Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርና ተስፋ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tloveandhope — ፍቅርና ተስፋ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tloveandhope — ፍቅርና ተስፋ
የሰርጥ አድራሻ: @tloveandhope
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 247
የሰርጥ መግለጫ

ተስፋ ማለት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብርሃን አለ ብሎ ማመን ነው።
ተስፋ ማለት ወደ ባህር እየተወረወሩ በሆነ ተአምር እንደ ሚድኑ ማመን ነው
ፍቅር ማለት ፍፃሜው የሚያምር ቅርብ ማንነትንና ግልፅነትን የሚያስተምር...ርህራሄና ለሰው ማዘንን በልብ የሚያኖር ከፈጣሪ የሚገኝ ፀጋ ነው።
ፍቅር ያለ እምነት ነፋስ ላይ እንደ ተቀመጠ ሻማ ነው።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 12:09:51 የአንድ አባት ፀሎት
።።።።።።።።።።።።።።።።
ሚበላ የሚላስ የሚጠጣ በሌለበት
የአንድ ሚስኪን አባት የለመና ፀሎት
በተቆራመተ መንገድ ንፋስ በሚነፍስበት
በብርዳማ አለም ብዙ መንገደኛ በሚተራመስበት
በባዶ ሆድ በብጣቂ ጨርቅ ተሸፍኖ ከሰዋች መሀል በሚታይበት
ስለሀገሩ አንድነት ፀለየ በእውነት
ቀጥሎም ስለ ራሱ እውነት
አብዝቶ ተማፀነ አንድ ሚስኪን አባት
ሰው በሚጓዝበት መንደር
ስለሰው አብዝተው ይፀልዩ ነበር
በችግሮቹ መሀል ሌላው እንዳይቸገር
አንድ ሚስኪን አባት ከራሱ አስቀድሞ ለሀገሩ ይፀልይ ነበር
የሰው እጅ በማየቱ ልቡ ቢያመው በብርቱ
አንዳች አላማረረም ፀሎት ነው ብርታቱ
M.M

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!

@tloveandhope
30 viewsChristyan, 09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 12:04:11 ፅናት!

"በዓለም ላይ የፅናትን ቦታ የሚተካ ምንም ነገር የለም። ብቃትም አይደለም። እንደውም ብቃት ያላቸው ስኬታማ እንዳልሆኑ ብዙ ቁጥር ያለው የለም። የረቀቀ ዕውቀትም አይደለም እንደውም ሰዎች እንደማወቃቸው ስኬታማ አለመሆናቸው ቢታይ አስገራሚ ትዕይንት ነው። መማርም አይደለም። ዓለማችን በተማሩና በማይሰሩ ሰዎች የተሞላች ናት። ጽናትና ቁርጠኝነት ግን ሁሉንም ነገሮች ናቸው። የአላማ ፅናት ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ቦታ ተነስተው ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ሊያቆማቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።" -ካልቬን ኮሌጅ

"እያንዳንዱ ታላላቅ የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው" -ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ


@tloveandhope
28 viewsChristyan, 09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:57:47 የዋህነት ማለት ክፋትን በክፉ ለመመለስ ሙሉ ሀይል ይዞ ነገር ግን ሀይል ለክፋት ላለመጠቀምና እራስን መግዛት ማለት ነዉ።የዋህ ማለት ሞኝ ማለት ሳይሆን ሀይል እንዳለዉ እያወቀ ሀይሉን ለክፋት ሳይሆን ለመልካምነት ብቻ ለመጠቀም የወሰነ እራሱን የሚገዛ ማለት ነዉ፡፡

በየዋህነት ዉስጥ ደሞ ጥሩነት ወይም መልካምነት አለ።መልካምነት እንደወጥ ማጣፈጫ ጨዉ ማለት ናት ማንም ሰዉ በዉስጡ መልካምነት ሳይኖረዉ ደስተኛ መሆን፡መርካት፡ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፡ጤናማ መሆን አይችልም።ምክንያቱም መልካምነት ሀገር የለዉም ድንበር የለዉም ጥቁር ነጭ አይልም በነፃ አገልግሎት ወገንን ማስደሰት ሁል ጊዜ ለሰዉ በመስጠት በማድረግ እንጂ ዉለታ የማይጠብቅ እራስ ወዳድነት የማይሰማዉ ልዩ ነዉ መልካምነት።የሚገርመዉ መልካምነት ሁሌ በመስጠት በማድረግ የሚረካ ሲሆን ትርፉም የህሊና ሰላም ደስታ ፍቅር ጤና ብቻ ብዙ ነገር እናገኝበታለን ።

ታድያ ይሄ ደስ አይልም
መልካም ነገር ማድረግ ባንችል እንኳን ከመጥፎ ስራዎች እንቆጠብ

@tloveandhope
37 viewsChristyan, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:18:54 ያልተሰራ አእምሮ የተሰራን ከተማ ያፈርሳል

የተሰራ አእምሮ ደግሞ የፈረሰ ከተማ ይሰራል!!


#tattoo
Join @tloveandhope
728 viewsChristyan, 16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:58:50 ..........
"... ምድር ለኛ የመጨረሻ መድረሻችን ሳትሆን ወደ ዘላለም የምንሻገርበት ድልድይ ናት... የሠማይ መንገደኞች ነን... ወደዚች ምድር የመጣነው እኛ ፈልገን ሳይሆን ምድር ስለፈለገችን ነው... እንዴት እንደምንኖር ግን እኛና አካባቢያችን እንወስናለን...
ትልቁ መኖርም እኛ እንደፈለግን ሳይሆን በምድር እንደተፈለግን መኖር ነው.. ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም.. ሁሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል...
የተፈጠርንለት ዐላማ ለሌሎች ሰዎች ጥቅምም ነው... የህይወት ዐላማችን የሚፈጸመው በሌሎች ውስጥ ነው... ነገር ግን ለሌሎች መኖር የምንጀምረው ለራሳችን በተገቢው መኖር ስንጀምር ነው....."
#ዮቶራዊት
51 viewsChristyan, 13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:46:40 በረደኝ


ይደክማል ጎዳናው የሰው ዋጋ መርሳት
ከእንቅልፍ ሲነቁ ያ'ዘን መርዶ መስማት
ይደክማል ጎዳናው የሰው እንባ ሲቀል
የሰው ልጅ ህይወቱ መንገዱ ሲነቀል
ይደክማል ጎዳናው ያለቦታው ማውራት
ሰው ሞቷል እያሉ ሁሌ ሻማ ማብራት
ይደክማል ጎዳናው ማንኳኳት የሰው በር
መኖር ያልጀመሩ ህፃናትን መቅበር
ይደክማል ጎዳናው እናት ስታለቅስ
ቤተክርስቲያን አዝና :ከፍቷት ስታስቀድስ
ይደክማል!
ይደክማል ጎዳናው በሰው መደራደር
ነገ ምን ይሆን ብለው? እየሰጉ ማደር


ምንድነው ባንዲራ?
ዝቅ ብሎ ይሰቀል ብሎ የሚነገር
የሞተውን ደሃ
ወደ ቤተሰቡ ላይመልሰው ነገር


በናት ቀሚስ ለቅሶ
ያለምንም ስስት ስልጣን እየገዙ
ነጋችን ወዴት ነው?
ዝቅዝቅ ነጠላዎች እንደዚ ከበዙ

እንደ ነኸምያ ቅጥር
እንባን ማበስ ማከም እጅህ ካልወደደች
አትኖርም ኢትዮጵያ
ቀስበቀስ እንዳምና በቀልድ ትሄዳለች


እግዚኦ ለትውልዱ እግዚኦ መአረነ
ህዝብህና ህዝብህ፡ ሄደ እየቀለለ(እየመነነ
እግዚኦ ለኢትዮጵያ እግዚኦ ለአገሬ
እንባዋ ይታበስ መዳን ይሁን ዛሬ
እግዚኦ ለትውልድህ እግዚኦ ላልቃሾች
ህመም ለለበሱ ለወደቁ ህዝቦች


ጌታ ሆይ

ሲነጋና ሲመሽ
እንደተራ ነገር ሰው መቅበር አመመኝ
እባክህ እንደ'ስራኤል
በ ክብርህ መተህ መባረክን ባርከኝ
ህዝቤን አስብልኝ!


ምንጮህበት አካል
እርዳኝ ምለው አባሽ ፡ወገን ስለሌለኝ
አቤቱ ጌታዬ
አሞኛል በሃይል ፈጥነህ መተህ እርዳኝ


የምስኪናን እንባ
እንደዘፈን አርገው በሚያደምጡት ጊዜ
አንተ ፊት ልደፋ
ማታ ልጩህ ፊትህ እግርህ ስር ወድቄ


ደከመኝ አመመኝ
ዛሬ አንድ ሰው ሄደ ትላንት ሁለት መቶ
ማነው የሚያወጣን
ከጭንቅ ጊዛያችን በታምራት መጥቶ????
በአራቱም አቅጣጫ
ብንሄድ ወገን ጋር መንገዱ ደም ብቻ

እኔ ልጠይቅህ

በደምህ የገዛኸው
ዋጋው ምን ያህል ነው የፍጥረትህ ዋጋ??



@tloveandhope
46 viewsChristyan, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:39:45 *ሀገሬ የት ገባሽ
ኧረ ምኑ ዋጠሽ
ለምንስ እድህ ሆንሽ '''

ኦሮሞ ጉራጌ ሙስሊም ክርስቲያኑ
አማራ ሶማሌ ህዝብ ና ዙፋኑ
የተከባበሩ በፍቅር የኖሩ
ሌላው መፍትሄ እጂ ያልሆነ ችግሩ
ሸሆች ሲናገሩ ቃላቸው ሲጣፍጥ
ቄሶች ሲጸብሉ ያለዘር ያለጎጥ
ኦሮሞው ሲያገባት ያማራን ውብ ቆንጆ
አፋር ከሶማሌ ሲመሰርት ጎጆ
ለሙስሊም በኣላት የሚጠራሩበት
የተቃለዱ የሚያሳልፍበት

በጣም የሚከበር የሚፈራ መቅደስ
አብሮ የሚበላ ተካፍሎ የሚቆርስ
ፈጣሪ ሳያዘው ማንንም ሳናጣ
ሀዘንታ ነበረን አስክሬን ሲመጣ
እንባችን አይደርቅም ከልብ ሲወጣ
ያኔ ድሮ ዶሮ እደዚህ ነበርን
..........ተከባብረን የኖርን
ሀገሬ የት ገባሽ
ኧረ ምኑ ዋጠሽ
ለምንስ እድህ ሆንሽ
አንድ ሰው ስናጣ ታሪክ የሚያስጠናን
ያኔ እዛጋ ቀረን ዛሬ ላይ እድህ ሆን

ዛሬ ተለውጠን በተቃርኖ ሁነን
ሠርቀን የምናድር ኑሮን የምለምን
ቆሶችን ሳንፈራ ሰይጣንን ያነገስን
በየወዛወዙ ሸህን የቀበርን
አምላክን ሳንፈራ ሰይጣን የምናምን
ሰውን አርደን የጣልን
.... አዘኔታን ያጣን
ከሰውነት ወርደን ስጋን እየበላን
ምንም የማያውቅን ህጻን ያቃጠልን።

ሰው ሜዳ ወርቆ ኪሱን የምዳብስ
እናት ልጇን አታ በመንታ ስታለቅስ
አሞራ አስበላነው አምላክ የሰራውን
ፈጣሪስ አስችሎት እደትስ አቆመን ።


ሀገሪቷ ጠባንን ድበር ስንገፋ
ዙሪያችንን ከቦት ደም እየተስፋፋ
ሁሉም እየሞተ ሁሉም ዘሩ ጠፋ።

#ሀሰን አለባቸው (hashuya)

መልካም በኣል
42 viewsChristyan, 11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:26:50 ፍቅርና ተስፋ pinned «መቸም ቢሆን አልረፈደም! ከ65 አመቱ ወጣት የምንማረው...! በአንድ ወቅት በአንዲት ኬንታኪ በምትባል የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ከመንግስት በየወሩ በሚሰጠው 99$ የሚኖር ፣ ገንዝብ አልባ ፣ ትንሽ ቤት ውስጥ የሚኖር እና አሮጌ መኪና የሚነዳ ሽማግሌ ሰው ነበር ። ይሄ ሰው ልክ 65 አመት ሲሞላው ልጅነቴንማ በዚህ መልኩ ማባከን የለብኝም በማለት ነገሮችን ለመቀየር ተነሳ ። ከዚያም ምን አገልግሎት? ለሰዎች…»
05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:26:33 መቸም ቢሆን አልረፈደም! ከ65 አመቱ ወጣት የምንማረው...!

በአንድ ወቅት በአንዲት ኬንታኪ በምትባል የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ከመንግስት በየወሩ በሚሰጠው 99$ የሚኖር ፣ ገንዝብ አልባ ፣ ትንሽ ቤት ውስጥ የሚኖር እና አሮጌ መኪና የሚነዳ ሽማግሌ ሰው ነበር ።

ይሄ ሰው ልክ 65 አመት ሲሞላው ልጅነቴንማ በዚህ መልኩ ማባከን የለብኝም በማለት ነገሮችን ለመቀየር ተነሳ ። ከዚያም ምን አገልግሎት? ለሰዎች ልስጥ ብሎ ሲያስብ ጓደኞቹ ሁሌ የሚያደንቁለት የዶሮ አሰራሩ ትዝ አለው ። ስለዚህ በህይወቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ይቺ የዶሮ አሰራር ቁልፍ እንደሆነች ወሰነ!!!

ከዛም ጥርስ የነቀለባትን ኬንታኪ ትቶ ይቺኑ የምግብ አሰራር ለመሸጥ ብዙ የአሜርካ ክፍሎችን ዞረ። ለብዙ የሬስቶራንት ባለቤቶች እጅ የሚያስቆረጥም የዶሮ አሰራር እንዳለው ነገራቸው። እንደውም ከሽያጫቸው ላይ ትንሽ ፐርሰንት ከሰጡት አሰራሩን በነጻ ሊሰጣቸው ሁሉ ፈቀድ።

የሬስቶራንት ባለቤቶቹ ግን እንደሱ አላሰቡም። 1000 ግዜ አይሆንም አሉት። እሱ ግን እጅ አልሰጠም።

ዶሮ አሰራሩ በጣም የተለየች እንደሆነች አጥብቆ ያምን ነበርና። የመጀመሪያውን እሺ እስኪያገኝ ድረስ 1009 ግዜ አይሆንምን ሰማ ።

በመጨረሻ ግን ኮሎኔል ሃርትላንድ ሳንድራስ አሜርካኖች ብቻ አይደለም በአለም ያለ ሰው ሁሉ ዶሮ የሚበላበትን መንገድ ቀይሯል ።

ኬንታኪ የተጠበሰ ዶሮ መሸጫ (KFC) የተፈጠረው በዚህ መልኩ ነው ።

ከ65 አመቱ ወጣት ጋሽ ሳንድራስ የምንማረው .....

#መቼም ቢሆን አልረፈደም!
40, 50 ወይም 60 አመትም ቢሞላን መንገድ መቀየር ከፈለግን ማለት ያለብን "ልጅነቴንማ እንደዚህ አላባክነውም" ነው ።

በህይወት መዘግየት ማለት አለመድረስ አይደለም። ስለዚህ ሁሌም ጉዞህን ቀጥል!

ሁሌም ካለህበት ጀምር፤ ያለህን ተጠቀምበት፤ የምትችለውን አድርግ!

መልካም ቀን!

@tloveandhope
45 viewsChristyan, edited  05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:26:02
ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ። ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል 'እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው' ይለናል። ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን። ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
37 viewsChristyan, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ