Get Mystery Box with random crypto!

👑 አዳም ረታ 👑

የቴሌግራም ቻናል አርማ adamureta — 👑 አዳም ረታ 👑
የቴሌግራም ቻናል አርማ adamureta — 👑 አዳም ረታ 👑
የሰርጥ አድራሻ: @adamureta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 591
የሰርጥ መግለጫ

ቀንዎን ያሳምሩ
👉የአዳም ረታ እና ሌሎችም እውቅ ደራሲያን ስራዎች
👉ግጥሞች
👉የአማርኛ መፅሀፍት በ pdf
👉 አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ፅሁፎች
👉ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የምትፈልጓቸውን አንድ ላይ በ አዳም ረታ ያግኙ።
👉 የመፃህፍት ጥቆማ
@AdamuReta
@AdamuReta
@AdamuReta
For cross promotion contact
@isrik
@isrik

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-09 20:24:05
#ማነው "ምንትስ"?

... ኧረ ስንቱ፥ ሞልቶ ስንቱ፥ ብኩን የመንፈስ ምንትስ
ለስጋውም አብሮን ወድቆ፥ ዳግም በአእምሮው ሲረክስ
በልቦናውም ሲሴስን፥ በህሊናው ህግ ሲድስ
'ፍሪ-ደሜ' ነው እያለ፥ የኔኑ ደም ሲያልከሰክስ
በቃሉና በመንፈሱ፥ ወድቆ ደቅቆ ሲበሰብስ
ቴህ ወዲያ ማነው ምንትስ! ...

#ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን
#እሳት ወይ አበባ
#ማነው "ምንትስ"?

https://t.me/AdamuReta
16 viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:07:48 ===ቀልዶች በጃንሆይ ዙሪያ===
አፈንዲ ሙተቂ
--------
እስቲ ዛሬ ደግሞ ልዑል ተፈሪ መኮንን “ግርማዊ ጃንሆይ” ከሆኑ በኋላ የተቀለደባቸውን ቀልዶች እናካፍላችሁ፡፡
------------
ሁለት ሰዎች እየተጨዋወቱ ነው፡፡ አንዱ ጃንሆይን ይወዳል፡፡ አንዱ ጃንሆይን ይጠላል፡፡ ጃንሆይን የሚወደው ሰውዬ “ግርማዊ ጃንሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ” አለ፡፡ ጃንሆይን የሚጠላው ሰውዬ በጥፊ ከመታው በኋላ እንዲህ አለው፡፡
“አንተን ብሎ እድሜ ቆራጭ! ግርማዊ ጃንሆይ ለዘላለም ይንገሡ አትልም ነበር?”
------------
ግርማዊ ጃንሆይ የአማኑኤል ሆስፒታልን ሊጎበኙ ሄዱ፡፡ አንዱ ሻል ያለው እብድ እንዳያቸው ተጠጋቸውና “ማን ትባላለህ?” አላቸው፡፡
“ሞአ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነን” አሉት ጃንሆይ፡፡
ይህንን የሰማው እብድ ሳቅ እያለ “ጉድ ነው! እኔንም እብደት ሲጀምረኝ እንዲህ ነበር ያደረገኝ” አላቸው፡፡
(በርሱ ቤት ጃንሆይ ሊታከም የመጣ እብድ መስሎታል)
------------
እነ ኒል አርምስትሮንግ ጨረቃን ረገጡና ዓለም ጉድ አለ፡፡ የዓለም መሪዎች ወደ ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ ጆንሰን የደስታ መልዕክት ማጉረፍ ጀመሩ፡፡ እንደ አጋጣሚ አሜሪካ የነበሩት ቀዳማዊ ኃይሥላሴም እንዲህ አሉ፡፡
“ጨረቃ ላይ በመውጣት የሰራችሁት ስራ ለናንተ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ህዝብም ኩራት ነው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ተመራምራችሁ ጸሐይ ላይ እንደምትወጡ መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኋን”፡፡
ከጃንሆይ አጠገብ የነበሩት ልጅ ይልማ ዴሬሳ ደነገጡ እና “ጃንሆይ ጸሐይ ላይ መውጣት አይቻልም እኮ” አሏቸው፡፡ ጃንሆይም በስጨት ብለው “አንተ ደግሞ አቃቂር ታበዛለህ! እኛ መናገር እንጂ ስለሌላው ምን አገባን? ቢፈልጉ ጸሐይቱ እንዳታቃጥላቸው ማታ ማታ ይጓዙና ይውጡ!”
------------
የዩጎዝላቪያው ማርሻል ቲቶ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ካበቁ በኋላ ለጃንሆይ “ሀገራችሁ ጥሩ ናት። ግን ሰዎቻችሁ በየጎዳናው ይሸናሉ” አሏቸው። በሌላ ጊዜ ጃንሆይ ዩጎዝላቪያን እየገበኙ ሳለ በጎዳና ላይ የሚሸና ሰው አዩ። በዚህን ጊዜም ወደ ሰውዬው እያመለከቱ ለማርሻል ቲቶ “ተመልከት! ያንተም ሰዎች በመንገድ ላይ ይሸናሉ” አሏቸው። ቲቶ በጣም ተናደዱ። ወታደሮችን ጠርተው “እዚያ ወዲያ የሚሸናውን ሰውዬ ይዛችሁ ወደኔ አምጡት” በማለት አዘዟቸው። ወታደሮቹ ሰውዬው አጠገብ ከደረሱ በኋላ ባዶ እጃቸውን ተመለሱ።ቲቶም “ለምን አልያዛችሁትም?” አሉ።
“ይቅርታ ማርሻል የዲፕሎማቲክ መብቱን መድፈር አልቻልንም”
“የምን የዲፕሎማቲክ መብት?”
“ሰውዬው አምባሳደር ነው”
“የየት ሀገር አምባሳደር?”
“የኢትዮጵያ”
---------
ጃንሆይ እና ጸሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከተማ ወርደው መዝናናት አማራቸውና ተያይዘው ወጡ። የተቻለውን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ ሲዝናኑ ከቆዩ በኋላ መሸ። በፒያሳ በኩል ወደ ቤተ መንግሥት በመመለስ ላይ ሳሉ ሲኒማ ኢትዮጵያ ደረሱ። “እስቲ እዚህም ገብተን ትንሽ እንይ” አሉና ወደ ሲኒማው ገብተው ከተመልካቾች ተርታ ተቀመጡ።
በዚያ ዘመን ቴሌቭዥን በየቤቱ ስለሌለ ህዝቡ ወደ ሲኒማ ሄዶ ነው ዜና የሚከታተለው። በዜና ላይ ጃንሆይ የታዩ እንደሆነ ደግሞ ማጨብጨብ የዘመኑ ደንብ ነው። ታዲያ ዜና አንባቢው “ግርማዊ ጃንሆይ ዛሬ የጃፓን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ” አለና ዜናውን በምስል አቀረበው። ይሄኔ በአዳራሹ የነበረው ጠቅላላ ህዝብ አጨበጨበ። አሁንም ሌላ የጃንሆይ ዜና ቀረበ። ህዝቡም አጨበጨበ። ሌላ የጃንሆይ ዜና ተከተለ። ህዝቡ አፍታ በአፍታ ማጨብጨቡን ቀጠለ። ጃንሆይና ጸሓፌ ትዕዛዝ ግን አላጨበጨቡም። ይህንን ያየ አንድ ጎልማሳ ተመልካች ወደ ጃንሆይ ተጠግቶ “ሽሜ! ጉድ ሳይፈላብሽ ብታጨበጭቢ ይሻልሻል” አላቸው።
---------

@wegoch
@wegoch
@paappii
24 views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 11:58:34 መንገድ
ክፍል 1
(በእውቀቱ ስዩም)

በደናው ቀን ብርቱ ነበርሁ፤ ባንድ እጄ ፑሽአፕ እየሰራሁ በሌላው እጄ ጢሜን እላጭ ነበር፤ አሁን አንድ ኪሎ ሜትር ከተራመድሁ ይደክመኛል፤ ትናንት ከቤት ወጥቸ የቀበናን መንገድ ትንሽ ወረድኩና እንግሊዝ ኢምባሲ የተከለውን የስልክ እንጨት ተደግፌ እፍወይይይይ ብየ ተነፈስሁ፤ እፎይይ ስል ከሆዴ መለስተኛ አውሎ ነፋስ ወጣ! መንገድ ዳር በቆሎ ጠብሰው የሚሸጡ ሴቶች ባተነፋፈሴ ተደንቀው ዞር ዞር ያሉ አዩኝ “ አሁን የተነፈስከውን ባግባቡ ብትጠቀምበት አምስት ምድጃ ያቀጣጥላል” የሚሉኝ መሰለኝ ፤
የቀረውን መንገድ በመኪና ለመመለስ ፈለግሁ፤ ግድ ካልሆነ በቀር ራይድ አልጠራም፤ ቀን ጥሏቸው መንገድ ዳር የቆሙ ላዳዎችን እጠቀማለሁ፤ ይቺ ላዳ አሮጌ ናት፤ ፍሬቻዋ ስለተሰረቀ ፋኖስ ተገጥሞላታል፤ የላዳውን በር ልከፍተው ሞከርኩ፤ እምቢ አለኝ ፤ ሰውየው ከውስጥ ሆኖ ሊያግዘኝ ተፍጨረጨረ ፤ በመጨረሻ ወጣና ለሁለት መታገል ጀመርን፤ ከእልህና እህል አስጨራሽ ትግል በሁዋላ የላዳው ጋቢና በር እንደ ድስት ግጣም ተነሳ! ገባሁና ከሁዋላ ተቀመጥሁ፤ ሾፌሩ የሳይክል እግር የሚያክለውን መሪ እንደ በረኛ ተጠምጥሞበት ጉዙ ጀመርን፤
ከጎኔ ያለውን ሳተራምስ ከቆየሁ በሁዋላ “ ቀበቶ የለም እንዴ?” ስል ጠየኩት
“ ቀበቶ ተበላሽቷል! ሰንሰለቱን ብትጠቀም ይደብርሀል?”
እንደ ባህታዊ ሰንለቱን ታጥቄ ጉዞ ጀመርን፤
“ የማንን ሙዚቃ ላድርግልህ? “
“ የሙሉቀን መለሰ ይኖራል?”
“ አይጠፋም “ አለና ፤ ከእግሩ ስር ዳንቴል ለብሶ የተጋደመውን ቴፕ ቆስቁሶ ጥላሁን ገሰሰን ከፈተልኝ ፤
“የዘንባባ ማር ነው ፍቅርሽ
ቄጤማ ይመስላል ጸጉርሽ”
“ የዘንባባ ማር የሚባል ነገር ግን አለ?” የሚል ጥያቄ አነሳሁ፤
“ ፍቅር አይያዝህ ወንድሜ” አለ ሾፌሩ” ፍቅር ከያዘህ አይደለም የዘንባባ ማር ፤ የግራዋ ወተት ሊታይህ ይችላል” አለኝ ሾፌሩ
እንዲህ እያወጋን ስንሄድ የትራፊክ ፖሊስ ነፍቶ አስቆመን፤
“ ጥፋቴ ምንድነው?”
“ ወድያ ያለውን መብራት ጥሰህ መጥተኻል”
ሰውየው በናቱ በአባቱ በመላእክቱ እና በህብረተሰቡ ምሎ ሸመጠጠ፤
ለሀያ ደቂቃ ከተከራከሩ በሁዋላ ሾፌሩ “ የዛሬን አስተምረህ ልቀቀኝ “ ሲል ሰማሁት፤
“ አስተምሬ ብቀጣህ እመርጣለሁ” አለ ፖሊሱ ቅጣቱን ፈርሞ አቀበለው ፤ ከዚያ ሌላ ህግ የሚጥስ መኪና ፍለጋ በጉጉት ማማተር ጀመረ፤
ሾፌሩ የተሰጠውን ደረሰኝ ዳጎስ ባለ የቅጣት መዝገቡ ውስጥ ከወሸቀ በሁዋላ ፖሊሱ ወደ ቆመበት አቅጣጫ እየተመለከተ
በሚጢጢ ድምጽ “ እስቱቢድ” ብሎ ተሳደበ፤ በሆዱ ቢሳደብ ራሱ ከዚህ የተሻለ ሳይሰማ አይቀርም፤
22 views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 16:50:25 ለካ ህይወት ማለት

ይታዩኛል እኒያው ፍቅረኞች ሻማ ፊት
ፍቅር ለመጀመር ሻማዋን ለኮሷት
ፍቅር ለማፋፋም ሻማዋን አጠፋዋት

ለካስ ህይወት ማለት
ጨለማን ማብራት ነው ፣ ወይም ቀኑን ማጥፋት!

(( ነብይ መኮንን ))

@AdamuReta
@isrik
@AdamuReta
36 viewsedited  13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 16:02:34 ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት
(በእውቀቱ ስዩም)

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው ራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድር ለማምለጥ አይመችም፤ ከዚያም አልፎ፤ በንቁና አስፈሪ ዘበኞች ይጠበቃል፤ በአክሱም ዘመን ደብረዳሞ የልኡላን ማጎርያ ሆኖ አገልግሏል፤ የሸዋ ነገስታት በተራቸው ሲገዙ፤ ለዚህ ተግባር የመረጡት ቦታ፥ ወሎ ዛሬ ግሼን ማርያም የምትገኝበትን አምባ ነበር፤ የጎንደር ነገስታት በበኩላቸው ዘመዶቻቸውን “ወህኒ” ወደ ተባለ ስፍራ ማጋዝ ጀመሩ፤ ወህኒቤት የሚለውን ቃል የወረስነው ከዚህ ስፍራ ነው ፤ ወህኒ በመሰረቱ የፖለቲካ እስር ቤት ሲሆን ፥የመጀመርያው የፖለቲካ ወንጀል ከንጉስ መወለድ ነበር፤

ንጉሱ ድንገት ወራሹን ሳያሳውቅ በጦር ሜዳ ይገደላል እንበል፥ አንዱ የቤተመንግስት መኮንን ብድግ ይልና አንዱን ልኡል ከማጎርያ ቤት አውርዶ ዙፋን ላይ ያወጣዋል፤ ሌላው የጦር አዝማች ደግሞ የኔን ምርጫ ካላነገስኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ይነሳል፤ ባንጋሾች መካከል የሚደረገው ፉክክር መዲናይቱን ባንዴ ወደ ፍርስራሽ እና ያስከሬን ክምር ይቀይራታል::

የቀድሞ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ብሄራዊ አደጋ ለመቀነስ የፈጠሩት “ዘዴ “ የንጉስን ሞት መሰወር ነበር ፤ የንጉስ ሞት ቀርቶ ህመሙ እንኳ ለህዘብ ይፋ አይደረግም፤ በዘመነ መሳፍነት ጊዜ ፥ የየጁው ራስ አሊ ሲሞት ፤ አንድ አሳባቂ ( የዘመኑ ፓፓራዚ) ወሬውን አሾለከው፤ ወድያው የረጋው አገር መላወስ ጀመረ፤ ጉዳዩ ያሳሰባት አንዲት አልቃሽ እንዲህ ብላ ገጠመች፥

“ እሻ እሻ ነው እንጂ የእስራኤልን ሞት
እንዲያልቅሰው አሊን ለምን ቀበሩት “

“ እሻ እሻ “ ማለት ዝም በሉ ጸጥ በሉ ማለት ነው ፤ በዘመኑ የንጉስ ወገን ነን የሚሉ ሰዎች ዘራቸውን ከሰለሞን ስለሚመዝዙ “ እስራኤል “ በሚል የወል ስም ይታወቃሉ፤
በግጥሙ መስመር ላይ ያለው ህብረቃል “ እንዲያልቅሰው “ የሚል ነው፤ ሰሙ “ እንዲህ አልቅሰው “ ሲሆን ወርቁ “ ሰው እንዲተላለቅ” የሚል ትርጉም አለው ፤

ባጭሩ አልቃሺቱ፥
“ ህዘብ እንዳይተላለቅ
የንጉስ ሞት ይደበቅ “ ማለት ነው የፈለገችው ፤

ከጥንት እስከዛሬ አገረ -መንግስታችን የሚቆመው ባንድ ሰው ትከሻ ላይ ነው ፤ መሪ ሲታመም አገር ይታመማል፤ መሪ ሲሞት አገር በጥቂቱ ይሞታል፤ ይህንን መለወጥ የሚቻለው እንዴት ነው? የማይሞቱ ተቋሞችን በመገንባት ፤ የማይታመሙ ህጎችን በመመስረት? ወይስ ሌላ መላ አለ?

#ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@AdamuReta
@AdamuReta
38 viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 13:28:03 ፍርሃትና ናፍቆት
┈┈•✦•┈┈
ፈቃደ አዘዘ
'
"ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ፣
"የመቅሰፍት ጊዜ! የመከራ ዘመን!"
"የት ደርሷል?" ስላቸው፣
"ቀርቧል!" ብቻ እያሉኝ፣
"መች ይመጣል?"ም ስል፣
"ደርሷል!" ብቻ እያሉኝ፣
ይኸው አርባ ዓመቴ
በፍርሃት አለሁኝ፣
ወይ ዘመኑ መጥቶ
ደቁሶ አልደቆሰኝ፣
ፍርሃቱ - ፍርሃቱ - ፍርሃቱ ገደለኝ።

"ሊመጣ ነው!" ሲሉኝ፣
"የሰላም የደስታ - የጥጋብ ዘመን!"
"የት ደርሷል?" ስላቸው፣
"ተቃርቧል!" እያሉኝ፣
"መች ይመጣል?"ም ስል፣
"ተዳርሷል!" እያሉኝ፣
ይኸው አርባ ዓመቴ
በናፍቆት አለሁኝ፣
ወይ ዘመኑ መጥቶ
በደስታ አላሻረኝ፣
ናፍቆቱ - ናፍቆቱ - ናፍቆቱ ገደለኝ

@AdamuReta
@isrik
26 viewsedited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 12:40:05 መች ተሰናኘን? መጣመር አማረን እንጂ መች ተሳካልን? .... ወዲያ እዛ ቀያቴ አድማስ ላይ ተንጠልጥሎ መቼ ደረስንበት የምኞታችንን ስዕል።
የደረስንበት ሲመስለን ከአይናችን የሸሸው ያ የህልም እንጀራ የሚርበን የፍቅራችን ማዕድ ነበር።
የምንሻውን መኖር አለመቻላችን የማን ጥፋት ነው?(የእኔ የብቻዬ መሻት የነበር እንደሆነስ በምን አውቃለሁ ... ከዓይናችን ስር የበበነው ጉም ፍቅር የኔ መሠሠት ብቻ የነበር ከሆነስ? )
በእንዴት ያለ መግፋት ብገፋሽ ነው በእንደዚያ ያለ መንደርደር የራቅሽው?.....ወይስ መሄድሽ ከጅምሩ የተወጠነ ነበር ( ዓላማሽ ተከታይ ልብ ማፍራት ነበር?) እኔ ግን አልከተልሽም ምክንያቱም ያ የእኛ መንገድ አይደለም። ( ያ የአንቺ እና ምንአልባት.... ) የኔ መንገድ ግን ተሰውሮብኛል። ምንአልባት እንደ ሹራብሽ ጠቅልለሽ ሻንጣሽ ውስጥ ሸሽገሽ ሄደሽም ሊሆን ይችላል።
በፍቅር አላመንኩሽም ነበር እኔ ጋር የነበረሽ ስም "ፍቅር" አልነበረም። ጥንስሱ ፍቅር መሆኑ የገባኝ ሽኝቱ ላይ ነበር።
ይሄን ለማን እና ለምን እንደምፅፈው አላውቅም (አንቺ አዝነሽ አትመለሽ) ግን የሆነ ዓይነት ቀላል መተንፈስ ይሰማኛል። ልብሽ እርግብግብ ይመስለኝ ነበር፥እንደ እናት። ፍቅር አርግዘሽ ፍቅር የምትወልጂ መስሎኝ ነበር። (ብዙ ነበሮች) ሃሃ ሃሃ (ይሄ "ሃሃሃ"... ተራ የፊደል ቅጥ ነው ወረቀት ደረት ላይ ተበትኖ ስታይው ውስጡ ግን እንባ ነው፣ውስጡ ግን ናፍቆት ነው ፤ ውስጡ ግን ፍቅር ነው ፣ ውስጡ ግን ንዴት ነው ......

@AdamuReta
@isrik

#ዕ_ያ
25 views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:19:00 "ቃሌ ቃል ባይመስላት ስቀርባት ብትርቅም
ለወጉ ነው እንጂ ጠልታኝ እኮ አታውቅም
"
ብዬ ስነግራቸው ሰዎች ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
በማላቀው ምክንያት
እስቲ ዞረህ እያት
ሲሉኝ አያታለው
መች መልስ አገኛለው
ምንድነው? እላለው
መልሰው ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
"ስከተላት ብትሸሽ ስቀርባት ብትርቅም
ኮርታብኝ ነው እንጂ
ጠልታኝ እኮ አታውቅም "
የሚል ቃል ሲወጣኝ ሳቃቸው ይገናል
አሁን በእናና ሞት ይሄንን ማን ያምናል
እነሱ ያሳቃቸው
እኔ ያስተዋልኩትን መሆኑን ባላውቅም
ጥርሷ ይርገፍና
አብረን ባለን ጊዜ ስቃልኝ አታውቅም

*------------------*

(ሚኪያስ ፈይሣ)

@AdamuReta
@AdamuReta
@AdamuReta
40 viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 15:57:05 #ላጣሽ_አቅም_አጣሁ

ዓለማዊ ልቤ፥ለበሰልሽ ዳባ፥ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ፥ የጠፋብኝ እንባ፥ ፊቴ ላይ ተገኘ

ላጣሽ አቅም አጣሁ፤
የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን ገድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብየ ነበር፥ ቄስ አንዳስተማረኝ
አንቺን አጣሁ ብየ፥ ማመኑ ቸገረህ

ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤

ልረሳሽ አልቻልኩም፥ ልረሳሽ እልና
ፊትሽን አትመሽ፥ በየብስ በደመና
ከንፈርሽ ያውና
ፈገግታሽ ያውና
ውብ ዓይንሽ ያውና።

@isrik
@AdamuReta
41 viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 15:54:14
የደመቁ ገፆች . . . . . .


ጋሽ ስብሀት ገ/እግዜአብሔር የመይሳው ካሳ መጣጥፍ መግቢያ ላይ እንዲህ ይለናል " አንዳንዴ በህይወታችን የሚያጋጥመን አስገራሚ ነገር አለ ። ለሰው ብንነግረው አያምነንም ልቦወለድ አስመስለን ብንነግረው ደሞ " ኢ- ተአማኒ ነው አይታመንም "ይላል።ፈጣሪ ግን አያልቅበትም ኢ - ተአማኒ የምንለውን እሱ በህይወታችን እንዲደርስ አድርጎ
ያሳየናል"

ስንቶቻችንን ይሁን ለሰው ብንነግረው ማያምነንን ክስተት ማያልቅበት ፈጣሪ ጀባ ብሎ ያስደመመን . . . .
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ስብሀት ገ/እግዜአብሔር (የመይሳው ካሳ)
አለማየሁ ገላጋይ (መለያየት ሞት ነው)
@AdamuReta
32 viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ