Get Mystery Box with random crypto!

'ቃሌ ቃል ባይመስላት ስቀርባት ብትርቅም ለወጉ ነው እንጂ ጠልታኝ እኮ አታውቅም ' ብዬ ስነግራቸው | 👑 አዳም ረታ 👑

"ቃሌ ቃል ባይመስላት ስቀርባት ብትርቅም
ለወጉ ነው እንጂ ጠልታኝ እኮ አታውቅም
"
ብዬ ስነግራቸው ሰዎች ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
በማላቀው ምክንያት
እስቲ ዞረህ እያት
ሲሉኝ አያታለው
መች መልስ አገኛለው
ምንድነው? እላለው
መልሰው ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
"ስከተላት ብትሸሽ ስቀርባት ብትርቅም
ኮርታብኝ ነው እንጂ
ጠልታኝ እኮ አታውቅም "
የሚል ቃል ሲወጣኝ ሳቃቸው ይገናል
አሁን በእናና ሞት ይሄንን ማን ያምናል
እነሱ ያሳቃቸው
እኔ ያስተዋልኩትን መሆኑን ባላውቅም
ጥርሷ ይርገፍና
አብረን ባለን ጊዜ ስቃልኝ አታውቅም

*------------------*

(ሚኪያስ ፈይሣ)

@AdamuReta
@AdamuReta
@AdamuReta