Get Mystery Box with random crypto!

'አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!' በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ። አዲስ እይታ በንግድ እና ኢንቨስ | የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

"አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!" በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ።

አዲስ እይታ በንግድ እና ኢንቨስትመንት የማማከር ሥራ አገልግሎት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "አዲስ እይታ ለስኬታማ ቢዝነስ!" በሚል ርዕስ ለተለያዩ አካላት ስልጠና ተሰጠ።

ቦሌ በሚገኘው በዓለም ሲኒማ ዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2014ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና ላይ ቢዝነስ የጀመሩ ማህበራት አባላት እና ስራ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

የሰው ባህሪ እና የቢዝነስ ስነ-ልቦና ፣ በቢዝነስ ውስጥ ስኬትን ማስቀጠል እንዴት ይቻላል፣ ቢዝነስ ለመስራት እራስን መስራት ፣ የቢዝነስ አመራርና አስተዳደር እና የማኑፋክቸሪንግ ቢዝነስ ባህሪያት በሚሉ ርዕሶች በዶክተር ወሮታው በዛብህ በዶክተር እዮብ ማሞ ፣በዶክተር ኤሊያስ በላይ ፣ በአቶ ሳሙኤል ተክለእየሱስ ፣ በአቶ ክብረት አካሳ እና በአቶ ተመስገን ዐብይ ተሰጥቷል።

ከአዲስ እይታ የስልጠና መርሐግብር ፍጻሜ በኃላ ከዚህ ቀደም የአዲስ ህይወት ስልጠና ወስደው በስራ ላይ የሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች እና አጋር አካለት የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አዲስ እይታ የኢትዮጵያ የንግድ ህግ አዋጅን መሰረት በማድረግ በወርሃ ጥር 2007 ዓ.ም የተመሰረተ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የቢዝነስ ማማከር አገልግሎት፣ የቢዝነስ ስልጠናዎችንና የስነልቡናዊ ምክሮችን የሚሰጥ የግል ተቋም ነው።
(ጌች ሐበሻ)