Get Mystery Box with random crypto!

የአምናው ጭፍጨፋ '…እኒህ የምታዩዋቸው ቤተሰቦች እዚያው ምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ጃርዴጋ ጃርቲ | ዘሪሁን ገሠሠ

የአምናው ጭፍጨፋ

"…እኒህ የምታዩዋቸው ቤተሰቦች እዚያው ምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ጃርዴጋ ጃርቲ ወረዳ ኮቲቻ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ ዐማሮች ነበሩ። ከቀን ጎዶሎ ቀን የኦነግ ታጣቂዎች በኮቲቻ ቀበሌ ገብተው ለወራት ምልክት ሲያደርጉባቸው በከረሙት የዐማራ ቤቶችን በድንገት ወርረው ተቆጣጠሩ። ታህሳስ 18/2014 ዓም።

"…ከወረራው በፊት የዞኑ አስተዳደር ከሚኒሻዎቹ እጅ የሚገኘውን መሳሪያ በሙሉ ነጠቀ። መከላከያውም አካባቢውን ለቆ እንዲሄድ ተደረገ። የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም ድራሹ ጠፋ። የአካባቢው ኦሮሞዎችም ሰፈሩን ለቀው እንዲሄዱ ተደረገ። እናም ዐማራ አፅጂው ማሽን ያለምንም ከልካይ ገባ። ወሮ ፍሬህይወትም በፍጥነት ስልክና ኢንተርኔቱን ከአዲስ አበባ ዘጋች።

"…ከዚያማ ምኑ ይጠየቃል። ኦነግ ጠያቂ፣ ጠበቃ፣ አጋዥ በሌለው የምስኪን ዐማራ ገበሬ ቤተሰብ ላይ ዘመተ። ጭለማ ስለሆነ ከቤቱ የወጣ የለም። ቀን ከአፈር ጋር ሲታገል የዋሉትም፣ ሁላቸውም ደክሟቸው በጎጆአቸው ተሰብስበዋል። ቆይቶ ቀበሌዋ በተኩስ ተናወጠች። ተኳሾቹም እዚህ ቤት ሰብረው ገቡ። እንደገቡም የተኙ ህጻናትን በተኙበት። የነቁትን በተቀመጡበት ረሸኗቸው። በዚህም መሰረት እኒህ ከዚህ በታች በስም የተዘረዘሩት የ አንድ ቤተሰብ አባላት በሙሉ ለዘር ሳያስቀሩ ፈጇቸው። ሟች ታራጆቹም።

1 ይብሬ አድማሱ (አባት)
2 በለጠች ጎባው (ሚስት)
3 ሃሚድ  ይብሬ (ልጅ)
4 መካ ይብሬ (ልጅ)
5 ፋጡማ ይብሬ (ልጅ)
6  አህመድ ይብሬ (ልጅ) 
7 ሙሳ አድማሱ የይብሬ  አድማሱ  ወንድም ነው። ሃሚድ ይብሬ በጨለማው ኩራዝ እያጠና ነበር። እዚያው ተስፋው ላይ ነው ያለርህራሄ የረሸኑት።

"…እነሆ በዓመቱ እዚያው ሆሮ ጉዱሩ ጃርዴጋ ጃርቲ ሰሞኑን ከ200 በላይ ዐማሮች በዚህ መልክ ተጨፍጭፈዋል!

@ዘመድኩን በቀለ

"…ነፍስ ይማር…!!