Get Mystery Box with random crypto!

ዮጵ ብዕርና ወረቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ yopbirnawereket1234 — ዮጵ ብዕርና ወረቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ yopbirnawereket1234 — ዮጵ ብዕርና ወረቀት
የሰርጥ አድራሻ: @yopbirnawereket1234
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 843
የሰርጥ መግለጫ

ሊንኩን ተጭነው ጥበብን በነፃነት ይኮምኩሙ ።
ጥበበኛ ባንሆንም ጥበበኛ ትውልድን መፍጠር እንችላለን !!!
#ዮጵ ብዕርና ወረቀት
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ሃሳብ አስተያየታችሁ ከታች ባሉት ሊንኮች ልታባደርሱን ትችላላችሁ ።
@debochYegohu1
ወይንም
@yeablijabu124
ልታደርሱን ትችላላችሁ ።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-12 16:03:15 ምግብ ቀረበ ተብሎ ያለ ሀሳብ አይበላም፣ አልጋ ተመቸኝ ተብሎ ያለ ሀሳብ አይተኛም፣ገንዘብ አለኝ ተብሎ ያለ መጠን አይወጣም፤ እግር አለኝ ተብሎ ያለ ምዕራፍ አይኬድም፣ይህ ኅሊናን ማደንዘዝና ጥቅም አልባ ማድረግ ነው፡፡
ወገኔ ያለህን ነገር በአግባቡና በሰአቱ ተጠቀምበት።

በተለይ ገንዘብ ላይ ማውጣት ያለብህ ቦታ ላይ ብቻ አውጣ ከሁሉም ደግሞ አፍህን ቆጥብ ማውራት ካለብህ ቦታ ላይ ብቻ አውራ። በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህ ወሰን ይኑረው። አያችሁ እናንተ ያላችሁን ጨርሳችሁ ከሰጣችሁ ሰጭ መሆን ቀርቶ ተሰጭ ትሆናላችሁ ነበረኝ እሚለው ቃል አለኝ እሚለውን አይተካከላትም።
ሁሉንም ነገር በአግባቡና በሰዓቱ መጠቀም ጥሩ ነገር ነው።

https://t.me/yopbirnawereket1234
https://t.me/yopbirnawereket1234
315 viewsደቦጭ / አማሩ, 13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 22:01:24 እምነት
""'''''''''''
የዓለም እሾህ ወግቶኝ
ከቤተ'ስቲያን ቅፅር፥መሬት ተንበርክኬ፤
ለጨነቀኝ ጭንቀት
ዕንባን አጎርፋለሁ፥መቅደሱን ታክኬ...

ፀልዬ ስነሳ
ያንኑ ጭንቀቴን አብሰለስላለሁ፤
አጉተመትማለሁ፤
አንስቼ ጥላለሁ፤
ድጋሚ ፈራለሁ፤
መቼም ሰው አይደለሁ!

ስሜትና ሀሳቤ፥አደብና ቀልቤ፤
ስክነቴን ሸክፈው
ሰቀቀን ሰዷቸው፥እርቀው ከበሬ፤
መልሶ ይወጋኛል
ለእምነቴ አለቅም፥የጭንቀቴን ፍሬ፤
የሞኝነት ነገር
"ባይችለውስ" ብዬ፥ፈጣሪን ጠርጥሬ...

አወይ ሰው መሆኔ!

አይ ፍርሃት፥
አይ ሸክም፥
አይ ጥረት፥
የህሊና ኡደት፥የመልፈስፈስ ዕዳ፤
ባይገባኝ ነው እንጂ
እምነቴ ቢጀግን
ግመል ጭንቄ ይሾልካል፥በመርፌ ቀዳዳ!

አብርሃም ፍቅሬ
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተለያዩ መፅሃፎችን ማግኘት ይችላሉ ።
Join በማለት የቀላቀሉ ና የተቀሩትን መፅሐፎች ያግኙ።
ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

Forward ማደረጋችሁን እንዳትረሱ!!!
2.4K viewsማሪያማዊት, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 21:47:08 አፍቃሪ – እና – ቅኔ
/ /
(የሰማይ – እና – የምድርአፍቃሪ)



ወለላሽን ያየ
ንፅ’ናሽ የሳበው
ፃ'ዳ ሊሆን ሽቶ
ወዳንቺ ተጠጋ ሊታይብሽ ጠርቶ –፤

* * * *

ከሰማያት መቅደስ
ከንግሥና ዓለሙ በቅኔው ያበደ

ከሕይወታት ባንዱ ቀን
በማህሌቱ ከብሮ ጥበብ የወለደ –፤


– እንደአማልክቱ –

በደመና ፈረስ
በቀስተ ደመና
የዘላለም ሐዲድ መጓዝ ቢቻለውም–፤


– እንደመናፍስቱ –

በአዕላፍ አክፋናት
መብረር ቢያሰኘውም
ባለባት እረግቶ ቅኔውን ይጠምቃል

መርማሪ ተማሪ
መዝሙሩን ዘማሪ
አዋቂ እስኪመጣ ሰማይ ቤት ይኖራል።


እናም.......

– – (እንዲህማለትያውቃል)– –

“ሰው ሰማይ ያህላል
ከሰማይ ይሰፋል
ከሰማይ ይጠልቃል
ባዲስ ቀን ማለዳ
ከልቡ ማህፀን ፀሐዩን ይወልዳል ---”


– (እንዲህም ያክላል) –

“--- ከረቂቅ መንፈሱ
ከህቱም ልቦናው
ቅኔ ነው መንገዱ የማይነጥፍ ወላጁ

ወደነፍሱ አርነት
እንደሕጻን ላህይ
እየተፈቀረ
ሃሰሳ እሱነቱን በሃሴት ወሳጁ ----”


ቅኔ ግን ይወርዳል..........
የሰማይን ዙፋን የነፍሱን መከዳ
የምድርን ከርሰ-ስምጥ የልቧን ግድግዳ

የሁለቱን ሕላዌ
አንድነት ተቃርኖ ለፍጥረት ያበስራል።

ባለምላሚ ለዛው
ውስጥ እየዳሰሰ
የሱነቱን ወይን
ጣ’ም የሰነቀውን ያንቆረቁረዋል።

* * * *

በሐምሌ ጨለማ
በሚባላ ጥቁረት
የደመናን ግግር
በፅናት ወልውለሽ

የፀደይን ሰማይ
ከነከዋክብቱ
ትጠሪያለሽ አሉ –፤

ትቢያ የለበሰ
ግሳንግስ ዘመኑ
መቀመቅ አዝቅጦት
የከረፋ ሁሉ

ያንቺ ስም ሲጠራ
ከፀሐይ ሰባት እጅ
ያበራል ይላሉ።

* * * *

ቅኔ ማለት ለሱ.....

የፈዘዘን ማድመቅ
የጎበጠን ማቅናት
የሞተን ቀዝቃዛ
ነፍስ ዘርቶ ማንሳት

– ሊመስለው ይችላል –፤


ቅኔ ማለት ለሱ......

የሰማይ ደመና
የቋጠረው መና
መሬት አረስርሶ–፤

የሞተን በስባሳ
የዘር ሕልውና
ማንሳት ይመስለዋል
ከጭቃ ለውሶ።


ቅኔ ማለት ለሱ.....

በስምሽ መሰላል
አዕላፍ መናፍስት ሲወጡ ሲወርዱ
በመውድስ ቃና በወረብ ሲያረግዱ

– ማየትይመስለዋል –፤


ቅኔ ማለት ለሱ......

ባይኖችሽ ውኃ ላይ
ኩልል ፍክት ብላ የታዘለች ተስፋ
አፍቃሪ ተመልካች
መፅናናትን ሽቶ የሚልሳት ጤዛ

– ይመስለው ይሆናል። –

ቅኔ ግን ይወርዳል
ባለምላሚ ለዛው ውስጥን ይዳስሳል።

* * * *

ደግሞም ሌላ መልኩ እንዲህ ይነግረዋል፡፡
ካፈር ያቦካዋል፡፡

አፈር ሆኖ ቆሞ
አፈር ሆኖ ስቆ
አፈር ሆኖ ለቅሶ
እንዲያልፍ ይነግረዋል።

ካ’ለም ተበጅቶ
ካ’ለም ስም አግኝቶ
እንደትኩስ ወላድ ድያፈር ቅኔ አግቶ

ምድር እሱነቱን
በውኃ እያላቆጠ በእሳት አያጋመ
በጋላቢ ነፋስ እያስገመገመ

.........እስከኖረ ድረስ.........

ያለሚቱ ማበድ የጨርቅ መጣሏ
ካለፈች በኋላ
ተታርቃ ከቀልቧ እብደቷን ማውለቋ

እሱን መች ሊጨንቀው -!?
መች ግድ ሊሰጠው –!?

ስታብድ አብሮ ያብዳል፡፡

ከእብደታት ባንዱ ቀን
ውቧን ቆንጆይቱን አቅፎ ይስማታል
ወ’ዶ ያነግሣታል፡፡
ስትኖር አብሮ ኖሮ ስታልፍ አብሮ ያልፋል።

* * * *

ሕይወት ማለት ለሱ....
የቅኔ ሰንሰለት
የወለደው ሀሴት
መሆኑን ያውቀዋል

ከሰማይ ከምድር ሲያስሰው ይኖራል–፤


ሕይወትንም ቅኔ––ቅኔንም ሕይወት ነው
ሙሾንም እልልታ––እልልታንም ሙሾ
ዜማውንም ዝርው––ዝሩውንም ዜማ
ገሃዱንም ምስጢር––ምስጢሩንም ገሃድ

ቅኔ እንዲህ ነው ይላል
እንዲህ ይመስለዋል፡፡

* * * *

ስምሽን ይጣራል
ለዛሽን ያውቀዋል፡፡

የቁጣውን ፈሳሽ
የጭራቅነቱን

የንዴቱን ሀሞት
የገዳይ ምሬቱን

ያውሬነት ጃኖውን
በለስላሳ ዕይታሽ ከላዩ ላይ ገፍፎ
አክሊል ይቀዳጃል ብፅ’ናን ታቅፎ።

ስላንቺ በማለም
መቅደሱን ባሪቲ በብርጉድ አፅድቶ
አዳፋ ዘመኑን
በእንዶድ አንጨፍጭፎ ወልውሎና አቃንቶ

ከማንነትሽ ላይ
ራሱን ቀምሮ ከነፍስ ሽሊገባ
ከቅድስናሽ ላይ መክሊቱን ሊጠባ–፤

መርማሪን ሳይፈልግ
ተማሪን ሳይጠይቅ

በጫነው ደመና – በአማልክት ኩራት
ክንፉን እያማታ – በመናፍስት ፅናት
ከፀረ - አርያም –ከሰማይ ወረደ፡፡


ካፈር ህልውናው ፍቅር እያነደደ
ቅኔ እየጠመቀ እውን እየወለደ
በሕይወት መንኮራኩር
ከምድር ራሱ ጋር ወደሰማይ ሄደ።


ዋ!! ቅኔ - - ዋ!! ፍቺ
በሰማይ አፍቃሪ በምድር ተወለደ፡፡

ዋ!! ምስጢር - - ዋ!! ሕይወት
በምድር አፍቃሪ ወደሰማይ ሄደ።



(ዮሐንስ ሀብተማርያም)

ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተለያዩ መፅሃፎችን ማግኘት ይችላሉ ።
Join በማለት የቀላቀሉ ና የተቀሩትን መፅሐፎች ያግኙ።
ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

Forward ማደረጋችሁን እንዳትረሱ!!!
1.9K viewsማሪያማዊት, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 22:10:07 አብረን ዝም እንበል

ከሰው መንጋ እንገንጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል
ምነው አዋሽ ማዶ ቆቃ
የሸለቆ ግርጌ ሸሽተን
የቆቃን ሰቆቃ ሰምተን
ሲቃውን ሲሰብቀው አይተን
ሰቀቀኑን ተወያይተን
የምሽት ጀንበር ቢውጠን
ውሃ አንደ ዱታ ሲተምም
በድን ሸለቆ ሲናገር
ሰማያዊ ፈረስ ተጭኖ
ከአጥናፍ አጥናፍ ሲንደረደር
ሲያስጉተመትም ሲያስገመግም
በአይነ ህሊና ለመመስከር
ሳንጨነቅ ሳንገደብ
ለማንም ምንም ሳናዋይ
ሳንናገር ሳንጋገር
ካይንሽ ከልብሽ ከልቤ
አዋሽ ማዶ አብረን እንብራር
አዋሽ ማዶ አብረን እንውረድ
አጉል ነው ብለን ሳንፈርድ
ድንቅም ነው ሳንል ሳንወድ
ዝም ብለን አብረን ብንወርድ
ከሰው መንጋ ተለይተን
ከጠረኑ ተነጥለን
ከጉምጉምታው ተገንጥለን
ከኳኳታው ብንከለል
ከላንቃው ከድምፁ ሸሽተን
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
በቆይታ በፀጥታ ዝም ብለን
አብረን ዝም እንበል
መቼም አይሆንም ካልሽ ቅሪ
ግድ የለም አትገደሪ
ልቦናሽ በመተረልሽ
ባሳደረብሽ እደሪ
ተስፋ መቀነን ነው መቼም
የሰው ልብ አይችለው የለም
ብቻ ዳግመኛ ሞት ሳንሞት
አዲስ ቀን ሳይጨልምብን
ድፍን ደመና ሳይቋጥር
ክረምት ውጅት ሳይወርድብን
ኮከባችንን ሳንጠራ
ሳንቆጥርባት ሳትቆጥርብን
ሞራችንን ሳናስነብብ
ሳናሳያት ሳታይብን
ጨረቃን መስክሪ ሳንል
ሳናውቅባት ሳታውቅብን
አዋሽ ማዶ ቆቃ በረን
እባክሽ ጀንበር ትጥለቅብን
ውሃ እንደ ዱታ ሲተምም
በድን ሸለቆ ሲናገር
በሰማይ ፈረስ ተጭኖ
ከአጥናፍ አጥናፍ ሲንደረደር
ሲያስጉተመትም ሲያስገመግም
በአይነ ህሊና ለመመስከር
ሳንጨነቅ ሳንገደብ
ለማንም ምንም ሳናዋይ
ሳንናገር ሳንጋገር
ካይንሽ ከልብሽ ከልቤ
አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር
ከሰው ኳኳታ እንነጠል
ላንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
873 viewsማሪያማዊት, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 20:53:55 ሹም ሽር
"""""""""""
አንቺ እቴ ፔንዱለም
ፌዝና የምርሽ የተደቃቀለ፤
እዚህ ሲሉሽ እዛ
ነፍስሽና ስጋሽ ሁሌ እየዋለለ፤
በውበትሽ ግርማ
አፍቃሪ ከጉያሽ ሲገባ እየዋለ፤
ልቡ እየቀለለ፥
ሰርክ እየማለለ...
በሀሰት ግብርሽ ላይ
ሀቂቃዊ ፍቅሩን ገምዶና ጠቅልሎ፤
ስንቱ አዳም መሰለሽ
በዥዋዥዌሽ ክር የሞተው ተሰቅሎ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ለሌሎች ምርጥ ግጥሞች join በሉ....


ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

ይቃላቀሉ ጥበብን ያትርፉ!!!
1.0K viewsማሪያማዊት, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 22:18:41 ብቻ አንተ ተቀመጥ



በለስ ባታፈራ
በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይል ጎራ

የት ይደርሳል ያሉት
የናፈቁት ዝናብ
ደመና ላይ ቢቀር እንዲያው እንዳቅራራ

ብቻ አንተ ተቀመጥ!!

ዘመኑን አይተሃል –!?

መሪው ላድር ባዩ ተግቶ የሚሠራ

አድርባይ በግፉ
በሲሾም ያልበላ
ሲሻር ይቆጨዋል በግለ ፉከራ

ለጥቅም አደግድጎ
በግራ መዳፉ ለደሃ ‘ማይራራ።

ደሃ በጭንቅ ዕጣው
እግዜሩን
መንግሥቱን
አለቃ --- ምንዝሩን ሁሉን እሚፈራ።

ከጭንቅ አዝመራው ላይ
ያለማወቅ ምርቱን ከግርዱ ሳይለያይ
ከነፍሱ ጎተራ አጭቆ የሚሰቃይ

ይደርስለት ያጣ
ይፈውሰው ያጣ
ይመረኮዝበት – ይደገፈው ያጣ

ሲያሮጠው የሚኖር የግራቸው ሴራ
ሆኖልህ አርፎታል የሸራቸው ሥራ።

ሲሮጡ ለኖሩት ዓላማ-ቢስ ሕይወት
“እናውቅልሃለን” ብለው አዋክበውት

ሮጦ ‘ማይሸሻቸው
ሰማዩም መሬቱም ሆነው አግተውት

ቀኙንም ግራውን
‘ፊቱን ኋላውን
በስውር ስልታቸው ጠንቅቀው ሠርተውት

ሕዝብህን ከ’በውት
በሕቡዕ አስረውት
መከራ እንደ ስኳር አጣፍጠው እያስላሱት
ግፍ እያሳፈሱት

እጅ አዙር ስማቸው አልጠራልህ ቢለው
ሞረሽ አርጩሜያቸው
ስውር ሰንበር ሰ’ቶት አልገለጥ ቢለው

‘ሮጦ መደህየት
‘ሮጦ ማጣትን
‘ሮጦ መመስከን
‘ሮጦ መራብን
መቼም እንደዳይለቀው በጭንብል ሰ’ተውት
ላምላኩ ተማፅኖ እንዲያቀርብ ዳርገውት

– እንዲህ እያለልህ ነው–
“ወይ እንጀራ ስጠኝ ወይ ዕድሌን ባርከው
ሆዴ ተቀደደ ሲርበኝ የማ’ከው…”

እነሱ ሲያስሮጡት እሱ ሲሮጥ ኖሮ

ትርፉን ሊያይ ዞር ሲል
አላባው ቢመክን ቢሆንበት ዜሮ

ተጣልቶ አረፈልህ ሕዝቡ ከ’ግዜር ጋራ

በሌላ እንዳይመስልህ
ሆዱ በናፈቀው በግማሽ እንጀራ

“ሆድ የለህ – አትበላው!
ስጠኝ” ብሎ አረፈው።

ፍረድ
ፍረድ
ፍረድ
ካልሆነልህ ውረድ
እጦት ሲያደባየን ሰማይ ሆነህ አትቀልድ።

ችግር ባስታጠቀው
አቅመ-ቢስ ቁጣ መቻሉ ሰልስላ

ሕሊናውም ከስላ
ሰውነቱ ቀልላ

አበሳ ቢያሳዩት
ፍዳ ቢያስቆጥሩት ባሳር ቢያራውጡት
ይችለውን ፈርቶ
ካይችለው ተናንቆ ከሰማይ ተጣላ።

ዘመኑን አይተሃል -!?

ከፊትህ --- ከፊትህ
ፊት ፊቱን እያየ
አራት-ዓይና እግሩን
እያፈራረቀ
አንዴ እየተከለ አንዴ እየነቀለ

ታሪኩን ሊሠራት
ኩሎ ሲያበጃጃት የሄደው የት አለ –!?
ከቀደሙት ወገን
እነማን ላይ ደርሶ ማንንስ አከለ!?

የገዛ እሱነቱን
ራሱ ውስጥ ተክሎ
በራስ መረዳት ውስጥ
የጠለለ ራሱን መቼና እንዴት ሳለ –!?

ዘመኑን አህተሃል –!?

ለመማር ‘ሩጫ
ለመብላት
ለመልበስ
ለመሥራት ‘ሩጫ

በሥራ ላይ ሥራ
በመማር ላይ ትምህርት
በማደግ ላይ ማደግ

ክንፍ ባበቀለ
ተክነፍናፊ እግር ለመሮጥ ማደግደግ
በጥድፈት መመንደግ።

ለመራገጥ ጥድፈት
ለመቃወም ቅስፈት

በጎጥ ለመቧደን
ማንም የማይቀድመን –፤

ያገር ዕጣን ጥለን
የግልን ለማፍካት ተንኮል የሚያከንፈን።

በጥድፈት ተወልደን
ወዲያው ተመንድገን
እዚያው ቀንድ አውጥተን
ባፍታ ሞት የሚያንቀን
ተነስ ‘ሩጥ ባዮች አትስማን እኛ ነን።

በጎች ከበረቱ ጣጥለው ቢጠፉ
ላሞች ከጋጣቸው ተማ’ረው ቢከንፉ

ላስመሳይ ጩልሌ
ለማንም ማካለብ
ዛቻ ማስፈራሪያ እግርህን ሳትሰጥ

ብቻ አንተ ተቀመጥ።

በተጎለተበት ስር ሰደደ ቢሉህ
ያልተራመደበት
እግሩ እንኳ ተማ’ሮ ተሰለበ ቢሉህ

ለማንም ማካለብ
ዛቻ ማስፈራሪያ
የእግርህን ቀልብያ በስህተት ሳትሰጥ

ብቻ አንተ ተቀመጥ።

ዘመኑን አይተሃል –!?

ከሰው መሃል ቆሞ
በሰው ተደምሞ

ሰው እየናፈቀው፤
ካ’ባይ ከፏፏቴው ከስምጡ ተደፍቆ
ዕንባውን የሚያፈስስ በኩሬ ተጨንቆ

የቱን ታድሎ ነው -- የቱንስ ተረግሞ –!?

የምትለው ‘ሯጭ
ካፍ – እስከ – ገደፍ ነው።

የገዛ ሥጋው ላይ ሀሰትን ጎዝጉዞ
የጎመዘዘ ሐቅ ነገው ላይ አርግዞ

ሥጋው ትል አብቅሎ
ሐቁ ህ…ቅ እያለው
የሚኖር ሁላ ነው ተነስ ሂድ የሚልህ።
ከቁና ትርፍ ነው ትንሽ እንዳይመስልህ።

ዘመኑን አይተሃል –!?

በዚህች እንዝርት ዓለም
እፍኝ በማትሞላ በቁንፅል ዕድሜ ትልም

በመሾር ተጋጭተን
በመጦዝ ተካርረን
ለእርቅ ኤሊ ሆነን
ለጠብ ሲላ ስንሆን ከሰይጣን አስንቀን

ስንት ጊዜ ገድለን
ስንተዜስ ሞተናል
ከ… እስከ የሌለው ስንተዜስ ስንት ነው -!?
ቆመን ለማናውቀው ተመኑስ መልስ ነው –!?

ዘመኑን አይተሃል –!?

በዚች በተሰቅሎ በብካይ ዓለም ላይ
ቁጥሩ የሚያስቸግር ሳይኖር አለሁኝ ባይ

እሮሮ ተግቶ
ቅኔው ግፍ ተቀኝቶ

ተንሳፋፊ አላፊ
የሚፀንስ ስቃይ እንደ አሸን ፈልቶ
የጥድፈት ገዳሙን ነፍሱ ላይ ገንብቶ

የሚኖር በርክቶ
ብካይ ዕድሜ አብክቶ
ፅልመት ውስጥ ሻግቶ

ሲናፍቅ ቢኖርም እፎይ መቼ ይምጣ
ሕይወት እንዴት ትፍካ ፀሐይ ከየት ትውጣ!?

“ወተት ተንጦ ነው ቅቤ የሚወጣው
ቅቤ ተገፍቶ ነው
ካናት የሚደርሰው” ያሉትን አትስማ –፤

“ሂድ” ሲሉህ አትሂድ
“ተነስ ሲሉህ አትቁም
ለጎምዛዥ ደስታቸው
ሳትሆን አካላቢ ቁጭ በል ሳታቅማማ።

ከመቀመጥ ብሉይ
ከመጎለት ሐዲስ
አውጣጥተው የሠሩት
ለመጪ ያቀበሉት
የቁጭ ባይ አዋልድ አልተገኘምና
የተቀማጭ ድርሳን ምንም የለምና።

ከተራራህ ጫፍ ላይ ቁጭ ያልከውን አንተን
ሜዳ ገደልህን
ተራራ ሰርጥህን

‘ሩጥ – ውረድ – ውጣ --- አትቀመጥ ሲሉህ

የረጋ ነፍስህን
ዓረና ሕሊናህን በረብሻ እንዳትንጥ
ለመሄድ እንዳትቋምጥ
ብቻ አንተ ተቀመጥ!!!

ምክንያቱም. . .
በጥድፈት ተወልደው
ወዲያው ተመንድገው
እዚያው ቀንድ አውጥተው
ያፍታ ሞት አንቋቸው ሕይወት የራቃቸው
ተነስ ‘ሩጥ ባዮች
እነርሱ‘ኮ ናቸው።

እናም. . .
በለስ ባታፈራ
በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይል ጎራ

የት ይደርሳል ያሉት
የናፈቁት ዝናብ
ደመና ላይ ቢቀር እንዲያው እንዳቅራራ

ላስመሳይ ጩልሌ
የእግርህን ቀልብያ ላምንም ሳትሰጥ

ብቻ አንተ ተቀመጥ!!!


( #ዮሐንስ_ሀብተማሪያም)
ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

ይቃላቀሉ ጥበብን ያትርፉ!!!
1.4K viewsማሪያማዊት, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 22:42:55 አድዋ!!!

የአፍሪካ ኩራት፣
የምዕራባዊያን እራስ ምታት፣
አድዋ!
የኢትዮጵያ ታላቅነት፣
የሙሉ አፍሪካ ነፃነት፣
የጥቁር ህዝቦች ጀግንነት፣
አድዋ!

የሰሜን ምዕራብ፣
የምስራቅ ደቡብ፣
የአንድነት ድባብ፣
አድዋዋዋዋ!

ዛሬ ላይ ነፃ የመሄኔ
ሚስጥር አድዋ!
ጀግኖች የተሰውሉሽ
የነፃነት ምድር ኢትዮጵያ!

እሄው ደረሰ
የጀግኖችሽ መታሰቢያ፣
የምራባዊያን አንገት መድፊያ፣
አድዋ!

ስማኝማ ወንድሜ
ስሚኝማ እህቴ
ቃል ባላገኝ አድዋን እምገልፅበት፣
የአንደበቴን የስሜቴን
ትንሽ ቢሆን ልናገርለት፣

አድዋ እኮ ማለት፣
ጀግኖች ለሃገራቸው
ደማቸውን ያፈሰሱለት፣
ለእምየ እናት ሀገሬ
መሰዋትነት የሆኑላት፣
እጅ አንሰጥም፣
ባሪያ አንሆንም፣
ኢትዮጵያን አላስደፍርም፣
ብለው
መስዋትነት የተከፈለበት
ቀን እኮ ነው አድዋ ማለት!
ንፁሃን ለሃገራቸው
ደማቸውን ያፈሰሱበት፣
ምዕራባውያንን አንገት ያስደፉበት፣
ነፃነታቸውን ያስከበሩበት፣
ከራሳቸው አልፈው አፍሪካን ነፃ ያወጡበት፣
አድዋ!

አድዋ እኮ ማለት በኔ የማይገለፅ
የኢትይኦጵያ ኩራት፣
የአፍሪካ አንድነት፣
የምዕራባውያን ሽንፈት፣
አድዋ!
የሴት ጀግንነት የታየበት፣
ዛሬ ላይ የመቆምህ ሚስጥር
አድዋ

አድዋ
ዛሬ ላይ በነፃነት እንድንቆም
መስዋትነት የተከፈለበት፣
አድዋ!
ለሃገራቸው ነፃነት፣
ጀግኖች የሞቱበት፣
እራሳቸውን የሰውበት፣
የብዙሃን ጀግኖች
ደም የፈሰሰበት፣
አድዋ!

አድዋ!
የኢትዮጵያ ኩራት፣
የአለም ድንቃ ድንቅ ትምህርት፣
ኢትይኦጵያ ከራሷ አልፋ
አፍሪካን ነፃ ያወጣችበት፣
ቀን እኮ ነው አድዋ ማለት
ጀግኖች ሃገራቸውን ያስከበሩበት
እራሳቸው ነፃ ወተው
አፍሪካን ከባርነት ያወጡበት
አድዋ !
አድዋ!
ዋ!
ዋ!

ቃል የማይገኝለት
እረቂቅ ሚስጥር አድዋ!
...
አባቶቻችን በደምም ያቆዩንን ሃገር እባካችሁ አንከፋፍላት በፍቅር እንኑን ከኛ አልፋ ለሌላም ትበቃለች ኢትይኦጵያ ለዘላለም ተትኑር! ታሪክ አውሪታ ሳይሆን ከአቤቶቻችን ተምረን ታሪክ ሰሪታ እንሁን! ቀዳሚዎች ነን ቀዳሚዎች ሁነን አንቀጥል።
ፍቅር
ሰላም
አንድነትን ያዝዝልን!
እንኳን ለ126ኛው የኢትዮጵያ ኩራት የአፍሪካ ነፃነት ለሆነው የአድዋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።



ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share
Join&share

ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

ይቃላቀሉ ጥበብን ያትርፉ!!!
3.1K viewsማሪያማዊት, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 12:02:52 ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተለያዩ መፅሃፎችን ማግኘት ይችላሉ ።
Join በማለት የቀላቀሉ ና የተቀሩትን መፅሐፎች ያግኙ።
ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

Forward ማደረጋችሁን እንዳትረሱ!!!
710 viewsማሪያማዊት, edited  09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 22:22:30
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተለያዩ መፅሃፎችን ማግኘት ይችላሉ ።
Join በማለት የቀላቀሉ ና የተቀሩትን መፅሐፎች ያግኙ።
ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234
@yopbirnawereket1234

Forward ማደረጋችሁን እንዳትረሱ!!!
3.8K viewsማሪያማዊት, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-09 23:43:41 በፍቅር ስም

ደራሲ - አለማየሁ ገላጋይ
የገፅ ብዛት:-219
መሉ መፅሐፉን በጥራት
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተለያዩ መፅሃፎችን ማግኘት ይችላሉ ።

Join በማለት የቀላቀሉ ና የተቀሩትን መፅሐፎች ያግኙ።

ዮጵ ብዕርና ወረቀት
@yopbirnawereket1234
2.7K viewsማሪያማዊት, edited  20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ