Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊሞች ለኢቲዮጲያ ምንም መስዋአትነት አልከፈሉም ማለት ከደንቆሮነት በተጨማሪ ታሪክን አለማንበብን | نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے

ሙስሊሞች ለኢቲዮጲያ ምንም መስዋአትነት አልከፈሉም ማለት ከደንቆሮነት በተጨማሪ ታሪክን አለማንበብን ነው የሚያሳየው። በጥላቻ ተረግዞ በውሸት የተወለደን ወሬ እንደፈለጉ ከመደስኮር፣ የታሪክ መዛግብትን ብታገላብጡ ነውራቹህን ታገኙት ነበር። ‹በእምነታቸው የተነሳ አጥንታቸው ሰብሳቢ ያጣው በየወደቁበት ያለቀባሪ የቀሩት የእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ እንደነበሩ Raymond Jonas የተባለ ጸሓፊ The battle of Adwa በተሰኘው መጽሐፉ ገልጾታል፡፡
" አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ይኼንን የታሪክ ሐቅ
"ትውልድ እንዳይደናገር እኛም እንናገር" በሚለው መጽሀፋቸው ገፅ 37 – 38 ላይ አስፍረውታል።› ሙስሊሞችን እንዳሻው ሲገድል የነበረን ግፈኛ መንግስትን በምን መልኩ ነው ዛሬ ላይ እሱን የምዘክረው!?። ከጥንት ጀምሮ እንደፈለጉ ሙስሊሙን እያተራመሱ ፣ ወራሪ ጥላት ሲመጣባቸው ሙስሊሙን ከፊት አሰልፈው ትንሽ ድልን ሲጎነጩ 44ቱ ታቦት አሸነፈ እያሉ ይዘምራሉ። ለታሪክ ምስክር ይሆነን ዘንድ፣ ዛሬ ላይ ከTDf ጋር የሚዋጉትን ሙስሊሞች ማየት በቂ ነው።

አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman