Get Mystery Box with random crypto!

#ላጣሽ_አቅም_አጣሁ ዓለማዊ ልቤ፥ለበሰልሽ ዳባ፥ምናኔ ተመኘ በናቴ ቀብር ላይ፥ የጠፋብኝ እንባ፥ | 👑 አዳም ረታ 👑

#ላጣሽ_አቅም_አጣሁ

ዓለማዊ ልቤ፥ለበሰልሽ ዳባ፥ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ፥ የጠፋብኝ እንባ፥ ፊቴ ላይ ተገኘ

ላጣሽ አቅም አጣሁ፤
የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን ገድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብየ ነበር፥ ቄስ አንዳስተማረኝ
አንቺን አጣሁ ብየ፥ ማመኑ ቸገረህ

ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤

ልረሳሽ አልቻልኩም፥ ልረሳሽ እልና
ፊትሽን አትመሽ፥ በየብስ በደመና
ከንፈርሽ ያውና
ፈገግታሽ ያውና
ውብ ዓይንሽ ያውና።

@isrik
@AdamuReta