Get Mystery Box with random crypto!

አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ abune_abib — አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ abune_abib — አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
የሰርጥ አድራሻ: @abune_abib
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123
የሰርጥ መግለጫ

❤ ክርስቶስ ሆይ ሕይወቴን ላንተ ❤

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-27 09:22:17 የፋሲካሰላምታአሰጣጥትርጉም

ምሕዛል ወቃለ ባሕ ዘትንሣኤ Paschal troparion & Greeting

(ለትንሣኤ የተቆነጠረ ሐሳብ)

ሀገርኛው የዘውትር ሰላምታችን ሰላም ላንተ ይኹን ጠላትኽን ያውድቅ ቢሰኛኽን ያርቅ! በሚል መነሻ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚታከልበት ምኞት መግለጫና ምስጋና ማቅረቢያ ነው!

የሰላምታው መንገድ ደግሞ በሦስት ሂደት (በቃል በእጅና በአንገት) የሚከወን ነው።


መጨባበጥ (ተራክቦተ እድ ፣ ፅብጠት፣ ተጻብሖ) ☞ በእጅ የሚፈጸም ፦ በመጨባበጥ handshake በመተቃቀፍ hugging አልያም በጉንጭ በመሳሳም cheek kissing ይፈጸም የነበረውን በቀደሙቱ ዘንድ “አምኃ ቅድሳት” holy kiss & kiss of peace ⇨ ἐν ἁγίω φιλήματι, και φιλί της ειρήνης እየተባለ የሚጠራው መንገድ ነው!

በዚኽ አጋጣሚ በወቅቱ ጉዳይ መጨባበጥ መተቃቀፍና መሳሳም ለወረርሽቹ በፍጥነት መዛመት ምክንያት መሆናቸውን አውቀን #አካላዊፈቀቅታ|ን በመጠበቅ በበሽታው የምናልፍ ሳንሆን በሽታውን የምናሳልፍ ነገንም የምናይ እንድንሆን በተከታዮቹ መንገዶች ሰላምታ የምንለዋወጥ ይሁን!


"እጅ መነሳሳት" (እማኄ) ☞ ባንገት፣ በወገብና በጕልበት የሚፈጸም ነው


የሰላምታ ቃል መለዋወጥ (በቃለ ተአምኆ) ሰላምታ በንግግር በመለዋወጥ የሚፈጸም ዋናዎቹ ናቸው!

ወደ ተቆነጠረው ሐሳብ እንለፍ ተዝካረ ትንሣኤው በሚታሰብበት ዐባይ ፋሲካ ፶ ዕለት በቤተክርስቲያናችን የሚፈጸም የተለየ ሰላምታና የዜማ ድጋም አመላለስ አለ

የጌታችን ተዝካረ ትንሣኤ በቤተክርስቲያናችን ሰፊ ቦታና ትርጉም ያለው በመሆኑ የዓመት ሢሦው (⅓) ነገረ ፋሲካን የሚያስታውስ ነው (የፋሲካ ጾም ⁵⁵ እና ዘመነ ትንሣኤ⁵⁰)

በቅዳሴው መግቢያ መስዋእቱ ከቤተልሔም ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ ከትንሳኤው እስከ በዓለ ፶ ጊዜው የተለየ መሆኑን ለማሳወቅ "እመቦ ብእሲ… " በሚለው መግቢያ ፈንታ "ሃሌ ሉያ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪነ ⇨ ሃሌ ሉያ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት፡፡" የሚል መልእክት በዜማ ይደርሳል!

ከዚኽ ውጪ ምሕዛል ዘትንሣኤ ወይም «የፋሲካ አመላለስ» ያልነው Paschal troparion እና ቃለ ባሕ ዘትንሣኤ «የፋሲካ ሰላምታ» ያልነው Paschal Greeting ከወትሮው በተለየ መንገድ ይፈጸማል። ሁለቱም በልሳነ ጽርእ (ግሪክ) #ክሪስቶስ_አኔስቲ / Χριστὸς ἀνέστη እየተባለ ይጠራል

① #ምሕዛል_ዘትንሣኤ Paschal troparion የፋሲካ አመላለስ

በእርግጥ ምሕዛል አልያም ምስትሕዛል የሚባለው በድጓው ሊቃውንቱ የሚያስተዛዝሉት ዜማ ድጋም ሲሆን መነሻውን ድጓ ያደረገው በቅዳሴው ክፍል የምናገኘው ይኽ የተዝካረ ትንሣኤ ምስትሕዛል፦
«ህየንተ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት እምትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ » በሚል የገባ ሦስት ጊዜ ደጋግመን በመቀባበል የምናደርሰው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ "

በሌሎች ምሥራቃውያን (Eastern ) እና ጽባሓውያን (Orientals) ዘንድም በእጅጉ የተለመደ ነው!

በግሪክ ፓስካል ትሮፓርዮን አልያም χριστος ανεστη የሚባል በዜማ የሚደርስና የዘመነ ሐዋርያት ጭምር ጥንታዊ መገለጫ አለው ተብሎ የሚታመን ነው።

Χριστὸς ἀνέστη ἐκ νεκρῶν,

θανάτῳ θάνατον πατήσας,

καὶ τοῖς ἐν τοῖς μνήμασι,

ζωὴν χαρισάμενος!

የንባባዊ ፍቺው አማርኛ ትየባ (transliteration) ደግሞ ይኽን ይመስላል!

ክርስቶስ አኔስቲ ኤክ ኔክሮኒ ፣ ታናቶ ታናቶን ፓቲሳስ፣ ኬቲስ ኤን ቲስ ሚ’መሲ፣ ዞይን ካሪዛሜኖስ

በትርጉሙም የእኛው " ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም ዕረፍተ ⇝ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሞቶ ሞትን አጠፋው በመቃብር ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ " ካለው ጋር አቻ ፍቺ አለው

Christ is risen from the dead, Trampling down death by death, And upon those in the tombs, Bestowing life!

② #ቃለባሕዘትንሣኤ Paschal Greeting «የፋሲካ ሰላምታ»

በሓ ወይም ባሕ የሚባለው የሰላምታ የቡራኬ ቃል ፍሥሓ ሰላም የሚለውን የሚገልጥ ነው!

በቤተክርስቲያናችን አበው መምህራንም ቅድመ ቃለ እግዚአብሔር ፣ ድኅረ ቃለ ቡራኬ ለ፶ው ዕለት ከምእመናን ጋር የሚለዋወጡት ሰላምታ ነው! ከዚያም አልፎ ምእመናንም ከምእመናን ጋር የትንሳኤውን የምሥራች ለማብሰርና መልካም ምኞት ለመግለጥ ያውሉታል።

አቀራረቡ በአመላለስ አገባብ የሚከወን ሲሆን ሰላምታ ሰጪና ሰላምታ ተቀባይ ይኽን ይለዋወጣሉ፤

በኢትዮጵያዊቷ የተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያናችም ከ6ኛው ምዕተ ዓመት አንስቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን መረጃዎች ይገልጣሉ። በቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ (ዘመወድስ) ውስጥ በፍታሕ ሊተ ሥር በመሪና ተመሪ የሚቀርብ ዛሬ ለፋሲካ ሰላምታ የምንገለገልበት የትንሣኤው ምስክርነት ቃል አለ። እንዲህ ይላል ፦

☞ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፣ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን ፣ አሠሮ ለሰይጣን ፣ አግዓዞ ለአዳም ፣ ሰላም ፣ እምይእዜሰ ፣ ይኩን ፣ ሰላም!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ፣ ሰይጣንን አሠረው፣ አዳምን ነጻ አወጣው ፣ ሰላም፣ ከዛሬ ጀምሮ ፣ ይሁን ፣ ሰላም

በመቀባበል እንዲህ ተጽፏል

☞ Christ is risen from the dead!
☜ By the highest power and authority!
☞ He chained Satan!
☜ Freed Adam!
☞ Peace!
☜ Henceforth!
☞ Is!
☜ Joy and Peace!

☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው፤ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ.....
See more
@ABUNE_ABIB
55 viewsብንያም በለጠ, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 09:21:15 ያሬዳውያን:
#ዘቅድስት፡፡
(መዝሙር፤ ምስባክ፣ ምንባባት፣ ወንጌል)

#መዝሙር_ዘቅድስት፤ግነዩ ለእግዚአብሔር
ሃሌ ሉያ(፭) ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ፤
ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ፤ /መዝ. ፻፬፥፩/
ሀቡ ስብሐተ ለስሙ፡፡ /መዝ. ፷፭፥፪/
አክብሩ ሰንበተ ተገብሩ ጽድቀ፤
ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት፤
ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሠራቂ፤/ማቴ.፮፥፲፱
ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ሐልዩ፤
ኀበ ሀሎ ክርስቶስ፡፡ /ማቴ. ፳፬፥፵፬/
ትርጕም፤ እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፤ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ፤ ለስሙም ክብር ስጡ፤ ሰንበትን አክብሩ፤ እውነትንም አድርጉ፡፡ ብልና ዝገት በማያጠፉት፣ ሌቦች ቆፍረው በማይሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፡፡ ክርስቶስ በሚኖርበት ቦታ ያለውን ክብር እያሰባችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፡፡


#እስመ ለዓለም ምሕረቱ
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ …፤
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ፤
ነአኵተከ ወንሴብሐከ፤ ለዘዓቀብከነ ወአብጻሕከነ፤
/ግነዩ …/ ወወሀብከነ ጾመ ቅድስተ
ከመ ናግርሮ ለሥጋነ፤
/ግነዩ …/ ወከመ ንትፋቀር በበይናቲነ
ወንኅድግ አበሳ ለቢጽነ፤
/ግነዩ …/ ይእዜኒ እግዚኦ ተራድአነ ሀበነ
ንትቀነይ ለከ ለነ፤ ለአግብርቲከ ወለአዕማቲከ፤
/ግነዩ …/ አብ ቀደሳ ወአልዓላ ለዕለተ ሰንበት፤
/ግነዩ …/ ኅብስተ እምሰማይ ፈኖከ ሎሙ
ከመ ይብልዑ ወይጽገቡ፤
/ግነዩ …/ በ፪ኤ ዓሣ ወበ፭ቱ ኅብስት
አጽገቦሙ ኢየሱስ ለ፶፻ት፤
/ግነዩ …/ ወሠርዓ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ
ውብውህ ሎቱ ይኅድግ ኃጢአተ፤
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ፨

#አራራይ፤
ሃሌ ሉያ፤ ለክርስቶስ ይደሉ ስብሐት፤
ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት፤
እግዚአ ለሰንበት ዘልማዱ ኂሩት፤
ሎቱ ስብሐት ለዘቀደሳ ለሰንበት፡፡

#ዕዝል፤
በወንጌል ኮነ ሕይወትነ፤
ሃሌ ሉያ(3)፤
ሰንበት ቅድስት ለውሉደ ሰብእ መድኀኒት፤
ለሙታን መንሥኢ፡፡

#ሰላም፤
ሰንበት ይእቲ ቅድስት ይእቲ፤
ሰንበት ተዓቢ እምኵሉ ዕለት እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤
ሰንበተ ሰንበታቲሁ ለውሉደ ሰብእ መድኀኒት፤
ጽዮን ቅድስት ሰላማዊት፤
ታስተርኢ እምርኁቅ ከመ ማኅቶት፡፡
#ምንባባት
፩ኛ.ተሰ ፬÷፩-፲፫፤ እግዚአብሔርን ደስ ልታሰኙ እንደሚገባችሁ እንመክራችኋለን፡፡/ቊ.1
፩ኛ.ጴጥ.፩÷፲፫፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጽ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ /ቊ.13/
የሐዋ. ሥራ ፲፥፲፯-፴፤እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኵስና የሚያፀይፍ ነው እንዳልል አሳየኝ፡፡ /ቊ.28/
#ምስባክ፤ መዝ. ፺፭÷፭
እግዚአብሔርሰ ሰማያት ገብረ፤
አሚነ ወሠናይት ቅድሜሁ፤
ቅዳሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ፡፡

(ትርጕም፤እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ፤ እምነትና በጎ ምግባርም በፊቱ ነው፤ ቅድሳትና የምስጋና ገናናነትም በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡)
#ወንጌል፤
ማቴ. ፮÷፲፮-፳፭፤
ሌቦች ቆፍረው በማይሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፡፡ /ቊ. ፳/)
#ቅዳሴ፤
ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ

መዝሙር ዘቅድስት
በ (፭/ር) ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ሀልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ።

ትርጉም፦

ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም ጥሩ ሥራውን ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙ ምስጋናን ስጡ/አቅርቡ ሰንበትን አክብሩ ጽድቅን ሥሩ ሌባ በማያገኘው ብል በማያጠፋው በሰማያት መዝገብን አከማቹ ክርስቶስ ባለበት ለመሆን በላይ ያለውን እያሰባችሁ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።

የዕለቱ ምስባክ፦

እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ፤
አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ፤
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ። መዝ ፺፭፥፭

ትርጉም፦

እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ፤
እምነትና በጎነት በፊቱ ናቸው፤
ቅድስና እና የክብር ገናንነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

ምሥጢር፦

እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ፈጠረ፤
ሃይማኖት ምግባር በፊቱ ነው አለ ምግባር ሃይማኖት የያዘ ሰውን ይወዳል፤
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ መመስገን ዓቢየ ስብሐት መባል ገንዘቡ ነው።n

መልእክት፦

ሰማይ ማለት ሥዕለ ማይ - የውኃ ንድፍ ማለት ነው አንድም ልዑል ማለት ነው። ቀለሙ/መልኩ ሰማያዊ ነው እጅግ ብሩህ ቢሆን ዐይን ይበዘብዝ ነበርና እጅግም ጨለማ ቢሆን ለዐይን ይከብድ ነበርና። ይህንንም የፈጠረው የዐይን ማረፊያ ይሆን ዘንድ ነው ጠፈር/ሰማይ ባይኖር የሰው የእንስሳ የአራዊት ዐይን ሁሉ ማረፊያ አጥቶ ወልቆ ወልቆ በወደቀ ነበርና።
ይህ ለሥጋዊ እንቅስቃሴአችን ሲሆን ለመንፈሳዊው እንቅስቃሴያችን ደግሞ በተለይ በጊዜ ቅዳሴ የዐይናችን ማረፊያ የሚሆነው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። አምላክችን ምግባር ከሃይማኖት አንድ አድርጎ የያዘ ሰውን ይወዳል ባልነው መሠረት አስቀድሳለሁ ብሎ ከቤቱ ተዘጋጅቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ሰው በዕለቱ የታወቀና ድንገተኛ ነገር ካላጋጠመው በስተቀር ሥጋ ወደሙን ይቀበል ዘንድ ወዶና ፈቅዶ የሚኖርበት ክርስቲያናዊው ሕግ ያስገድደዋል ይህን ካላደረገ ዐይኑ ማረፊያ ያጣ ሰው ሆኗል።
“እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ - እግዚአብሔርማ ሰማያትን ፈጠረ” ብሎ ለመዘመር አቅም የሚያንሰው ይሆናል። ዐይናችን ማረፊያ ሲያገኝ ልባችንም በተስፋ የተመላ ይሆናል እንዲህ ከሆነ ዐይን ያላያትን በሰው ልብ ያልታሰበችውን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ያዘጋጃትን ዘለዓለማዊት መንግሥት በተስፋ እየጠበቀ የመኖር ዕድሉ ከቀን ወደቀን ያድጋል “ትምጻእ መንግሥትከ - መንግሥትህ ትምጣልን” እያለ ይጸልያልና።


 የዐቢይ ጾም ስለሁለቱ ሳምንታት ዘወረደ እና ቅድስት



@mekra_abaw



@firehaymanotgroup



@ABUNE_ABIB
39 viewsብንያም በለጠ, 06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 09:20:36
"የትንሳኤ ትምሕርት"

ባለፍ ነው በአብይ ፆም የመጨረሻ ሳምንት ሕማማት ይህም ትንሳኤን ከማየታቸው በፈት ምዕመናን የክርስቶስን ሕማማት በመሳተፍ ያስቡታል እዕለተ አርብን ከዕለተ ዕሑድ ቀድመው በማለፍ ተግባራዊ የሆነ የክርስቶስን መከራ እያሰቡት ሕመሙ ሕመማቸው ቢሆን ሊሸከሙት እንደማይችሉ እያሰቡ ሁሉ ቻይነቱን በእንባ ይገልፁታል ። ሰው በሕይወቱ ብርሃንን ከወደደ ሌት ጨለማንም ማለፍ ማየት አለበት ። ሙላቶቻችን ሚመዘኑት በሞላናቸው ጎዶሎዎች መጠን ነው ። ይህ ደግም የክርስቶስ የትንሳኤ እየተከበረ ያለበት ሳምንት እንደመሆኑ አምላክ በመሞቱ የማይሞተው ሞተ እያልን ብንደነቅም ከዚህ በላይ ግን ሞትን አሸንፎ በነሳቱ ይበልጥ እንደነቃለን ። ሰው በህይወቱ ውስጥ እንደሞት የከበደ መከራ ቢገጥመውም እንደ ብርሃን ያለ ደማቅ ህይወት እንደሚጠብቀው እና እንደሚያልፈው አምኖ ለበጎ የሆነውን የመከራውን ጊዜ አምላኩን ያመስግን ።


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
33 viewsብንያም በለጠ, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 11:36:14
#አፋልጉን!
#ሼር_በማድረግ_የበረከት_ሥራ_ይስሩ!!
በፎቶዉ ላይ የሚትመለከቱት ወንድማችን ዲያቆን ሃይለሚካኤል መለሠ ይባላል፤በቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶያማ ደብረ ሣህል ቅድስት ሥላሴ ቤተክርሲቲያን አገልጋይ የነበረ ሲሆን በ2009 ዓ/ም የአብነት(የቄስ) ትምህርት ለመማር ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሄደ ሲሆን በስልክ ቤተሰቦቹን ካናገራቸዉ ሁለት ዓመታት አለፈዉታል!!
እናም ዲያቆን ሃይለሚካኤልን ያዬ ወይንም ያለበትን የሚያዉቅ በ0922355652 አልያም በ0900133803 ወይም 0942966646 በመደወል መንፈሳዊ ትብብር እንዲታደርጉልን በወላዲተ አምላክ ስም እንጠይቃለን!!!
#ባህር_ዳር_አከባቢ_ላሉ_ምዕመናን_ሼር_ያድርጉ!!
75 viewsBini Belete , 08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 11:35:38 ለአቢይ ፆም የሚሆኑ የዘለሰኛ(የመሰንቆ) መዝሙሮች Subscribe


51 viewsBini Belete , 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 11:24:17 ቅበላ «ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥሩ ቆነጃጅት»


"በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።እኩል ሌሊትም ሲሆን።

እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ሁካታ ሆነ።
በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። ሰነፎቹም ልባሞቹን መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። ልባሞቹ ግን መልሰው። ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።

በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ። እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"

{የማቴዎስ ወንጌል ፳፭÷ ፩-፲፫}
«እንኳን ለዓቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ! »
67 viewsBini Belete , 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 21:33:47 ††† እንኳን ለአባታችን ታላቁ ቅዱስ በርሱማ ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

@mekra_abaw
@mekra_abaw
@mekra_abaw

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ አባ በርሱማ †††

††† ታላቁ (THE GREAT ይሉታል) አባ በርሱማ በሶርያ ቤተ ክርስቲያን ምንኩስናና ገዳማዊ ሕይወትን ያስፋፋ አባት ነው::

በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ምድረ ሶርያን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች የቅድስና ሕይወትን ያስፋፋው ቅዱስ በርሱማ ለቤተ ክርስቲያን ምሰሶ ከሆኑላት አበው አንዱ ነው:: እርሱ ከተጋድሎው ብዛት ለ54 ዓመታት ያለ እንቅልፍ ቆይቷል::

በእነዚህ ዘመናትም ግድግዳ ላይ ጠጋ ብሎ ከማረፉ በቀር መቀመጥን እንኩዋ አልመረጠም:: በመዓልትም በሌሊትም በፍቅር አብዝቶ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ በመጸለዩ የብዙዎቹን ነፍስ ወደ ሕይወት ማርኩዋል::

ገዳማትን ከማስፋፋትና ደቀ መዛሙርትን ከማብዛቱ ባለፈ በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረለት አባት ነበር:: በ431 (423) ዓ/ም በኤፌሶን በተደረገው የቅዱሳን ጉባኤ ላይ ከተገኙ ሊቃውንትም አንዱ ነው:: በቅድስና ሕይወቱ የተገረመው የቁስጥንጥንያው ንጉሥ (ትንሹ ቴዎዶስዮስ) የንግሥና ቀለበቱን እና ማኅተሙን ሸልሞታል::

ቅዱሱም የዋዛ አልነበረምና በንጉሡ ማኅተም እያተመ "ተፋቀሩ" የሚሉ ብዙ አዋጆችን ወደ መላው ዓለም ልኩዋል:: በ451 (443) ዓ/ም በኬልቄዶን 636 ሰነፍ ዻዻሳት ጉባኤ አድርገው አባ ዲዮርስቆሮስን እንደ ገደሉት ሲሰማም ወደ ቤተ መንግስት ሒዶ ከሃዲዎቹን (መርቅያንና ሚስቱ ብርክልያን) በአደባባይ ዘልፏቸዋል::

ስለ አዘነባቸውም ተቀስፈዋል:: ታላቁ ቅዱስ አባ በርሱማ ፀሐይን ማቆሙን ጨምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† ቸር አምላኩ ከበረከቱ ይክፈለን::

††† የካቲት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ) የመነኮሱበት በዓል
3.ቅዱስ ዻውሎስ ሶርያዊ (ሰማዕት)
4.ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት

††† ወርሐዊ በዓላት
1."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
2.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
3.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
4.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)

††† "ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን" †††
(ሚክ. 6:6)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
58 viewsBini Belete , 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 21:33:32 እሁድ ጥር 1 -ቅዱስ እስጢፋኖስ - ልደቱ እና እረፍቱ

ማክሰኞ ጥር 3 -አባ ሊባኖስ - በዓለ እረፍታቸው
በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት እና በጣፎ ገብርኤል

ረቡዕ ጥር 4 -ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ - የተሰወረበት መታሰቢያ እለት

ሐሙስ ጥር 5 -አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ - በዓለ ልደታቸው ከታህሳስ 29 ወደ ጥር 5 የተዘዋወረ

አርብ ጥር 6 -ኢየሱስ - ግርዘቱ - በገዳመ ኢየሱስ እና በፈርንሳይ ገነተ ኢየሱስ
- ነብዩ ኤልያስ - በእሳት ሰረገላ ያረገበት
- ቅድስት አርሴማ - በዓለ ልደቷ

ቅዳሜ ጥር 7 -ቅድስት ሥላሴ - የባቢሎን ግንብ ያፈረሱበት መታሰቢያ እለት

ማክሰኞ ጥር 10 - ከተራ

ረቡዕ ጥር 11 - በዓለ ጥምቀት

ሐሙስ ጥር 12 - ቅዱስ ሚካኤል - ቃና ዘገሊላ

አርብ ጥር 13 - ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

- ቅዱስ ሩፋኤል

ቅዳሜ ጥር 14 - አቡነ አረጋዊ - ልደታቸው

እሁድ ጥር 15 - ቅዱስ ቂርቆስ - እረፍቱ

ሰኞ ጥር 16 - ቅድስት ኢየሉጣ - እረፍቷ

ረቡዕ ጥር 18 - ቅዱስ ጊዮርጊስ - ስባረ አፅሙ

ቅዳሜ ጥር 21 - እመቤታችን -እረፍቷ በዓለ አስተርእዮ

እሁድ ጥር 22 - ቅዱስ ዑራኤል - በዓለ ሲመቱ

ማክሰኞ ጥር 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት -በፀሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት (የተነሳበት) መታሰቢያ እለት

ረቡዕ ጥር 25 - ቅዱስ መርቆርዮስ - በስዕሉ ላይ አድሮ ታምር የሰራበት - በጎፋ መብራት ሀይል

ሐሙስ ጥር 26 - አቡነ ሃብተ ማርያም - ቅዳሴ ቤት- አስኮ ቃሉ ተራራ

አርብ ጥር 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤት - በቀበና መድኃኔዓለም

ቅዳሜ ጥር 28 - ቅዱስ አማኑኤል - 2 አሳ እና 5 እንጀራ አበርክቶ የመገበበት መታሰቢያ እለት

ሰኞ ጥር 30 - ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ - ቅዳሴ ቤት - በቤላ በጣፎ እና በምንጃር ሸንኮራ ዮሐንስ

ቸር ያገናኘን አሜን !!!
@mekra_abaw
41 viewsBini Belete , 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 21:32:50 ሕማማት በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ.pdf
የመጽሐፉ password ፦ @eotc_books_by_pdf ነው።

ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ በPdf ከ200+ ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍትን ብቻ በpdf ለማግኘት #1 ምርጫዎ ያድርጉን

ጉዞ ወደ እግዚአብሔር
█➥ ክፈት
ገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት
█➥ ክፈት
ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን
█➥ ክፈት
ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ
█➥ ክፈት
ውዳሴ ማርያም በግዕዝ
█➥ ክፈት
ዓምደ ሃይማኖት
█➥ ክፈት
ሕማማት በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
█➥ ክፈት
መጽሐፈ ቅዳሴ
█➥ ክፈት
የኤፍራጥስን ወንዝ
█➥ ክፈት
ባህረ ሀሳብ
█➥ ክፈት
የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ
█➥ ክፈት
አንድሮሜዳ
█➥ ክፈት

█▓▒░►ᴏᴘᴇɴ░ᴏᴘᴇɴ▒▓█
█▓▒░►ᴏᴘᴇɴ░ᴏᴘᴇɴ▒▓█
█▓▒░►ᴏᴘᴇɴ░ᴏᴘᴇɴ▒▓█
█▓▒░►ᴏᴘᴇɴ░ᴏᴘᴇɴ▒▓█
39 viewsBini Belete , 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 21:31:09 ከንቲባ አዳነች አቤቤና ካቢኔያቸው ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተዋል።

ከንቲባዋና ካቢኔያቸው ዛሬ የካቲት ፰ ቀን ፳፻ ወ፲፬ ዓ.ም በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተገኙት ቋሚ ሲኖዶሰሰ የካቲት ፬ ቀን ፳፻ ወ ፲፬ ዓ.ም በመስቀል አደባባይ፣ በወይብላ ማርያም ጉዳይ፣ በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀትና በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ዙሪያ ተወያይቶ አሉ የሚባሉ ችግሮችን በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለመፍታት ይዞት የነበረው ቀጠሮ በወቅቱ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ ስለነበረውና ከንቲባዋም በዚያ መገኘታቸው የግድ ስለሆነ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር የነበረው ቀጠሮ ለዛሬ እንዲተላለፍ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና ከአስተዳደሩ የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአካል ተገኝተው ለቋሚ ሲኖዶስ በገለጹት መሰረት የውይይቱ ጊዜ ለዛሬ እንዲተላለፍ መደረጉ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ከንቲባዋና የካቢኔ አባላቶቻቸው ዛሬ የካቲት ፰ ቀን ፳፻ ወ፲፬ ዓ.ም በሰዓቱ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ሲሆን ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ብፁአን ከባቶች፣የሕግ ባለሙያዎች፣ከመምሪያ ኃላፊዎች ጋር በሚያደርጉት ውይይትም አሉ የሚባሉና ቤተክርስቲያን የምታቀርባቸው ጥያቄዎች ሁሉ ፍጹም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍትሔ የሚያገኝበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ ተብሎ ይገመታል።

ከዚህ ቀደም በቋሚ ሲኖዶስ አባላትና በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ መካከል ሊደረግ የታሰበው ውይይት በተለያዩ ምክንያቶች እንቅፋት እየገጠመው መቆየቱ ይታወሳል።
ምንጭ፡-የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC
37 viewsBini Belete , 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ