Get Mystery Box with random crypto!

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdu_rheman_aman — نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے ن
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdu_rheman_aman — نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
የሰርጥ አድራሻ: @abdu_rheman_aman
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.20K
የሰርጥ መግለጫ

فليس العلم بكثرة الرواية ولا بكثرة المقال.
ولكنه نور يقذف فى القلب يفهم به العبد الحق
ويميز به بينه وبين الباطل. /هـ
አስታያየቶዎንና ምክሮዎን⇩
@Nehnu_abnau_aselefiyin_bot
በዚህ ያድርሱን👆

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 08:14:45 ቀደም ሲል የተለቀቁ የተላላቅ ዑለማዎች ታሪክን ለማንበብ፣ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ያንብቡ!።
1.1K viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 07:43:56 ተብለው ሲጠየቁ "እንደኔ ሀሳብ የዚህ ዘመን (ሙጀዲድ)የተሃድሶ አራማጅ ሸይኽ አልባኒ ነው።" ብለው መናገራቸው ነው።
እኔም እንዲህ ብዬ ላወድሳቸው " እርሶ በሀዲስ እውቀት ላይ የአንቀፁ ልጅ፣ የዓረፍተነገሩ ወንድም፣ የሀረጉ አባት ናችሁ ብዬ ልመሰክር እደፍራለሁ። በስፍራዎ የጥበብ ብርሃኖች ሲንፀባረቁሎት ይታየኛል። እውነትም ከሐዲስ በላይ ምን ጥበብ አለና!"
በመጨረሻም እንዲህ ልበል "የሸይኹን ስም የፈለገ 1 የሐዲስ ኪታብ ገልጦ ይመልከት።"

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينے

••●◉Join us share◉●••

t.me/abdu_rheman_aman
419 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 07:43:30 የደማስቆው ኮከብ፤ የአልባኒያው ልጅ!
****
«ከሰማይ ጠለል በታች በዘመነ ሐዲስ እንደ ሸይኽ ሙሀመድ ናሲሩ አድ-ዲን አል-አልባኒ ስለ ሐዲስ ይበልጥ የሚያውቅ ሰው አላየሁም።» ሲሉ ሸይኽ ዐብዱል ዓዚዝ ቢን ባዝ መስክረዋል።
"ሸይኽ ሙሃመድ ናሲር አድ-ዲን አልባኒ" ይባላሉ!

ሸይኹ በ1914 ዓ·ል መገኛዋን ደቡብ ምስራቅ አውሮፓ ባደረገችው አልባኒያ ምድር "አሽቁደራ" በተሰኘችው ጥንቲቷ ከተማ ተወለደ። ምንም እንኳን ቤተሰቡ በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ውስጥ የነበሩ ቢሆንም አባቱ ወደ ኢስታንቡል በማቅናት የተማረውን የሸሪዓ አስተምህሮት በሀገሩ ላሉ ወገኖች በማስተማር ያገለግል የነበረ ታላቅ ባለአደራ ሰው ነበር። በዘመኑ የተሾመው ገዥ መሪ [አህመድ ዙጞ] በሁሉም የህይወት ትግበራዎች ላይ ምዕራባዊያንን አርአያ በማድረግ የሀገሩን የአስተዳደር ስርዓት ወደ secularism(መንፈሳዊነትንና ሸሪዓን ያገለለ አለማዊ አገዛዝ) በመለወጥ ብዙ የጥፋት መስመሮችን ዘረጋ።
ሙስሊሟ የአልባኒያ ሴት በግድ ሒጃቧን እንድታወልቅ ፣ ወንዱም አለባበሱ ምዕራባዊያንን የተከተለ እንዲሆን ተደረገ። ብዙ… ብዙ… ብዙ ተደረገ። በዚያን ወቅት ስለ እምነታቸው የተጨነቁ፣ ስለ መጨረሻው መጥፎ ፍፃሜ የሰጉ ምስኪን የሀገሩ ህዝቦች ወደ ሌሎች ሀገራት መሰደድ ጀመሩ። የአልባኒ ቤተሰቦችም ስለ ሀገሩ ዕጣ ፈንታ በማሰብ በሀዘን ቢጨለጡም ምርጫቸውን ስደት አድርገው ሻም ወደምትገኘው የስልጣኔ ማዕከል "ደማስቆ" ገቡ።
ይህ ሀገሩን ለቆ የተሰደደው ልጅ "አል-ኢስዓፍ አል-ኸይሪይ" በተባለችዋ የደማስቆ ትምህርት ቤት ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ተማረ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ አባቱ ትምህርቱን እንዲቀጥል አልፈለገም። ታዲያ እምነታዊ ትምህርቶችን የሚማርበት የተስተካከለ መደበኛ ፕሮግራም ቀረፀለት። ቁርአን፣ ተጅዊድ፣ ሰርፍ፣ የሀነፊያ መዝሀብ ፊቅሂን በማስተማር ይኮተኩተው ያዘ።
ልጁን ከራሱ በላይ ለማድረግ የሚታትር እንዲህ አይነት አባት ያስደስታል። የሀዲስ ጠቢብን የቀረፀ አባት መቼም ቢሆን አሻራው አይለቅም። ይህ ልጅ በአባቱ እጅ ላይ ቁርአንን በመሀፈዝ ለማኽተም በቃ ፣ ብዙ የትምህርት ዘርፎችንም ወረሰ። እንዲሁም አቅራቢያው ከነበሩት ሸይኾች የዓረብኛን ሰዋሰው ትምህርት ቀሰመ።
ወጣቱ እድሜው ወደ 20 ዓመት ገደማ ሲሆን ሸይኽ መሀመድ ረሺድ ሪዳ የሚባል ሰው ያዘጋጀው በነበረው "አል-መናር" ጋዜጣ ጥናት ተፅዕኖ ስር በመውደቅ ወደ ሀዲስና ስነ ሀዲስ ዘርፍ ጥናት በጥልቀት ይመራመር ገባ። በርግጥ አባቱ የሀነፊያን መዝሀብ አጥብቆ እንዲይዝ ይመክረውና በስነ ሀዲስ ጥናት ስር እንዳይገባ ያስጠነቅቀው ነበር። ወጣቱ ግን ሱንናን በግልፅና ትክክለኛ በሆነ መረጃ መከተል የሚሻ ስለነበር ጉዞውን በሀዲስ መስመር ላይ አደረገ። እጅግም ወደደው። ደማስቆ ውስጥ "ዟሂሪያ" በተሰኘችው ቤተ መፅሃፍት በቀን ውስጥ ለ12 ሰዓታት በዚህ ዘርፍ ጥናት ሲቸክል ይቆይ ነበር። ምግብ ትዝ ሲለው ሁሉ አብዛኛውን ጊዜ ቤተ መፅሀፍት ውስጥ ነበር የሚመገበው። ሁኔታውን ሲመለከቱ የቤተ መፅሀፍቱ አስተዳደር በጥናቱ ጉዳይ እንዲበራታ ልዩ ክፍል አበጁለት። እጅጉኑ ለፋ! የሀዲስ ጠቢብ ለመሆንም በቃ! ሙሀዲስ(የሀዲስ ጠቢብ) የሚለው የማዕረግ ስም እንዲሁ የተወሰኑ ትምህርቶችን ላስተማረ ሰው የሚሰጥ ተራ ስም እንዳይመስላችሁ! ብዙ ልፋት ያስፈልገዋል።
(ከአሁን በኋላ ከሊቃውንት ተርታ ተሰልፏልና በአንቱታ ልጥራው)

ሸይኹ ደማስቆ ውስጥ ስማቸው በስፋት ይጠራ ጀመር። ለመጀመሪያ ጊዜ የፃፉትና በተደጋጋሚ ለህትመት የበቃው መፅሃፍ "ተህዚሩ አስ-ሳጂድ ሚን ኢት-ቲኻዚል ቁቡር አል መሳጂድ" ተሰኝቷል። ከዚያ በኋላ ስማቸው እጅግ ከመሰራጨቱ የተነሳ መዲና የምትገኘው ኢስላማዊቷ ዩኒቨርሲቲይ በስነ ሀዲስ አስተማሪነት አጨቻቸው። ለ3 አመታት መዲና ውስጥ ካገለገሉም በስተኋላ የሀዲስ ጥናታዊ ትምህርታቸውን ለማሟላት ወደ ደማስቆ ተመለሱ።
ሸይኹ እጅግ ይደንቃሉ። በሀዲስ ቁልመማ ኡማውን ሲያወናብዱ የነበሩ ቀጣፊዎችን በማጋለጥ የሱንና ጠበቃ ሁነው ነበር።
የሀዲስ ጥናት የህይወታቸው አንድ ክፍል ሆነ። በደም ስራቸው ውስጥ የሚተላለፈውም ደምም የሀዲስ ጥናት ነበር ማለት ማጋነን አይሆንም። በጊዜው የነበሩ ጎጠኛ የቢድዓና የመዝሀብ ጭፍን ተከታዮች እርሳቸውን በጥቁር ዓይናቸው እያዩ የጥላቻን እንባ ያቀሩ ነበር። ሸይኹን በምን አጊንተን እንበቀል የሚለውም የዘወትር ጭንቀታቸው ነበር።ምንም አጥፍተው አይደለም። ቁርአናዊና ሀዲሳዊ መረጃን መሰረት ያደረገን ጉዞ ስለተጓዙ እንጂ! በግፍና በጥላቻ ስሜት ምክንያት ሁለት ጊዜ እስር ቤት ተወረወሩ። ሸይኹ እንዲህ የሚለውን የዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም) ንግግር ይደጋግሙ ነበር፦ «ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው፡፡»

ወህኒ ቤትኮ ለሊቃውንት ራሳቸውን የሚያሰለጥኑበት መድረክ፣ ደስታን የሚላበሱበት ጨፌ እንጂ ምንም አይደለም። ሸይኹም ወህኒ ቤት ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ለአላህና ለመልዕክተኛው ቃል ተገዥ እንዲሆኑ ዳዕዋ አድርገውላቸው ብዙ ሰዎች ዳዕዋቸውን ያለማቅማማት ተቀብለው ነበር። የሚገርመው በደማስቆ የተሳሩበት ወህኒ ቤት ሸይኹል ኢስላም ቢን ተይሚያህ ታስረው የነበሩበት ወህኒ ቤት ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢብኑ ተይሚያህ በኋላ ወህኒ ቤት ውስጥ ሰላተል ጁሙዓ የተቋቋመው እኚህ የአልባኒያ ተወላጅ በታሰሩ ጊዜ ነው።
ሸይኹ በህይወታቸው በርካታ መፅሃፍትን አበርክተው ያለፉ ሲሆን ለህትመት ያልበቁም መፅሃፍትም አሏቸው።
"ኢርዋኡል ጘሊል" ፣ "ሲልሲለቱል አሓዲሲ ሰሒሓ" ፣ "ሲልሲለቱል አሓዲሲ ዶዒፋህ" ዝነኞቹ ሲሆኑ
"ተወሱል" ፣
ኹጥበቱል ሓጃህ፣
ሲፈቱ ሰላቲ አን-ነቢይ፣
ሰላቱ አትተራዊህ ፣
አህካሙል ጀናኢዝ፣
አዳቡ አዝ-ዚፋፍ ………… ወዘተ ለአብነት ተጠቃሾች ናቸው።
ከርሳቸው የእውቀት ማዕድ የተጠቀሙና ሌሎችን በመጥቀም የሚለፉ የርሳቸው ተማሪዎች በርካታ ናቸው።
ሸይኽ ሓምዲ ዐብዱል መጂድና ሸይኽ ዐብዱርራህማን ዐብዱል ኻሊቅ ……ግዙፎቹ ናቸው።
ህልፈት
ሸይኹ ኡርዱን ውስጥ በምትገኘው ኦማን ከተማ በ1999 ዓ·ል ጥቅምት ወር ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ቶሎ ቅበሩኝ ሲሉ አደራ ብለው ነበርና ከዒሻእ ሰላት በኋላ ሊቀበሩ ችሏል።
ሊቃውንት ስለክብራቸው ሲናገሩ፦
«ከሰማዩ ጠለል በታች በዘመነ-ሀዲስ ስለ ሃዲስ እንደ ሸይኽ ሙሀመድ ናሲሩ አድ-ዲን አል-አልባኒ ይበልጥ የሚያውቅ ሰው አላየሁም።» ሸይኽ ቢን ባዝ
ሸይኽ መሀመድ አል አሚን አሽሺንቂጢ መዲና ላይ እያስተማሩ ሸይኽ አልባኒን ሲያልፉ ከተመለከቷቸው ትመህርታቸውን አቋርጠው ቆመው ሰላም ይሏቸው እንደነበር ተወስቷል።
" መፅሃፎቹን ባነበብኩባቸው ጊዜያት ውስጥ በሀዲስ ላይ የብዙ እውቀት ባለቤት መሆኑን አውቂያለሁ።" ሸይኽ ቢን ዑሰይሚን
"በሸይኽ (አል-አልባኒ) መፅሃፎች እውቀትን የምንጨምር ከመሆን አልተወገድንም።" ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋዲዒ
"ይህ ሰው ተበድሏል። ዐረብ ደረጃውን አላወቀለትም። " ሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊ
"ሸይኽ(አል-አልባኒ) ልትተው የማትገባን ድልብ ለትውልዱ አስተላልፈዋል።"
(ሃፊዝ ቢን ዓብዱር'ራህማን አልመደኒይ)
በጣም የደነቀኝ ሸይኽ ቢን ባዝ የዚህ ዘመን (ሙጀዲድ) የተሓድሶ አራማጅና የለውጥ ኃዋሪያ ማን ነው?
302 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:23:06 የኹጥባ መጨረሻ ላይ " أقم الصلاة " ማለት: ከሰለፎች መገኘቱን እኔ አላውቅም። ኢማሞች ሊሏት አይገባም።

[ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን]

المصدر: سلسلة فتاوى نور على الدرب > الشريط رقم [257]


ጁሙዓ ኹጥባ የምታደርጉ ኢማሞች እቺን ብትሰሟት ጡሩ ነው
http://zadgroup.net/bnothemen/upload/ftawamp3/Lw_257_12.mp3
507 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, edited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:01:20 ሴትን ልጅ መሳም ወይም መንካት ውዱእ ያበላሻልን?
=======================

☜ هذه المسألة اختلف فيها أهل العلم على ثلاثة أقوال‏:‏

☞በዚህ ነጥብ ዙሪያ የዕውቀት ባልተቤቶች ወደ ሶስት ንግግር ተለያይተዋል:

☜ القول الأول‏:‏ أن لمس المرأة لا ينقض الوضوء، وأن المراد بقوله تعالى‏:‏ ‏{‏أَوْ لاَمَسْتُمُ النِّسَاءَ‏}‏ ‏[‏سورة النساء‏:‏ آية 43‏]‏ ‏:‏ هو الجماع لا مجرد اللمس‏.‏ وعلى هذا القول لمس المرأة لا ينقض الوضوء مطلقًا‏.‏

☞የመጀመርያው ንግግር : ሴትን ልጅ መንካት ዉዱኧ አያፈርስም የሚል ሲሆን፣ አሏህ በቁርኣኑ ውሥጥ (ሶላትን አትቅረቡ……"ሴቶችን የነካካቹህ ስትሆኑ" ሲል የፈለገው ወሲባዊ ኒኪኪን እንጂ ዝም ብሎ ያለውን ኒኪኪን አይደለም። በዚህ ንግግር ዕይታ: ሴትን ልጅ መንካት ዉዱእ አያፈርስም።

☜ القول الثاني‏:‏ أن لمس المرأة ينقض الوضوء مطلقًا إذا لمسها من غير حائل، وهذا مذهب الشافعية؛ مفسرين ‏{‏أَوْ لاَمَسْتُمُ النِّسَاءَ‏}‏ ‏[‏سورة النساء‏:‏ آية 43‏]‏ باللمس باليد مثلاً‏.‏

☞ሁለተኛው ንግግር : በየትኛውም መልኩ ሴትን ልጅ መንካት ዉዱእን ያፈርሳል፣ ያለ ግርዶሽ ነክቷት እንደሆነ፣ ይሄ የሻፊዒዮች መዝሃብ ነው። (ይሄም መዝሃባቸው የሆነው የ'አላህን ቃል : (ሶላትን አትቅረቡ……"ሴቶችን የነካካቹህ ስትሆኑ" የሚለውን፤ እንደምሳሌ በእጅ መንካትን ብለው ፈስረው ነው።

☜ القول الثالث‏:‏ وهو قول الحنابلة‏:‏ أن لمس المرأة بشهوة ينقض الوضوء، أما لمسها بدون شهوة؛ فإنه لا ينقض الوضوء‏.‏

☞ሶስተኛው ንግግር የሐንበልያዎች ንግግር ነው። እሱም ሴትን ልጅ በስሜት መንካት ዉዱኧ ያፈርሳል፣ ያለ ስሜት መንካት ዉዱእን አያፈርስም የሚለው ነው።

☜ هذه مذاهب أهل العلم فيما أعلم حول هذه المسألة‏.‏

☞በዚህ ነጥብ ዙርያ እኔ በማውቀው ይሄ ነው የሙሁራኖች ዕይታ።

☜ ولعل الاحتياط هو القول الثالث‏:‏ أنه إذا كان بشهوة؛ فإنه ينقض الوضوء؛ لأنه مظنة خروج الشيء منه، والمظنة في كثير من الأمور تنزل منزلة الحقيقة

☞እንደው ለመጠንቀቅ የሚበጀው ሶስተኛው ንግግር ነው። እሱም በስሜት ከሆነ ዉዱኡ ይፈርሳል፣ ምክንያቱም ከሰውየው የሆነ ነገር ሊወጣ ይችላል ተብሎ ያስጠረጥራልና። ብዙን ግዜ ደግሞ ጥርጣሬ የዕውነታን ቦታ ያስወግዳለ።

☜ وإن كان بدون شهوة؛ فإنه لا ينقض الوضوء؛ لأنه ليس هناك مظنة لخروج شيء‏. 

☞ግን ካለስሜት ከነካት ውዱኡ አይፈርስም። ምክንያቱም በዚህን ግዜ ከሰውየው የሆነ ነገር ሊወጣ ይችላል ተብሎ አያስጠረጥርምና።

ምንጭ ፦ አል-ሙንተቃ ሚን'ፈታዋ ሊሸይኽ ሳሊሕ አል-ፈውዛን

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman
407 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 10:06:27
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት ሰው አቶ ደሊል ኑሬ ይባላል የትውልድ ቦታው በስልጤ ዞን አልቾ ወረዳ ልዩ ስሙ አብጀት በሚባል መንደር ተወልዶ ያደገ ሲሆን በደቡብ ምራብ ክልል በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ላይ ኑሮ መስርቶ በመኖር ላይ ሳለ ባጋጠመው የጤና እክል አዲስ አበባ ሂዶ ወንድሞቹ ሳምንት ሲያሳክሙት ከቆየ ቡሀላ ታህሳስ 14(4)2012 ጁምአ ለቅዳሜ ለሊት ወንድሞቹ በተኙበት ወቶ የደረሰበት አልታወቀም የሶስት ሴት እና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ሲሆን እድሜው55 አስከ 58 ባለው ይሆናል ስለዚህ ለአላህ ብላቹህ አንድታፋልጉን ስንል እንማፀናለን

ጠያቂ ባለቤቱ እና ልጆቹ እንዲሁም ቤተሰቦቹ
ስልክ 0923344558
0918948600
280 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:17:26 ማሳዘኗ
====
ያሸይኽ! እኔ እባሌጋር ተጋጭተን እንዲፈታኝ ብጠይቀውም እንቢ አልፈታሽም አለኝ። እና ጓደኞቼን ለመፈታት ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሳማክራቸው፣ ፀጉርሽን ከተላጨሽ ኒካሁ ይወርዳል አሉኝና እኔም ፀጉሬን ተላጨሁት፣ እና ኒካሁ ይወርድልኛል?

[የዛሬ ስንት ዓመት አከባቢ ሸይኽ ……የሆኑ ሸይኽ ሲጠየቁ ከሰማሁት ጥያቄዎች ውስት አንዱ ከላይ የጠቀስኩት ነበር።]

"ሱብሓነሏህ" ይገርማል!! ጓደኞቻ ምን ያክል በድለዋታል!!።

ዛሬ ደግሞ ለመፃፍኳን የሚያሳፍርን ጥያቄ ስሰማ ይሄ ጥያቄ ታወሰኝ።

አብደረህማን አማን
303 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, edited  19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:46:33 ሚስት የረመዷን ቀዷ ኑሮባት ቀዷውን ማውጣት ካሰበች፣ ባልየው የመከልከል ድርሻ የለውም።(ማውጣት ትችላለች።)ሊፈቅድላትም ይገባል። ባልየው ቢከለክላት'ኳን እሺ ልትለው አይገባም። ምክንያቱም ቀዷውን እንድታወጣ ያዘዟት አሏህና ነቢያችን ﷺ ናቸውና። በሐይድና በኒፋሳ ምክንያት እረመዷንን ያልፆመች ሴት: ቀዷ ይወጅብባታል ብለው ሙስሊሞች ተስማምተዋል። ባልየውም ቀዷዋን ከማወጣት ሊከለክላት አይገባም።

ግን ትርፍ ፆም ሁኖ ባልየው እቤት ከሌለ ብትፆም ችግር የለውም። እቤት ካለ በሱ ፍቃድጂ እንዳትፆም። ነቢያችን ﷺ እንዲህ ብለዋልና ፦

"لا تصومن امرأة وزوجها حاضر إلا بإذنه"

["ባልየው እያለ በሱ ፍቃድ ቢሆንጂ ሚስት እንዳትፆም።]ባልየው ካለ እሱ ሳይፈቅድልሽ ልትፆሚ አይገባም። ትርፍ ፆም በማለት የፈለኩት፦ የሃሙስ የሰኞ፣ ወይም ስድስቶ የሸዋልን፣ ወይም በየወሩ የሚፆመውን ሶስቷን ቀን የመሳሰሉትን ነው። እነዚህን ለመፆም የባልሽ ፍቃድ የማይቀር ነው። ከፈቀደልሽ ፁሚ፣ ካልፈቀደ እንዳትፆሚ።

አብደረህማን አማን
============
ከሸይኽ ኢብኑ ባዝ ፈትዋ የተወሰደ። የሸይኹን ሙሉ ፈትዋውን ለማንበብ ይሄን ይጠቀሙ
https://binbaz.org.sa/fatwas/8590/%D8%AD%D9%83%D9%85-%D8%B5%D9%8A%D8%A7%D9%85-%D8%A7%D9%84%D9%85%D8%B1%D8%A7%D8%A9-%D8%A8%D8%AF%D9%88%D9%86-%D8%A7%D8%B0%D9%86-%D8%B2%D9%88%D8%AC%D9%87%D8%A7

t.me/abdu_rheman_aman
571 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 14:32:19 የትኛው ይበልጥ ያስፈልጋል

መወደድ

መታመን
300 viewsلَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ