Get Mystery Box with random crypto!

ኦነግ በምርጫው ለመሳተፍ እየተፍጨርጨርኩ ነው አለ:: የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በውስጣዊ የፖ | YeneTube

ኦነግ በምርጫው ለመሳተፍ እየተፍጨርጨርኩ ነው አለ::

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በውስጣዊ የፖርቲ ቀውስ የተነሳ በ6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ አጣብቂኝ ውስጥ መውደቁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አሳውቋል፡፡የፖርቲው ቃላቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ምርጫ ቦርድ ፖርቲው የገጠመውን ችግር ለመቅረፍ አሰቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያደርግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ቢሰጥም በተቀዳሚ ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እንቢተኛነት ማድረግ እንዳልቻለና እና ልመና ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ውዝግቡ ከተፈጠረ ወዲህም ምርጫ ቦርድ ጋር በስመ ሊቀመንበርነት የግንባሩ ተወካይ ናቸው በሚል ግንኙነት ስላላቸው ፈጽሞ የጋራ ውሳኔና መመሪያ እየሰጡም ፤እየተቀበልንም አይደለም ነው የሚሉት አቶ ቀጀላ፡፡እኛ ምርጫ ቦርድ ችግሮን ተገንዝቦ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠን እና ወደ ምርጫ ዝግጅቱ እንድንገባ እየጠየቅን ነው ይላሉ፡፡

አሊያም ግን ምርጫ ውስጥ የማይሳተፍ ፖርቲ ጥቅሙ ምን ሊሆን ይችላል ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡በዚህ አይነት ከሄድንም የእርሳቸው ስብስብ በምርጫው ለመሳተፍ አይችልም ምክንያቱም ህጋዊ አይደለም ባይ ናቸው ፡፡

የእኛ ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ከእርሳቸው ጋር የሚያደርገውን ግንኙንት እንዲያጤነውና መፍትሔ እንዲሰጠን ነው ምክንያቱም ይህ ነገር አግባብነትም ሆነ ፍትሐዊ አይደለም ነው የሚሉት አቶ ቀጀላ፡፡

ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሄድ የግድ መሆኑን የሚያነሱት አቶ ቀጀላ አሁን ድርጅታዊ ቀውስ ውስጥ ስላለን ወደ ምርጫው መግባት አንችልም ከባድ ብለው፡፡ችግሮ እስኪፈታ ምርጫ ቦርድ በልዩ ሆኔታ ቀናትን ገፋ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን፡፡ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ምርጫውን መካፈል ከባድ ሊሆን እንደሚችል ነው ያነሱት፡፡

@YeneTube @FikerAssefa