Get Mystery Box with random crypto!

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdu_rheman_aman — نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے ن
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdu_rheman_aman — نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
የሰርጥ አድራሻ: @abdu_rheman_aman
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.20K
የሰርጥ መግለጫ

فليس العلم بكثرة الرواية ولا بكثرة المقال.
ولكنه نور يقذف فى القلب يفهم به العبد الحق
ويميز به بينه وبين الباطل. /هـ
አስታያየቶዎንና ምክሮዎን⇩
@Nehnu_abnau_aselefiyin_bot
በዚህ ያድርሱን👆

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-18 11:11:01 ላ ኢላሀ ኢልለሏህ
=~~~~~~~~~=
ተውሒድ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻው ይህችን የኢስላም መግቢያ ቃል ለማስፈፀም የሚውል የአሏህ መብት ነው። ላኢላሀ ኢልለሏህ ከሁለት ክፍል ጥምረቶች የተገኘ ነው።

1)«ላ ኢላሀ » ትርጉሙ: በሐቅ የሚገዙት አምላክ የለም ማለት ሲሆን ይህም የሚመለኩ አካላትን ሁሉ ውድቅ ያደርጋል። በዚህ ባሕሪውም የተነሳ በዑለሞች(ሌክቸረሮች) ምዛናዊ የቃላት አጠቃቀም «አንـናፊ» (ውድቅ አድራጊ) በመባል ይታወቃል።

2)«ኢልለሏህ» ትርጉሙም: አሏህ ብቻ ቢሆን እንጂ ማለት ሲሆን ከመጀመርያው ክፍል ከአምልኮት ባለቤትነት ውድቅ የተደረጉት በሙሉ እንደወደቁ ይቀሩና አሏህ ብቻ ቢሆን እንጂ በሚል ገለፃ የተመላኪነት ባለቤትን ለእርሱ ብቻ ያፀድቃል። ይህም አምልኮን ለአሏህ ብቻ አረጋጋጭ ክፍል ሲሆን በዚህ ባሕሪውም በዑለሞች ቃላዊ አጠቃቀም«አልـሙሥቢት» (አጽዳቂ) በመባል ይታወቃል። ይህች ቃል በኢስላም ውስጥ ያላትን ድርሻ ለማወቅ ለአንድ ማሽን ሞተር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ማወቅ በቂ ነው። ቃሏ የኢስላም ሞተር ነች።

ነብያት በሙሉ የኃላፊነታቸው መጀመርያ የነበረው የዚህችን ቃል ፍርድ ማስፈፀም ነበር የዚህችን ቃል ፍርድ ሕዝቡ በትክክል ተረድቶታል፣ ተግባር ላይም አውሎታል ተብሎ እስካልታመነ ድረስ ወደ ሌላ ርዕስ በፍፁም አይገቡም ነበር።

ማሳሰቢያ፦
======
ተውሂድ በሶስት አይከፈልም ምን አልባት ወሀቢዮች መንደር ቢሆን እንጂ እያሉ ለሚለፈልፉ፣ የአሻዒራዎች መሪ የነበረው "ጘዛሊ" ተውሒድን በአራት እንደከፈለ ማሳወቁ በተውሒድ ዙርያ የሚያስለፈልፍ አጋንንት ለሰፈረባቸው የአሕባሽ ጫጩቶች ደህና የአፍ መቆለፍያ ሰረገላ ነው። [ኢሕያእ ዑሉሙ ዲን 4/245 እና አል አርበዒን 103ـ 104]
~
ኢብኑ አማን
`
t.me/abdu_rheman_aman
366 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 07:51:11 ጠያቂው እንዲህ ይላል ፦

ماحكم إمرأة صلت وقدماها مكشوفات، ليست لابسة جوارب؟
እግሮቿ ተገልጠው : ካልሲም ሳትለብስ የሰገደች ሴት ሁክሟ ‹ፍርዱ› ምንድን ነው?

ሸይኹ-ል-አልባኒይ ፦
لاتصح
‹ሶላቷ› አይበቃም

ጠያቂው ፦
يعني يجب عليها أن تعيدها؟
ማለት: ሶላቷን መመለስ ግዴታ ይሆንባታል ማለት ነው ?

ሸይኹ ፦
إي: نعم
አዎን ‹መመለስ ይዎጅብባታል።›

[سلسلة الهدى والنور: شريط 603]

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman
35 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 23:17:53 ሸይኽ ዐብደ-ል-ሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር የሚከተለውን ተጠየቁ ፦

የሆነ ግለሰብ በመስጂደ ነበዊይ ጫማው ተሰረቀበት: የሌላን ሰው ጫማ መውሰድ ይችላልን?

መልስ ፦
"إذا ظُلمت فلا تظلم غيرك "
"ከተበደልክ ፣ ካንተ ውጭ ያሉትን አትበድል"
[ደርስ ሶሒሑ -ል- ቡኻሪይ: ሶፈር /28/ 1440 هـ]

= ባጭሩ መልሱ ፦
ስለተሰረቀብህ የሌላን ሰው ጫማ አትውሰድ/ አትስረቅ ነው። በመስጂደ'ነበዊይ ይሁንም በሌላም መስጂድም ይሁንም አትውሰድ/አትስረቅ።

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman
85 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, edited  20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:45:18 የጥበብ ጮራ 4!
ይሰማህ!
"ጨረቃን ውብ ያደረጋት በጨለማ መከበቧ ነው። በደማቁ የምትታየውም አጠገቧ ያለውን ፅልመት ስለገረሰሰች ነው። አንዳንድ ጊዜ በችግርህ ስትከበብ ድሎትህ ሊፈነጥቅ፤ በውድቀት ስትሞላ ስኬትህ ሊያብብ ፤ በጥላቻ ስትወገዝ በፍቅር ልትደሰት እንደሆነ ይሰማህ!።"
.
.
.
ከችግር ጋር ምቾት አለ!
t.me/abdu_rheman_aman
80 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 10:25:55
.
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
134 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, edited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 09:02:09 ሶሃቢዩ ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑ -ል-ኸጣብ "አሏህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና፦

يهجر يوم الجمعة
فيطيل الصلاة قبل أن يخرج الإمام

ጁምዓህ ቀን ይማልዳል‹በጥዋት ወደ መስጂድ ይገባ›ና ፡
ኢማሙ ‹ለኹጥባህ›ከመውጣቱ በፊት‹እስከሚጣ ደረስ›ሶላትን ያረዝም (ያበዛ) ነበር ።

[ሙሶነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባህ ቁ 5403]
t.me/abdu_rheman_aman
143 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 08:27:13 አል-ኢማሙ'ሻፊዒይ እንዲህ ይላሉ ፦

فإذا راح الناس للجمعة :
صلّوا ‹يعني النافلة› حتى يصير الإمام على المنبر,فإذا صار على المنبر كف منهم من كان يصلي

ሰዎች ወደ ጁምዓህ በሄዱ ጊዜ ፡
ትርፍ ሶላቶችን ኢማሙ ሚንበር ላይ እስከሚወጣ ድረስ ይሰግዳሉ(መስገድ ይችላሉ) ፤
ኢማሙ ሚንበር ላይ ከሆነ ግን ከእነርሱ መሃከል ይሰግዱት የነበሩት ከሶላቶቻቸው ይቆጠባሉ።

[አልኡም 1/198]
t.me/abdu_rheman_aman
144 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 08:25:41 ዐብዱሏህ ኢብኑ ዑመር ኢብኑ -ል-ኸጣብ፦

يُجَمِّرُ ثِيَابَهُ فِي كُلِّ جُمُعَةٍ

በየ ጁምዓው ልብሱን መልካም ሽታ ያለውን እጣን ‹በኹር› ያጥን ነበር ።

[ሙሶነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባህ ቁ 5591]
t.me/abdu_rheman_aman
144 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 07:57:58 የአሏህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ፦

" إِذَا جَاءَ أَحَدُكُمْ الجمعة فَلْيَغْتَسِلْ"

"አንደኛቹ ወደ ጁምዓህ በመጣ ጊዜ ይተጣጠብ።"

[አል-ቡኻሪይ 877]
t.me/abdu_rheman_aman
146 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:16:38 ተጋበዙልኝ ውዶች

ልብን ሰርስሮ የሚገባ
መሳጭ ቲላዋ

https://t.me/umu_reyyis_jilbab_azegaj
https://t.me/umu_reyyis_jilbab_azegaj
175 views𝐮𝐦𝐮 𝐫𝐞𝐲𝐲𝐢𝐬 𝐛𝐢𝐧𝐭 𝐦𝐮𝐠𝐚, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ