Get Mystery Box with random crypto!

~ ዘካቱል ፊጥር ~ ክፍል አራት/ የመጨረሻው ክፍል ① ዘካቱል ፊጥር የእህሉን ዋጋ መ | أبو سعيد

~ ዘካቱል ፊጥር ~
ክፍል አራት/ የመጨረሻው ክፍል
① ዘካቱል ፊጥር የእህሉን ዋጋ መስጠት ይቻላል???

ዘካቱል ፊጥር የእህሉን ዋጋ መስጠትን አስመልክቶ በዑለሞች መካከል ይቻላል እና አይቻልም የሚሉ አቋሞች ተንፀባርቀዋል።ነገር ግን የአብዛሃኛዎቹ ዑለሞች( የኢማሙ ማሊክ፣ሻፊዒይ፣አሕመድ....) አቋምና መረጃም የሚደግፈው አስገዳጅ ነገር እስካልተከሰተ ድረስ ዘካተል ፊጥር የእህሉን ዋጋ መስጠት አይቻልም የሚለው የዑለሞች አቋም ነው።በዚህ መሰረት ዘካችንን መስጠት ያለብን ከዚህ በፊት ያሉት ክፍሎች እንዳየነው ገንዘቡን ሳይሆን እህሉን ነው።ዘካውን የምንሰጠው ሰው ብሩን ከፈለገ ሽጦ መጠቀም ይችላል።
② ዘካውን እንዲሰጥልን ሰውን መወከል ይቻላልን???
አንድ ሰው ዘካተል ፊጥሩን መስጠት ሳይመቸው ቀርቶ ዘካውን እንዲሰጥለት ሌላ ሰውን ቢወክል ምንም ችግር የለውም።እንዲሁም ከሰዎች ዘካተል ፊጥራቸውን ተቀብለው ለሚስኪኖች የሚያከፋፍሉ ተቋሞች ወይም ማህበራት ካሉ፤እንዲሁም ታማኝና ዘካውን ለሚስኪኖች ከሶላት በፊት የሚያከፋፍሉ ከሆኑ ዘካችንን ለነሱ መስጠት እንችላለን።በተጨማሪም እነዚህ ተቋማት ወይም ማህበራት እህሉን ገዝተው የሚሰጡልን ከሆነ ለነሱ እህሉን የሚገዙበት ገንዘብ መስጠት እንችላለን።ከላይ ዋጋውን መስጠት አይቻልም የተባለው ቀጥታ ለሚስኪኑ ገንዘቡን መስጠት ነው።አሁን ግን የተፈቀደ ነው ያልነው እኛ ለተቋማቱ ገንዘቡን እንሰጣለን፤ ተቋማቱ ደሞ እህል ገዝተው ለመሳኪኖች ማከፋፈላቸውን ነው።
③ ዘካቱል ፊጥራችንን የት ነው ማውጣት ያለብን???
ዘካችንን ማውጣት ያለብን የፆምንበት ቦታ(ሀገር) ላይ ነው።ነገር ግን ይህንን ማድረግ ካልቻልን ሌላ ቦታ ላይ ያለን አካል ዘካችንን እንዲሰጥልን መወከል እንችላለን።ለምሳሌ ከቤተሰብ እርቀው የሚማሩ ተማሪዎች ከቻሉ እዛው የፆሙበት ቦታ ላይ ዘካቸውን ያወጣሉ፤ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን ቤተሰባቸው ቢያወጣላቸው ምንም ችግር የለውም።
④የብዙ ሰዎችን ዘካ ሰብስበን ለ አንድ ሚስኪን መስጠት እንዴት ነው????
ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ፦ ለምሳሌ የአንድ ቤተሰብን ዘካ ሰብስበን ለአንድ ሚስኪን መስጠት ምንም ችግር እንደሌለው ዑለሞች አስቀምጠዋል።ስለዚህ 3 የቤተሰብ አባላት ቢኖሩን የግድ ለተለያዩ ሶስት ሚስኪኖች መሰጠት አለበት አይባልም።

አልሓምዱሊላህ ፅሁፌን እዚህ ላይ ጨረስኩ


★ "ዘካቱል ፊጥር "~~ በሚለው ፅሁፌ
ሸርሑ አልሙምቲዕ( በሰፊው)
ተማሙ አልሚና(በተወሰነ)
አል ሙጝኒ(በስሱ)
እንደ ምንጭነት ተጠቅሚያለው የበለጠ ማጥናት የፈለገ እነዚህንና ሌሎችን ኩቱቦች በደንብ ማየት ይችላል፤በአሏህ ፍቃድ በርዕሱም ላይ ሰፋ ያለ ግንዛቤንም ይሸምታል።
~ ወሏሁ ኣዕለም ~~~
ኢንሻአሏህ የረሳሁት ነገር ካለ እመለሳለሁ