Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ኢትዮጵያ/About Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ aboutethiopia — ስለ ኢትዮጵያ/About Ethiopia
የቴሌግራም ቻናል አርማ aboutethiopia — ስለ ኢትዮጵያ/About Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @aboutethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.20K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ፣ባህል ፣ትውፊት ፣ቅርስ ፣መልከአምድር እያወቅን የምንማማርበት ገፅ ነዉ ይቀላቀላሉን አብረን ኢትዮጵያን እንቃኛት።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-19 22:39:18
#የታላቁ_ህዳሴ_ግድብ_እውነታዎች

ግድቡ 5,150 ሜ.ዋ ሀይል የማመንጨት ሀይል አለው

13 የሀይል ማመንጫ ዩኒቶች (ተርባይኖች) የተገጠሙለት ነው

እያንዳንዱ ተርባይን 375 ሜ.ዋ በላይ የማመንጨት አቅም አለው

ግድቡ 145 ሜትር ወደ ላይ ይረዝማል፤ ወደ ጎን ደግሞ 1.8 ኪ.ሜ
የሚሸፍን ሆኖ ነው የተገነባው

ከዋናው ግድቡ ሞልቶ የሚወጣው ውሃ ሳድል ግድብ (ኮርቻ ግድብ)
ውስጥ ይከማቻል

ኮርቻ ግድብ 50 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ወደ ጎን 5.2 ኪ.ሜ የሚሸፍን ነው

በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ግድብ ነው።

አጠቃላይ እስካሁን ባለው መረጃ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 16.2 ቢሊዮን
ብር በላይ ተሰብስቧል

ግድቡ አሁን ያለበት ደረጃ 1ኛ እና 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቋል

በነገው እለት አንዱ ተርባይን ሀይል የሚያመነጭ ይሆናል

አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 83.9% ተጠናቋል

ግድቡ ለቱሪዝም፣ ለአሳ ሀብት ለኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ጠቀሜታዎች
አሉት

ከግድቡ ግንባታ ጋር ተያይዞ 246 ኪ.ሜ የሚሸፍን አርቴፊሻል ሀይቅ
ይፈጠራል።
1.9K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-18 22:25:43

የካቲት 12/1929ዓ.ም ፋሺሽት ኢጣልያ 30,000 የሚሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ንፁሃን ኢትዮጵያዊያንን ዘር ፣ ቀለም ፣ ሐይማኖት ፣ ፆታ ፣ እድሜ ሳይለይ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ በግፍ የጨፈጨፈበት ቀን ሆኖ እለቱ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በክብር ታስቦ ይውላል።



እናንት የሀገር ዋልታዎች በደም እና በአጥንት መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ከእነሙሉ ክብሯ ስለ አስረከባችሁን በልባችን እስከዘላለሙ ከብራችሁ እና ፀንታቹህ ትኖራላችሁ



ዘላለማዊ ክብር እና ሞገስ ለየካቲት 12 ሰማዕታት
1.4K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 13:12:16
የጨዋታ ቀን
ምሽት 4.00

ኢትዮጵያ Vs ኬፕቬርዴ

አያሆሆ ኢትዮጵያዬ ማታ ነው ድልሽ

ይቅናሽ ሀገሬ
2.1K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 09:04:27
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤
********
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ።
**********
በዐሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና ፣ የመረዳዳት ፣ የአብሮነት ይሁንላችሁ!!
1.9K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 23:32:03
በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፤
በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ

የገና ጨዋታ መቼ እደተጀመረ የሚገልፅ ትክክለኛ መረጃ ባይኖርም ከክርስቶስ ልደት በፊት እረኞች በተለይ በበጋው ወቅት ከብት እየጠበቁ መስክ ላይ ይጫወቱት እንደነበር ይነገራል፡፡ ታድያ ይህ ጨዋታ አዝናኝና ተወዳጂ በመሆኑ ዘር፤ የሀብት ደረጃን፤ የሥራ ኀላፊነትና ሌሎች ልዩነቶች ሳይኖሩት ሁሉንም ሰው
ያሳትፋል በዚህም “በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ” እየተባለ ይገጠምለታል፡፡ የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል የሚከበረው የገና ጨዋታ በሚዘወተርበት ወቅት በመሆኑም በዓሉ ሲከበር የገና ጨዋታም በስፋት ይካሄዳል፡፡

t.me/Aboutethiopia
1.6K views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 13:44:44 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በድምቀት ከሚከበሩት
የኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት መካከል የልደት (ገና) በዓል አንዱ ነው።

ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው ይህ በዓል በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች በብሔራዊ በዓልነቱ ቢታወቁም በጥንቷ ሮሃ በዛሬዋ የቅዱስ ላሊበላ ከተማ ያለው አከባበር ግን አጅግ የላቀ ፣ የደመቀ እና የተለየ ነው።

የቅዱስ ላሊበላ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን አቅጣጫ በ800 ኪሜ ርቀት ገደማ የምትገኝ በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩት ንግስናን ከክህነት አጣምረው ከያዙት አራቱ ቅዱሳን መካከል አንዱ በሆነው በቅዱስ ላሊበላ ስም የተሰየመች፣ መልከዓ ምድራዊ
አቀማመጧም ቀይ መሬት በሆነ ኮረብታ የምትታወቅ እና ከአንድ አለት ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሙዚየም ነች ።

በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልነበረበት ከ800 ዓመት በፊት ድንቅ በሆነ የአሠራር ጥበብ ታንፀዉ በዘመናችን በትንግርት ማዕከልነታቸዉ የሚጠቀሱ ሆነዋል። እንደ ሰንሰለት ተያይዘዉ ከተማዋን ያደመቁት አብያተ ክርስቲያናቱ ዮርዳኖስ ተብሎ በሚጠራዉ አነስተኛ ሸለቆ
ተለያይተዉ በሦስት ምድብ ተከፍለዉ ይገኛሉ። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ከመሠረት እስከ ጣራ፣ ከመቅደሱ እስከ ቅኔ ማህሌት ድረስ ከአንድ ወጥ አለት ተፈልፍለዉ የተሰሩ ፣ በልዩ ልዩ ቅርጾች ያጌጡና አንዱ ከሌላዉ ጋር የማይመሳሰሉ ናቸዉ።ከመደበኛዉ የህንፃ አሠራር ሁኔታ በተለየ መሠረታቸዉ የተጣለዉ ከጣራቸዉ ላይ መሆኑ ደግሞ የተለየ አግራሞት የሚፈጥር ነዉ።

የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን በ1520 ዓ.ም በመጎብኘት የመጀመሪያ የሆነዉ አዉሮፓዊ የፖርቱጋል ቄስ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ጉብኝቱን “እጅግ በጣም አስደናቂ እና ከፍተኛ የጥበብ ችሎታ የሚታይበት ዕፁብ ድንቅ ሥራ በመሆኑ ያየሁትንና የተሰማኝን ነገር ሁሉ
ብጽፍ የሚያምነኝ ስለማይኖር በእግር ተጉዘዉ ሄደዉ በአይናቸዉ ለሚያዩት ትቻለሁ“ በማለት አጠቃሎታል።የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የአህመድ ግራኝንም የጭካኔ ልብ የሰበሩ የጥበብ
መዶሻዎች ናቸዉ።አህመድ ግራኝ በ16ኛዉ መቶ ክ/ዘ ወረራዉ አብያተ
ክርስቲያናቱን አድንቆ ሳይነካቸዉ ትቷቸዉ እንደ ሄደ የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከሌላው አካባቢ በተለየ ሁኔታ የገና
በዓል በቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የሚከበርበት ዋና ምክንያት
ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት በታህሳስ 29 ቀን በመሆኑ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የዚህ ጻድቅ ንጉስ የልደት ቀን ከጌታችን የልደት ቀን ጋር በመግጠሙ የልደት በዓል በቦታው እንዲከበር ምክንያት ሆነ፡፡ በገድሉም እንደተጻፈው ቅዱስ ላሊበላ የተወለደው ታህሳስ 29 ቀን በ1101 ዓ.ም ከአባቱ ከንጉስ ዛም ስዩም እና ከእናቱ ከኪርወርና ነው፡፡ ኪርወርና በጥንቱ የአገውኛ ቋንቋ ቤተ ክርስቲያን ማለት እንደሆነም ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜ ነጫጭ ንቦች ስለከበቡት እናቱ ይህንን አይታ ልጇን ንብ በላው ለማለት በአገውኛ ላል በላ እንዳለችውና በሂደትም ስሙ ላል ይበላ /ላሊበላ/ ተብሎ መጠራት እንደጀመረ በገድሉ ተገልጿል፡፡

ድንቅና ማራኪ የሆነው የገና በዓል ሥርዓት የሚከናወነው በቤተማርያም
ቤተክርስቲያን ዙሪያ እንደ አጥር ከቦ ከሚገኘውና በተለምዶ ማሜ ጋራ ተብሎ በሚጠራው ኮረብታማ ዓለት ላይ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ካህናቱ ከላይ ከኮረብታውና ከታች ከቤተክርስቲያኑ ዙሪያ ሆነው በመላእክትና በእረኛ ምሳሌ የሚያመሰግኑት ‹‹ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ›› የሚለው ዝማሬ ልብን የሚመስጥና ከ2 ሺህ ዓመት በፊት የተከናወነው መንፈሳዊ ታሪክ በምናብ የሚያስቃኝ ነው፡፡ በገና በዓል ሰሞን የቅዱስ ላሊበላ ከተማ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪው ዓለምበሚመጡ
አማኞችና ጎብኚዎች ትጥለቀለቃለች፡፡በመሆኑም እንደ አቢያተክርስቲያናቱ የገና በዓልም የከተማዋ ዋነኛ መታወቂያ ሆኖ
ይገኛል፡፡

የቅዱስ ላሊበላ ከተማ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ዳግማዊ ኢየሩሳሌምበመባል ትታወቃለች፡፡የመጀመሪያው ወደ ቅድስት አገር
ኢየሩሳሌም ለመሳለም ይሄዱ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ሥቃይ
ለመቀነስ ቅዱስ ላሊበላ ኢየሩሳሌም በሚገኙ ቅዱሳን መካናት አንፃር
በቦታው አብያተ ክርሰቲያናቱን በማነፁ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች ኢየሩሳሌም ሄደው የሚያገኙትን መንፈሳዊ በረከት ብዙ ችግር ሳይገጥማቸው አገራቸው ለማግኘት እንዲችሉ ታስቦ አብያተ ክርስቲያኑ እንደታነፁ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ሌላው ምክንያት ደግሞ የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያንን ተሳልሞ በቀጥታ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ሄዶ እንደተሳለመ ይቆጠርለታል በማለት ለቅዱስ ላሊበላ በገድሉ የተሰጠውን ቃል ኪዳን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

በቅዱስ ላሊበላ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረው የልደት በዓል መንፈሳዊ
በረከት የሚታፈስበት ብቻ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ትምህርት የሚገኝበት ትእይንት፣ለጭስ አልባው የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሰፊ ድርሻ ያለው እና
ለአገር ገፅታ ግንባታ የላቀ ሚና የሚጫወት የቅርስ ሀብታችን
ነው።

ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ
1.4K viewsedited  10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-06 13:44:28
የገና (የልደት)በዐል በላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት

t.me/Aboutethiopia
1.2K views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-05 15:58:58
"የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት ፤ የግል ርስት አልፈልግም ። ደግሞስ የተሾምነው እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል?"
አፄ ምንሊክ

t.me/Aboutethiopia
1.2K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 13:40:02
አፄ ቴዎድሮስ ከእረፍታቸው ጥቂት ቀናቶች ቀደም ብሎ ጄነራል ናፒየር ለአፄ ቴዎድሮስ በጻፈው ደብዳቤ ንጉሡ እስረኞቹን ከፈቱና ለ"እንግሊዟ ንግሥት እጅ ከሰጡ" "በክብር እንደሚያዙ" አሳወቃቸው። ሆኖም ንጉሰ ነገሥቱ ከኩራታቸው አንጻር ይህን አይነት መዋረድ እንደማይቀበሉ አሳወቁ። በዚህ ሁኔታ ንጉሱ አቋማቸውን በደምብ የሚያሳውቅ፣ በጊዜው "ድንቅ" የተባለ ማንነታቸውንም በርግጥ የሚይሳይ ደብዳቤ ጻፉ። ለናፒርየር የተጻፈው ይህ ደብዳቤ አጠቃላይ የጊዜውን የኢትዮጵያ ሁኔታ የዳሰሰና ለኢትዮጵያ ህዝብ የገቡት የመጨረሻ ኪዳን ነበር።

"በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አንድ አምላክ፡ በሥላሴ፣ በክርስቶስ፡ የሚያምነው ፡ ካሳ ለአገሬ ሕዝብ"ግብርን ተቀበሉ፣ስርዓትንም ተማሩ" ብየ፡ብነገር፡ እነርሱ ፡ ግን፡ ይህን ፡ በመቃወም፡ ከኔ ጋር ጥል ጀመሩ። አንተ ፡ ግን ፡ በስራት፡ በሚመሩ፡ ወታደሮች፡ ታሸንፋለህ። አልባሌ ፡ የብረት፡ ኳስ፡ ፈርተው፡ የሚወዱኝና ፡ የሚከተሉኝ ፡ሰወች ፡ ጥለውኝ ፡ ጠፉ። አንተ ፡ጥቃት፡ ስታደረስ፡ ከነርሱ፡ ጋር አልነበርኩም። እኔማ፡ እራሴን፡ ትልቅ ፡ አድርጌ፡ ቆጥሬ፡ ዋጋ ፡ በሌለው፡ መድፍ ፡ ተዋጋሁ። እግዚአብሔር ፡ ቢፈቅድ፡ ሁሉን ፡ለመመራት፡ ነበር፡ ሃሳቤ፣ አምላክ ፡ ይሄን፡ ከከለከለኝ ፡ ሞቴን እጠብቃለሁ ፡ እራስክን ፡ ትላንት ፡ያስደሰትክ ሆይ፣ አምላክ እንደኔ አያድርግህ፣ በተለይ ደግሞ አምላክ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ጠላቶቸን አያድርግህ። እኔማ
እየሩሳሌም ሂጄ ቱርኮችን ለማባረር ነበር ሃሳቤ። ወንዶችን የማረከ፣ በሌሎች ሊማረክ አይችልም።"
1.4K views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-02 14:34:20
አጤ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ከእንግሊዝ አገር ከመጡ 32 ሺህ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቷ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ
እንደተፈፀመ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ።
ከተዘረፉት ውስጥ አንዱ የሆነው የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ(ሹሩባ) በጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ታላቅ አቀባበል እየተደረገለት ነው።

https://t.me/Aboutethiopia
1.9K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ