Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግስት የንብረት ማስመለስ አዋጅ በሚል ያቀረበውና በምስጢር የተያዘው ረቂቅ ህግ አነጋ | Zehabesha

የኢትዮጵያ መንግስት የንብረት ማስመለስ አዋጅ በሚል ያቀረበውና በምስጢር የተያዘው ረቂቅ ህግ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል። በሃገር ቤት ሃብት ያፈሩ ሰዎች፣ እንዲሁም ከውጭ ሃገር በሃገር ቤት ቤትና ሌላም ንብረት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸው እየተገለጸ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የባንክ ተጠቃሚው ቁጥር ከሕዝብ ብዛቱ 2 ፐርሰንት በማይሞላበት ሁኔታ 98% ሕዝብ እንዴት አድርጎ የሃብቱን ምንጭ ማስረጃ ማቅረብ ይችላል የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ፤ ሃገር ቤት፣ ቤት የሰራ አንድ ዲያስፖራ በአዲሱ ረቂቅ መሰረት ከ10 ዓመት በፊት ገንዘብ የላከበትን ደረሰኝ ሊጠየቅ ነው። ዶላር በኪሱ ይዞ ገብቶ በሃገር ቤት መንዝሮ ንብረት ያፈራ ሰው የመነዘረበትን ማስረጃ ከየት ሊያመጣ እንደሚችል የሚያውቅ የለም። ይህ ረቂቅ ህግ ግን እያስፈራሩ ገንዘብ ለሚቀበሉ ባለስልጣኖች ደንበኛ የሙስና በር የሚከፍት መሆኑም እየተነገረ ነው። ንብረት ያላቸውን ሰዎች ሊወረስ ነው በሚል ሊሰሩት የሚችሉት ወንጀል ከወዲሁ እየተፈራ ይገኛል። ይህ ዲያስፖራውንም በሃገር ውስጥ ንብረት ያፈራውን ሰው ያስደነገጠው ረቂቅ አዋጅ ጉዳይ ላይ ባለፈው ቅዳሜ በሰበር ዜና ካቀረብነው መረጃ ተጨማሪ መረጃ አቅርቡልን ባላችሁን መሰረት ረቂቁ የያዛቸውን ነጥቦች እጃችን ከገባው ባለ 37 ገጽ ሰነድ እንደሚከተለው እናቀርብላችኋለን።