Get Mystery Box with random crypto!

ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abagiyorgismnale — ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የቴሌግራም ቻናል አርማ abagiyorgismnale — ዳግማዊ ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የሰርጥ አድራሻ: @abagiyorgismnale
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሕይወትና ትምህርት ይቀርብበታል።
አባ ጊዮርጊስ ምን አለ???
ለሌሎች በማጋራት መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ
ለጥያቄዎችና ለአስተያየት
https://t.me/Mikua @feke17

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 08:32:12 "#ሌላኛዋ_ማርያም " (ማቴ.27:61፤ ማቴ.28:1)
በሐዲስ ኪዳን "ማርያም" በሚል ስም ከሰባት ያላነሱ ሴቶች ተጠርተውበታል ፣ መ"ና"ፍ"ቃ"ን ከድንግል ማርያም በቀር ስለሌሎቹ "ማርያሞች" ይዘምራሉ ፣ ይሰብኳቸዋልም ፣ በላያቸው የሰፈረው አስለፍልፍ ግን ስለ ድንግል ማርያም ክብር እንዲናገሩ አያደርጋቸውም ።
#ከድንግል ማርያም በቀር በሐዲስ ኪዳን የተጠቀሱት "ሁሉም ማርያሞች" ባለትዳር የነበሩና ወንድ የሚያውቁ ናቸው ፣ ድንግል ማርያም ግን ዘላለማዊት ድንግል ስትሆን መቼም ቢሆን ወንድ የማታውቅ ንጽሕት ናት ። (ሉቃ.1:26) ፣ የሁሉም "ማርያሞች" ታሪካቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈልን አንዳቸው ከሌላቸው የሚለዩበት መለያ ቅጽል አላቸው ።
#በዚህ የመለያ ቅጽልነት መሠረት ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ድንግል ማርያምን በተለይ ከታዋቂዋ "ባለትዳሯ ማርያም" የተለየች መሆኗን ሲያሳይ፤ ሌላኛዋ ስመ ሞክሼ "ሁለተኛዋ ማርያም" የምትባል ሌላ ማርያም እንዳለች ይነግረናል ። እርሷም ከድንግል ማርያም የምትለይ ሌላ ማርያም መሆኗን ለማሳወቅ መጽሐፍ ቅዱስ "ሁለተኛዋ ማርያም" ሲል መለያ ቅጽል ይሰጣታል ።(ማቴ.27:61፤ ማቴ.28:1) "ሁለተኛዋ ማርያም" ተብሎ መጠራትም አንደኛ ማርያምነትን ለድንግል ማርያም ሰጥቶ በመናገር የመጣ አገላለጽ ነው ።
#ጎበዝ !!!
#አንደኛዋ ማርያም ፣ ድንግል ማርያምና የሁለተኛዋ ማርያም ባለትዳሯ ማርያም ፍጹም የተለያዩ መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ ይገልጻል ። በርግጥ "ማርያም" የሚለው ስመ ሞክሼ ሁለቱም ማርያሞች ስለሚጠሩበት መለያ ቅጽሉን እስካላወቁ ድረስ ብዙዎች አሁንም ሊደናገሩ ይችላሉ ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ድንግል ማርያምን አንደኛዋ ማርያም በማለቱ ሌላኛዋን "ባለትዳሯ" ማርያምን "ሁለተኛዋ ማርያም" ከሚለው መለያ ቅጽል ጋር ሁለቱ "ማርያሞች" የሚለዩበት ዝርዝር ማንነት ስላስቀመጠልን መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ ሰው መደናገር የለበትም ።
#ድንግል ማርያም በመልአክ ብሥራት ያለወንድ ዘር ኢየሱስን ወልዳልናለች ፣ ከኢየሱስም በቀር ልጅ የላትም ፤ እስከ መጨረሻው ወንድ የማታውቅ ዘላለማዊ ድንግል ናት ፣፤ "ሁለተኛዋ ማርያም" ግን ትዳር መስርታ ልጆች ያሏት ናት ። ልጆቿም ያዕቆብ ፣ ዮሳ፣ ስምዖን ፣ ይሁዳ ይባላሉ ። (ማቴዎስ.13:53፣ ማር.3:31)
ድንግል ማርያም የኢየሱስ እናት ተብላ ስትጠቀስ ፣ "ሁለተኛዋ ማርያም" የእነ ዮሳ እናት ማርያም ተብላ ትታወቃለች ።
#በመጽሐፍ ቅዱስ ድንግል ማርያም ፣ የኢየሱስ እናት ተብላ ተጠራች እንጅ የያዕቆብ ፣ የዮሳ፣ የስምዖን ፣ የይሁዳ እናት ተብላ አልተጠራችም ። ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የተነሱ ሐሰተኛ ሃይማኖተኞች የእነ ዮሳን ( ያዕቆብ ፣ ዮሳ፣ ስምዖን ፣ ይሁዳ ) እናት "የሁለተኛዋን ማርያም" ማንነት ከድንግል ማርያም ጋር እያቆራኙ ከእውነተኛይቱ ሃይማኖት ሕዝቡን አስወጥተውታል ። (ማቴዎስ.13:53፣ ማር.3:31፤ማር.6:3) በዛሬ ዘመንም "ሐሳውያን መሲሖች"" በኦርቶዶክስ ላይ በሚያደርጉት የቅሰጣ ዘመቻ ድንግል ማርያም ያይደለች ሌላኛዋን ማለትም "የሁለተኛዋን ማርያም" ስም እየጠሩ ከድንግል ማርያም ጋር ማንነቷን እያቀላቀሉ መንጋቸውን ያደናግሩበታል ። የኢየሱስን እናት፣ የድንግል ማርያምን ንጽሕና ፣ቅድስናና ድንግልና ላለመቀበል በላያቸው የሰፈረው ክፉ መንፈስ ያስለፈልፋቸዋል ።
#ጎበዝ !!!
#በ"ድንግል ማርያም"ና በ"ሁለተኛዋ ማርያም" መካከል ሰፊ ልዩነት አለ ። #ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ሲሞት፣ ወዲያው ከመቀበሩ በፊት የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያምን ዮሐንስ ወደ ቤቱ ወስዷታል ፣(ዮሐንስ.19:27) የእነዮሳ እናት ባለትዳሯ "ሁለተኛዋ ማርያም" ግን ኢየሱስን ከመስቀል አውርደው ወደ መቃብር ሲያወርዱት ሁሉ ትመለከት ነበር ፤ (ማርቆስ.15:47፤ ማርቆስ 16:1) ፣ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያም አማኝ ናት ፤ ልጇ አምላክ እንደሆነና ሞትን ድል አድርጎ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሳ ታውቃለች ። የእነዮሳ እናት "ሁለተኛዋ ማርያም" ግን ተጠራጣሪ ናት ። ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣም አታውቅም ነበር ። ሰውነቱን ሽቱ ለመቀባት በሦስተኛው ቀን ወደ መቃብሩ ተጉዛለች (ማር. .16:1፤ማቴ.28:1) ፣
#የእግዚአንሔር ቃል የሚነግረን እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ ጸረ ኦርቶዶክሶችና ሐሰተኞቹ በሚያደርጉት ቅሰጣ የኢየሱስ እናት ድንግል ማርያምን ሊያስጥሉን ስለፈለጉ የኢየሱስን አምላክነት ያልተገነዘበችውን የእነ ዮሳን እናት "ሁለተኛዋ ማርያምን" ስም እየጠሩ ኦርቶዶክሳውያንን ሊያሳስቱ ዘመቻ ከፍተውብናል ። (ማርቆስ .6:3)
#ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ኃጢአት ሀሞት ሲያጠጡት መራራውን ታግሶና በመስቀል ላይም ችንካሩን ታግሶ ባለበት ሁኔታ "እነሆ እናትህ !!" ብሎ የሰጠንን እናቱን ድንግል ማርያምን ፤ ማንም አይነጥቀንም ።እርሷ የሥርዐተ አምልኮአችን ምልክት ናት ፤
#ስለእኛ በመስቀል የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ልናመልክ ስለተፈጠርን ፣ በመስቀሉ ስር የተሰጠችንን ድንግል ማርያምን ልናመሰግን ስለተወለድን፣ መስቀሉን ደግሞ ልናከብር ስለተመረጥን እጅግ ደስ ሊለን ይገባል ።
#መቼም ቢሆን ከታች ቮድካ ሰውሮ ከላይ ኮካ የሚጠጣ ሰካራም "ሐሳዊ መሲሕ" ኦርቶዶክሳውያንን ሊያስት አይችልም ። ይኸው ነው።

https://t.me/abagiyorgismnale

ሊቀ ጠበብት ዶ/ር ዘሪሁን ሙላቱ
55 viewsMichael Eshetu, edited  05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:15:19
እመቤታችን በኢትዮጵያዊያን ቅዱሳን ሊቃውንት አንደበት
++++++++++++
  “ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል፣ ይእቲኬ ቤተ ምስአል፣ ለኩሉ ፍጥረት ትተነብል”

“ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያ፣ የጸሎት ቤት ናት፣ ለፍጥረታት ሁሉ የምትለምን አማላጅ ናት”
#ቅዱስ-ያሬድ
+++++++++++++++++++++++
“እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፤ አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፤ ንዌድሰኪ እንዘ ንብል ምክሐ ዘመድነ፤ ዮም በፍሥሓ ለማርያም እምነ፤ አስተርእዮ በሰማይ ኮነ”

“የትንቢት አበባ እግዚአብሔር እኛን ሥጋ የሆነውን የአንቺን ሥጋ ለብሶ በምድር እንደተገለጠ ለእኛም እንዲታወቅ ድንግል ሆይ የባሕርያችን መመኪያ ዛሬ ለእናታችን ለቅድስት ማርያም በሰማይ ፍጹም በደስታ መገለጥ ሆነ እያልን እናመሰግንሻለን”
#አባ-ጽጌ-ድንግል
+++++++++++++++++++++++
“የደናግል መመኪያ የቅዱሳንም የመመረጣቸው አክሊል፣ ያልበደሉት የድንግልናቸው መመኪያ፣ ያላደፉትም የንጽሕናቸው አክሊል፣ ሥጋ የለበሰ ሁሉ መመኪያ፣ ነፍስ የተዋሐዳቸው ፍጥረት ሁሉ አክሊል፣ የነዳያን ሀብት የንጹሐን መመኪያ፣ ለባሕርያችንም መመኪያ ሆንሽ፣ የዓለም ሁሉ መድኃኒት በአንቺ ተደረገ”
#አባ-ጊዮርጊስ-ዘጋሥጫ
133 viewsMichael Eshetu, 13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:13:35 Live stream started
19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 09:20:37
እመቤቴ ሆይ የአንቺን <<ይሁንልኝ >> የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ። ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ሰው መሆን ያቃተኝን እኔንስ ሰው የምታደርጊኝ መቼ ይሆን ? አምላክ ሰው እንዲሆን ይሁን ያልሽዋ ሆይ ስለ እኔ ሰው መሆን <<ይሁን>> የምትዪው መቼ ይሆን ? 'በርታ ሰውም ሁን ' የሚለውን ቃል መጠበቅ አቅቶኝ ኃጢአት ሰልጥኖብኝ ''ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንደሚጠፉ እንስሳት መሰለ '' የሚያሰኝ ሕይወት ለምኖረው ለእኔ ወደ መሐሪው ልጅሽ ‛‛ይህ ኃጢአተኛ ባሪያህ እንደቃልህ ይሁንልኝ’’ ብለሽ እኔንም እንደቃሉ የምታደርጊኝ መቼ ይሆን?

https://t.me/abagiyorgismnale

               ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
              የብርሃን እናት
              ዲ/ን ዘ፲፪ እሸቱ
872 viewsMichael Eshetu, edited  06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:12:57
የፍጥረት አለቆች አዳምና ሔዋን በፊቱ መቆም ያልቻሉትን የአዳምና የሔዋን ልጅ ድንግል ማርያም እንደምን ወሰነችው??? ሰማይና ምድር አይወስኑትም እኮ! ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በቅዳሴው እንደተናገረው ''ዓሣዎች የማይዋኙት ጥልቅ ነው፤ንስሮች የማይበሩት ምጡቅ ነው፤ ኪሩቤል የሚያዩት ረቂቅ ነው፤ ነፋሳት ሩጠው የማይደርሱበት ሰፊ ነው፤ እሳታውያኑ ኪሩቤል ሊነኩት የማይቻል እሳት ነው ፤ ከአርያም በላይ የሚገኝ ልዑል ፤ ከበርባኖስም በታች ያለ እረጅም ነው ...'' ከዚያም በላይ ነው ።ነገር ግን ለመለኮት ነውና ላይገርመን ይችላል መለኮት ሁሉን ይችላልና ። በጣም የሚገርመው በአንዲት የ15 ዓመት ብላቴና ማኅፀን ሲወሰን ከሚያንጸባርቀው ዙፋኑ ከሚወጣ ብርሃናዊ ክብሩ የተነሣ ፊቱን ለማየት ብርሃናውያኑ ፍጡራን ፊታቸውን በክንፎቻቸው የሚጋርዱለት እርሱን በማኅፀኗ ተሸከመችው ። ወዮዮዮዮዮ ድንቅ ነው

ኢይትነገር አላ ይትነከር
https://t.me/abagiyorgismnale

እነርሱ ዙፋኑን እንኳን እንዳያዩ ነው'ኮ  የሚለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፊታቸውን ይሸፍናሉ አለ። እርሷ ግን ዙፋን ሆነችው ፤ ሶስት ክንድ ከስንዝር ሆና ሳለ የማይወሰነውን ወሰነችው ፤ ጠባብ ሆና ሳለ ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎች በማኅፀኗ ተዘረጉ የሚያስደነግጠውና የሚያስፈራው ኪሩቤል የሚሸከሙት ዙፋን በማኅፀኗ ተዘጋጀ።

ኢይትነገር አላ ይትነከር
ይደነቃል እንጂ ሊነገር አይችልም።

           ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መላክ
      ሕይወተ ማርያም ድንግል
       ዲ/ን ዘ፲፪ እሸቱ
210 viewsMichael Eshetu, edited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:24:20
231 viewsMichael Eshetu, 05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:23:58 ★ መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን የርኩሰት ፊልም ያስቁም !

★ ክርስቲያኖች ተጠንቀቁ!! " ፍልሰት" በሚል ርዕስ በቃና ቲቪ የሚተላለፈውን የሴት ሰዶማውያን /ሌዝብያን / ፊልም ፈጽሞ እንዳታዩ።★

እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፣የራሳቸውን ጥቅም እንጂ በትውልድ ሕይወት ላይ የሚያመጣውን መጥፎ ተድኅኖ የማያገናዝቡ ስግብግብ ግለሰቦች ያገኙትን የውጪ ፊልም ሁሉ በገንዘባቸው እያስተረጎሙ ትውልድን እያረከሱ ሃገርን እያቆሸሹ ይገኛሉ።

ይህ "ፍልሰት" የሚል የማታለያ ትርጉም የተሰጠው ፊልም Orfaos da Terra ከሚል የስፔናውያን ቋንቋ የተወረሰ ሲሆን የፊልሙ ዋና ዓላማ በፍቅር ስም የሴት ሰዶማዊነትን/ሌዝቢያዊነትን /በትውልድ ልብ ውስጥ ለማስገባትና ወጣቶችን በረከሰ ተግባር ለማጨመላለቅ በምሥጢር ታቅዶ የተሰራ ፊልም ነው።ፊልሙ እጅግ በረቀቀ ዘዴ ወጣቶችን በመሳብ ልባቸውን እያንጠለጠለ የአዕምሮ እጥበት/Brain wash/ በማድረግ ሴት ከሴት ጋር በዝሙት መጨመላለቅን እንደ ዘመናዊነትና እንደ ሥልጣኔ ለማሳየት የተዘጋጀ አጋንንታዊ ፊልም ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን የተከበረ ባህል፣የተቀደሰ ሃይማኖትና የተለየ ሥርዐት ያለን ክቡር ሕዝቦች ነን ይህንን የተከበረ ማንነታችንን በፊልም፣በሙዚቃ፣በተለያዩ ፋሽኖች በማርከስ ሙሉ ለሙሉ ለሰይጣን ተገዥዎች ለማድረግና ከእግዚአብሔር ሕግ ለማውጣት የውጭና የውስጥ ባንዳ ጠላቶቻችን በብዙ ዓይነት ስልት እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ ይህንን ትውልድ ገዳይ ርኩስ ተግባር ጠንክረን ልንታገልና ልናስቆም ይገባል።

ስለዚህም ይህ" ፍልሰት " በሚል ርዕስ በተከታታይ ለሕዝብ በይፋ በቃና ቲቪ የሚተለለፍ ነውረኛ ፊልም በአስቸኳይ መቆም አለበት። ወላጆች ልጆቻችሁን የሚያረክስ ፊልም ስለሆነ በአስቸኳይ እንዲቆም አድርጉ ልጆቻችሁም እንዳያዩ ከልክሉ ፣ክርስቲያኖች ይህ ዲያብሎስ ቀስ በቀስ እያታለለ ልባችሁን የሚያሸንፍበትና ከእግዚአብሔር እቅፍ የሚለይበት ወጥመድ ስለሆነ አጥብቃችሁ በመቃወም አስቁሙ ፈጽሞ እንዳታዩ። የሃይማኖት አባቶች፣መምህራነ ወንጌል ፣የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ይህንን ትውልድ ገዳይ የርኩሰት ፊልም አጥብቃችሁ ተቃወሙና አስቁሙ።ውሃ ሲወስድ አሳስቆ ነውና እንደ ኖርማል ፊልም አቅልላችሁ የምታዩ ሰዎች መጨረሻ ላይ ሕይወታችሁን በለየለት ርኩሰት ውስጥ ገብቶ ስለምታገኙት ከወዲሁ ነቅታችሁ አቁሙ፣ተለዩ፣ተቃወሙ።

1ቆሮ 6 ፥9

"አመንዝራዎች፡ወይም፡ቀላጮች፡ወይም፡ከወንድ፡ጋራ፡ዝሙት፡
የሚሠሩ፡
10፤ወይም፡ሌባዎች፡ወይም፡ገንዘብን፡የሚመኙ፡ወይም፡ሰካሮች፡ወይም፡ተሳዳቢዎች፡ወይም፡ነጣቂዎች፡
የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡አይወርሱም።
11፤ከእናንተም፡አንዳንዶቹ፡እንደ፡እነዚህ፡ነበራችኹ፤ነገር፡ግን፥በጌታ፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡
በአምላካችንም፡መንፈስ፡ታጥባችዃል፥ተቀድሳችዃል፥ጸድቃችዃል።"
283 viewsMichael Eshetu, 05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 07:28:06 ነገረ ክርስቶስ

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

ክፍል 3

የጌታችን በማህፀነ ማርያም ማደር

ቅድስት ድንግል ማርያም "እንደ ቃልህ ይሁንልኝ " በማለት በእምነት ስትቀበል አካላዊ ቃል በግብረ መንፈስቅዱስ በማህፀኗ የእለት ፅንስ ሆኗል ።ዮሀንስ ወንጌላዊ "ቃል ስጋ ሆነ" በማለት በማህፀነ ማርያም የተፈፀመውን ምስጢረ ተዋህዶ እንደገለፀ መለኮትና ትስብዕት(ስጋ) ያለ መለወጥ ፣ ያለመከፈል ፣ ያለመጨመር ፣ያለ መቀላቀል በእመቤታችን ማህፀን በመዋሀዳቸው ከሁለት አካል አንድ አካል ፣ ከሁለት ባህሪ አንድ ባህሪ ፣ከሁለት ፈቃድ አንድ ፈቃድ ፣ ከሁለት ግብር አንድ ግብር በመሆናቸው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ማህፀን የተዋህዶ እምነታችን የተመሰረተበት ስፍራ ሲሆን የመሰረተውም ስጋችንን የተዋሀደው ክርስቶስ ነው

መለኮት ምሉዕ ነው አይዳሰስም አይያዝም አይራብም አይጠማም ዘመን አይቆጠርለትም ። ስጋ ደሞ ይራባል ይጠማል ውስን ነው ዘመን ይቆጠርለታል። ተዋህዶ ስንል እነዚ የስጋን ባህሪያት መለኮት ሳያጠፋው የመለኮትንም ባህሪያት ስጋ ሳያጠፋው በተዋህዶ አንድ ሆነ ። የአብ ልጅ የማርያም ልጅ ተባለ የማርያም ልጅ የአብ ልጅ ተባለ ። መለኮት በተዋሀደው ስጋ ምክንያት ዘመን ተቆጠረለት 30 አመት ሲሞላው ተባለ ፣ ተራበ ተጠማ በስጋ ሞተ ። ስጋም በተዋሀደው መለኮት አምላክ ሆነ ውስን የነበረው ምሉዕ ሆነ ደካማ የነበረው ብርቱ ሆነ ሟች የነበረው ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ ። ድንግልም እንዳትደነግጥ መልዐኩን ልኮ አበሰራት ፍቃዷንም ጠየቃት እሷም እነሆ የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለችው

ከዛች ደቂቃ ጀምሮ ማንም በማይመረምረው መልኩ ከመላዕክትም በተሰወረ መልኩ በማህፀኗ አደረ ።ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ "ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ እንደምን የድንግል ማህፀን ቻለው ? ይላል። ሊቃውንትም በመተባበር እመቤታችን በሰው መጠን ሶስት ክንድ ከስንዝር ስትሆን ርሷ ግን ከጽርሐ አርያም በላይ ርዝመቱ ከበርባኖስ በታች ጥልቀቱ ከአድማስ እስከ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይመረመር በሁሉ የመላውን አካላዊ ቃል በማህፀኗ የተሸከመች በመሆኗ "የእግዚአብሔር ሀገር " ተብላለች


ይቀጥላል
https://t.me/abagiyorgismnale
196 viewsMichael Eshetu, edited  04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 06:25:20 +አንቺን የሰጠችን ቤተ ክርስቲያን ከፍ ከፍ ትበል+


"ነገር ግን ስለእርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለሁ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ።"


የሚመጥናትን ምን ዓይነት ልዩ ምስጋና እናቅርብላት? የዚኽ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር “ዓለም አልተገባቸውም” (ዕብ ፲፩፥፴፰) ካላቸው፤ ለአምላክ እናትማ ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሓይ ለኾነችው ለርሷ ምን ልንል እንችል ይኾን? (ራእ ፲፪፥፩)

ምን ምስጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናንና አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነ አስተውል፤ ታዲያ የአምላክን እናት ታላቅነት ኹሉም ሰው እንደምን አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ላገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ (የሐዋ ፭፥፲፭)፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ (የሐዋ ፲፱፥፲፩)፤ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኃይል ተሰጥቷት ይኾን?

ለቅዱሳኑ ይኽንን ያኽል ድንቅ እንዲያደርጉ ባለሟልነትን ከሰጣቸው ወልዳ ላሰደገችው እናቱማ ምን ያኽል ይሰጣት ይኾን? በምን ዓይነትስ ስጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ “ክርስቶስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ” ስላለው ብፁዕ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቊልፍ ከተሰጠው (ማቴ ፲፮፥፲፮-፲፱)፤ እርሷ ከኹሉም ይልቅ እንዴት የተባረከች (ብፅዕት) አትኾን? (ሉቃ ፩፥፵፭)፤ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ “ምርጥ ዕቃ” ከተባለ (የሐዋ ፱፥፲፭)፤ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃው ትኾን?

ነገር ግን ስለእርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለሁ ስለዚኽ ካኹን ወዲኽ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ።"

+ሊቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ +
251 viewsMichael Eshetu, 03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:37:38 መምህር የኋላሸት ደመቀ ርዕስ የበጎች በር እኔ ነኝ ዮሐ 10 ፤ 9


242 viewsMichael Eshetu, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ