Get Mystery Box with random crypto!

ትህነግን ማመን ወይም ለትህነግ መዘናጋት ከመቃብሩ ላይ ቆመህ ነው! ለተደጋጋሚ ወረራ የተዳረገው | ዘሪሁን ገሠሠ

ትህነግን ማመን ወይም ለትህነግ መዘናጋት ከመቃብሩ ላይ ቆመህ ነው!

ለተደጋጋሚ ወረራ የተዳረገው ህዝባችን ፣ የደረሰበትን ሁለንተናዊ ስብራት መጠገን ቢከብድም ቢያንስ እነዚያ አስከፊ ጭፍሮች ከፊቱ ገለል ብለውለት ያለስጋት ወጥቶ መግባቱም ትልቅ እፎይታ ነው!

ነገርግን  ዜናውን በመልካምነቱ ከመቀበል ባሻገር አንዳች የሚያስደልቀንና የሚያስፎክረን ጉዳይ አይኖርም! ይሄ የቤቱ ጣራ ሳይቀር እየተነቀለ የተዘረፈበትና ራቅቱን የቀረ ህዝብ ፥ ሀዘኑንም ስቃዩንም የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ስብራቱንም መጠገን የሚቻለው "ትህነግ" የተባለ ቡድን ከነአስተሳሰቡ ጭምር እስከወዲያኛው ሲቀበር ብቻ ነው!

አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታም ፥ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ትህነግን ዋጃ ላይ ጥምር ጦሩን ቆቦ ላይ አስቀምጦ ማዶ ለማዶ እየተያዩ "ህዝቡን መጡ ሄዱ ፥ ጀመሩ አልጀመሩ" በሚል ስጋት ውስጥ እንዲቀጥል ከሆነ ፥ የትናንትናው የትህነግ ለቆ መውጣትን ሌላ ትርጓሜ እንዲይዝ ያደርገዋል!