከፋ ችግር ሊከሰት ይችላል ሲሉ ቡድኑ መሪዋ አስጠንቅቀዋል፡፡

በመሆኑም በበጎ ፍቃደኞች አሁንም ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ እና በተለይም ለተፈናቃዮችም በቂ መጠለያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነዉ ሲሉ ወ/ሮ ዝናሽ ወርቁ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

@Addis_News
@Addis_News