Get Mystery Box with random crypto!

'ወሎ!' = = ኢላሂ ብለሽ ጩሂ ወሎ ተናገሪ የውስጥሽን ስቃይ ሀዘንሽን አውሪ የፖለቲ | نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

"ወሎ!"
= =
ኢላሂ ብለሽ ጩሂ ወሎ ተናገሪ
የውስጥሽን ስቃይ ሀዘንሽን አውሪ
የፖለቲካን ቅጥፈት ተይ ለአሏህ ንገሪ

ታሪክሽን አውጪ ማንንም አትፍሪ
ስቃይሽን አውጪ ኢላሂ ብለሽ ጥሪ

ተስፋችን ሙሉ ነው በአረህማን ጌታችን
መቼም አረሳንሽም በውዱ ዱዐችን

ኡኡ ብለሽ ጩኺ ወሎ ተናገሪ
ሁሉን ቻይ ነውና ፈጣሪሽን ጥሪ

ወሎ!!
ስብርብሩ ይውጣ ይዋረድ ጠላትሽ]

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman