Get Mystery Box with random crypto!

❖❖❖ አንድ ' ግዩር ' እንዲህ ይመክራል ❖❖❖❖ ሥለ እግዚአብሔር ብለን ሰውን እን | የርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች

❖❖❖ አንድ " ግዩር " እንዲህ ይመክራል ❖❖❖❖

ሥለ እግዚአብሔር ብለን ሰውን እንውደድ እንጅ ስለ ሰው ብለን እግዚአብሔርን መውደድ አይገባንም ። በእግዚአብሔር ፊት ሰውን መውደድህን ይገለጥልህ እንጅ በሰው ፊት የእግዚአብሔር ወዳጅ ለመምሰል ብለህ የምትኖ ር አትሁን ። ለሰዎች ብለህ እንደወደድከው ለሰዎች ብለህ ልትጠላው ትችላለህ እና ።
❖❖❖❖❖❖❖
የእግዚአብሔር ሰው መሆን ማለት እግዚአብሔርን መመገብ እንጅ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም ። ለመዳን ብለህ እወቅ እንጅ በእውቀትህ የምትድን አይምሰልህ ። የማታውቀውን የምታውቀው ልትኖረው እንጅ እውቀቱ በክርስቶስ ቀኝ ሊያቆምህ አይምሰልህ ። በጎ ነገርን ያወቅሃት ዕለት ብቻ ደስ አይበልህ ፥ የሠራሃት ዕለት እንጅ ፥ በመሥራትህም አትመካ አልፈጸምካትምና ። ከእግዚአብሔር ያወቅሃትን መልካም ነገር ወዲያው ሥራት ፥ እየሠራሃት ያለችህን መልካም ነገር አትልቀቃት ። እየኖርክ ተማር እንጅ እየተማርክ ብቻ ዘመንህን እንዳትፈጽም ተጠንንቀቅ ። ያለ ዕውቀት ብትኖር ከፍርድ የምታመልጥ አይደለምና መቼም ቢሆን ከቤተክርስቲያን ጉባዔያት አትታጣ ፥ በማወቅህ ፍርድ አይቀርልህምና ያወቅኸውን ፈጥነህ ሥራ ።
❖❖❖❖❖❖❖
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት ዕወቃት ፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ ዕወቃት ። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን ፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ ። በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ ። እሊህም ፦ ኪዳን ማስደረስ ፥ ማስቀደስ ና ንስሐ ገብቶ መቁረብ ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው ። ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን !

ብቻየን ለፋሁበት ብለህ ገንዘብህን ብቻህን አትጨርሰው ። ከምታገኘው ሁሉ ለመድኀኔዓለም ድርሻ አስቀምጥ ። የለመነህን ሰው አትመርምረው ቢቻልህ ስጠው ባይቻልህ እዘንለት እንጅ ። ለስንፍናህ ሁሉ ምክንያት አታብጅለት ። መልካሙን ነገርም ዛሬ ሥራው ፥ ክፉውን ነገርም ዛሬ ተናዘዘው ። እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ የገነትና የሲዖል ሰው ለመሆንህ ዋጋ እንዳለው እወቅ ።
ይቆየን
መልካም የሆነ እግዚአብሔር ለመልካም የሚሳብ መልካምን የሚያደርግ በመልካሞ የሚጸና በጎ ሕሊና ይስጠን !

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን
ሰኔ ፲፯ - ፳፻፲፪ ዓም
http://t.me/abagebrekidan
http://t.me/abagebrekidan