መጋቢት 29 ††† በዓለ ጽንሰት ††† ††† ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች:: በዚሕ ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር:- 1.ሰማይና ምድርን ፈጠረ:: (ዘፍ. 1:1) 2.በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ (ተጸነሰ):: በዓሉም "በዓለ ትስብእት" ይባላል:: "አምላክ ሰው : ሰው አምላክ የሆነበት" ማለት ነው:: (ሉቃ. 1:26) 3.የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ:: (ማቴ. 28:1፣ ማር. 16:1፣ ሉቃ. 24:1፣ ዮሐ. 20:1) 4.ጌታችን ዳግመኛ ለፍርድ በዚሕች ቀን ይመጣል:: (ማቴ. 24:1) ††† በእነዚህ ታላላቅና ድርብርብ በዓላት ምክንያት ቀኑ "ርዕሰ በዓላት" (የበዓላት ራስ) : "በኩረ በዓላት" እየተባለም ይጠራል:: ††† "እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል:: ዓይንም ሁሉ: የወጉትም ያዩታል:: የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ:: አዎን አሜን:: ያለውና የነበረው: የሚመጣውም: ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ: አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ይላል::" ††† (ራእይ ፩፥፯) እንኳን አደረሳችሁ http://t.me/abagebrekidan http://t.me/abagebrekidan 13.9K viewsÃńŧęŋəĥ, edited 18:12