Get Mystery Box with random crypto!

ፍርሃትና ናፍቆት ┈┈•✦•┈┈ ፈቃደ አዘዘ ' 'ሊመጣ ነው!' ሲሉኝ፣ 'የመቅሰፍት | 👑 አዳም ረታ 👑

ፍርሃትና ናፍቆት
┈┈•✦•┈┈
ፈቃደ አዘዘ
'
"ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ፣
"የመቅሰፍት ጊዜ! የመከራ ዘመን!"
"የት ደርሷል?" ስላቸው፣
"ቀርቧል!" ብቻ እያሉኝ፣
"መች ይመጣል?"ም ስል፣
"ደርሷል!" ብቻ እያሉኝ፣
ይኸው አርባ ዓመቴ
በፍርሃት አለሁኝ፣
ወይ ዘመኑ መጥቶ
ደቁሶ አልደቆሰኝ፣
ፍርሃቱ - ፍርሃቱ - ፍርሃቱ ገደለኝ።

"ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ፣
"የሰላም የደስታ - የጥጋብ ዘመን!"
"የት ደርሷል?" ስላቸው፣
"ተቃርቧል!" እያሉኝ፣
"መች ይመጣል?"ም ስል፣
"ተዳርሷል!" እያሉኝ፣
ይኸው አርባ ዓመቴ
በናፍቆት አለሁኝ፣
ወይ ዘመኑ መጥቶ
በደስታ አላሻረኝ፣
ናፍቆቱ - ናፍቆቱ - ናፍቆቱ ገደለኝ

@AdamuReta
@isrik