Get Mystery Box with random crypto!

መች ተሰናኘን? መጣመር አማረን እንጂ መች ተሳካልን? .... ወዲያ እዛ ቀያቴ አድማስ ላይ ተንጠል | 👑 አዳም ረታ 👑

መች ተሰናኘን? መጣመር አማረን እንጂ መች ተሳካልን? .... ወዲያ እዛ ቀያቴ አድማስ ላይ ተንጠልጥሎ መቼ ደረስንበት የምኞታችንን ስዕል።
የደረስንበት ሲመስለን ከአይናችን የሸሸው ያ የህልም እንጀራ የሚርበን የፍቅራችን ማዕድ ነበር።
የምንሻውን መኖር አለመቻላችን የማን ጥፋት ነው?(የእኔ የብቻዬ መሻት የነበር እንደሆነስ በምን አውቃለሁ ... ከዓይናችን ስር የበበነው ጉም ፍቅር የኔ መሠሠት ብቻ የነበር ከሆነስ? )
በእንዴት ያለ መግፋት ብገፋሽ ነው በእንደዚያ ያለ መንደርደር የራቅሽው?.....ወይስ መሄድሽ ከጅምሩ የተወጠነ ነበር ( ዓላማሽ ተከታይ ልብ ማፍራት ነበር?) እኔ ግን አልከተልሽም ምክንያቱም ያ የእኛ መንገድ አይደለም። ( ያ የአንቺ እና ምንአልባት.... ) የኔ መንገድ ግን ተሰውሮብኛል። ምንአልባት እንደ ሹራብሽ ጠቅልለሽ ሻንጣሽ ውስጥ ሸሽገሽ ሄደሽም ሊሆን ይችላል።
በፍቅር አላመንኩሽም ነበር እኔ ጋር የነበረሽ ስም "ፍቅር" አልነበረም። ጥንስሱ ፍቅር መሆኑ የገባኝ ሽኝቱ ላይ ነበር።
ይሄን ለማን እና ለምን እንደምፅፈው አላውቅም (አንቺ አዝነሽ አትመለሽ) ግን የሆነ ዓይነት ቀላል መተንፈስ ይሰማኛል። ልብሽ እርግብግብ ይመስለኝ ነበር፥እንደ እናት። ፍቅር አርግዘሽ ፍቅር የምትወልጂ መስሎኝ ነበር። (ብዙ ነበሮች) ሃሃ ሃሃ (ይሄ "ሃሃሃ"... ተራ የፊደል ቅጥ ነው ወረቀት ደረት ላይ ተበትኖ ስታይው ውስጡ ግን እንባ ነው፣ውስጡ ግን ናፍቆት ነው ፤ ውስጡ ግን ፍቅር ነው ፣ ውስጡ ግን ንዴት ነው ......

@AdamuReta
@isrik

#ዕ_ያ