Get Mystery Box with random crypto!

መለማመድ መለማመድ መለማመድ በኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ ከ ሚካኤል ጆርዳን ጋር ስጫወት ይላል ስቲል | የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

መለማመድ መለማመድ መለማመድ
በኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ ከ ሚካኤል ጆርዳን ጋር ስጫወት ይላል ስቲል አልፎርድ
የተባለ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ ከ ሚካኤል ጆርዳን ጋር ስጫወት ቡድኑ ውስጥ ከነበሩ ታላላቅ ተጫዋቾች ችሎታና በእርሱ ችሎታ መካከል ክፍተት ነበር ያስገረመኝ የነበረው ግን ሁልጊዜ ሲመጣ መጀመሪያ ሲሔድ መጨረሻ ነው በልምምድ ዋጋ ይከፍል ነበር።
ቢርድ ቢራርሊይ የአሜሪካ ሴናተር ከመሆኑ በፊት ጎበዝ የቅርጫት ኩዋስ ተጫዋች ሆኖ ነበር በ ስፖርቱ ጎበዝ የሆነበት ምክንያት ገና ሁለተኛ ደረጃ ትምርትቤት እያለ በቀን ለ4 ሰዓት ይለማመድ ነበር የአሁኑ ጊዜና ያለፈው ጊዜ በሚለው የግል ማስታወሻው ውስጥ የሚከተለውን ብሎ ነበር
"የቡድን አባላቶቼ ከሔዱ በኁዋላ እኔ ለመለማመድ ወደኁዋላ እቀር ነበር ልምምዴን የምጨርሰው ሜዳው ላይ ከአሉት ከእያንዳንዱ ምልክቶች 15 ቅርጫቶችን በተከታታይ ሳስቆጥር ነበር"ይላል።ከሳተ ከመጀመሪያው ደግሞ ይጀምራል ይህንን ጠንካራ የልምምድ ዝግጁነት ያዳበረው አንተ ባትለማመድ የሆነሰው የሆነቦታ እየተለማመደ ነው ከዚያ ሁለታችሁ ስትገናኙ እኩል ችሎታ ቢሰጣችሁ እንኩዋን እሱ ያሸንፋል የሚለውን የልምምድ አስፈላጊነት የተረዳበት ፅንሰ ሀሳብ ይዞ በመከተሉ ነው በህይወት የትኛውም ቦታ ላይ ለመድረስ ብቸኛው መንገድ ለዛ ነገር ጠንክሮ መስራት እንደሆነ መማር ያስፈልጋል

ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ እንደተናገረው
በፍቅር ተፃፈ