Get Mystery Box with random crypto!

በመጪው ሚያዚያ ወር መጀመሪያ 9 ሚሊየን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ክትባት ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባ | YeneTube

በመጪው ሚያዚያ ወር መጀመሪያ 9 ሚሊየን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ክትባት ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ::

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ኢትዮጵያ አባል በሆነችበት የአለም አቀፉ የኮቫክስ የጋራ ትስስር በኩል የሚገባውን ክትባት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል::

ክትባቱ በተያዘው አመት ሚያዝያ መጀመሪያ እንደሚገባ የገለፁት ሚኒስትሯ ክትባቱም በተለይም ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በቅድሚያ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል::

ይሄንን ሃላፊነት የሚወጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱንም ገልፀዋል::ከክትባቱ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ አሁንም ቢሆን መከላከል ላይ ትኩረት እንዲያደርግም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል::

@YeneTube @FikerAssefa