Get Mystery Box with random crypto!

አሽከርነትና አጋርነት! ' አሽከርነት አጋርነት አይደለም! ' - የሱፍ ኢብራሒም አስተማማኝ ወገ | ዘሪሁን ገሠሠ

አሽከርነትና አጋርነት!

" አሽከርነት አጋርነት አይደለም! " - የሱፍ ኢብራሒም

አስተማማኝ ወገንና ተገን የሌለው እንዲሁም ራሱን ችሎ የማይቆም፤ በፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ የራሱ ፍላጎት፣ ግብ እና ሚና የሌለው፤ አዳሩን እና ተስፋውን በተመን ያስተላለፈ አካል ከተደራጁ ኃይሎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት— አጋርነት ሳይሆን አሽከርነት ነው!

የአቻነት፣ የነፃነትና የትብብር ግምት የማይወሰድበትና የአንድ አቅጣጫ የድጋፍ ፍሰት ያለበት አጋርነት ሳይሆን አሽከርነት ነው። ለአሽከር የሚታሰብ ክፍያ ወይም ዳረጎት የአጋርነት ማስረጃ አይሆንም!
-
በነገራችን ላይ ወገኑን ከድቶ ለአሳዳሪ የሚገባ አሽከር ክፉ እንደሚሆን ይታወቃል! ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወገኖቻችን ላይ የሚፈፀመውን ግፍና ጭፍጨፋ ከመካድ አልፈው ተጎጅዎችን ለመወንጀል የተሰለፉ አካላት ለዚህ ማሳያ ይሆናሉ።

ምናልባት ዛሬ ለአሳዳሪ ሃሳብ፣ የልብ ትርታና እስትንፋስ ሲባል ዘወትር ወገናቸውን የሚዘልፉና የሚቧጭሩ አካላት ነገ አንገታቸውን ቀና አድርገው ለመሄድ እንደማይችሉ መገንዘብ ይኖርባቸዋል!

አሽከርነት አጋርነት አይደለም!