Get Mystery Box with random crypto!

'የትንሳኤ ትምሕርት' ባለፍ ነው በአብይ ፆም የመጨረሻ ሳምንት ሕማማት ይህም ትንሳኤን ከማ | አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

"የትንሳኤ ትምሕርት"

ባለፍ ነው በአብይ ፆም የመጨረሻ ሳምንት ሕማማት ይህም ትንሳኤን ከማየታቸው በፈት ምዕመናን የክርስቶስን ሕማማት በመሳተፍ ያስቡታል እዕለተ አርብን ከዕለተ ዕሑድ ቀድመው በማለፍ ተግባራዊ የሆነ የክርስቶስን መከራ እያሰቡት ሕመሙ ሕመማቸው ቢሆን ሊሸከሙት እንደማይችሉ እያሰቡ ሁሉ ቻይነቱን በእንባ ይገልፁታል ። ሰው በሕይወቱ ብርሃንን ከወደደ ሌት ጨለማንም ማለፍ ማየት አለበት ። ሙላቶቻችን ሚመዘኑት በሞላናቸው ጎዶሎዎች መጠን ነው ። ይህ ደግም የክርስቶስ የትንሳኤ እየተከበረ ያለበት ሳምንት እንደመሆኑ አምላክ በመሞቱ የማይሞተው ሞተ እያልን ብንደነቅም ከዚህ በላይ ግን ሞትን አሸንፎ በነሳቱ ይበልጥ እንደነቃለን ። ሰው በህይወቱ ውስጥ እንደሞት የከበደ መከራ ቢገጥመውም እንደ ብርሃን ያለ ደማቅ ህይወት እንደሚጠብቀው እና እንደሚያልፈው አምኖ ለበጎ የሆነውን የመከራውን ጊዜ አምላኩን ያመስግን ።


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ